Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የእግዚአብሔር ፍቅር

    የክርስቶስ የፀጋ ሐብት በእግዚአብሔር ፍቅር አማካኝነት ለቤተ-ክርስቲያንና ለዓለም ተነሳ፣« እግዚአብሔር እንዲሁ ዓለሙን ወዲልና አንድ ልጁን እስኪለወጥ ድረስ፣ በእርሱ ያመነ ሁሉ አንዳይጠፋ የዘለዓለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጂ፡፡› (ዮሐንስ 3:16) ለእኛ ለኃጢዓተኞች እንዲሞት ክርስቶስን ያስገደደው ፍቅር ከማስተዋላችን በላይ ነው፡፡GWAmh 97.3

    ከሕግ ጋር ብቻ ኃጢዓት በነገሠበት አካባቢ የክርስቶስ ፀጋ በበለጠ መገኘቱን የሚዘነጋ ሰው እንዴት ይጐዳ? ሕግ አንደሚገባው ከተብራራ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይገልጻል፡፡ በቀዘቀዘ ሁኔታ ሲነገር ግን የሰዎች ልብ አለመነካቱ አያስደንቅም፡፡ ሕግና ክርስቶስ ያላቸውን ግንኙነት ለማዛመድ ወንጌላዊያን ሲያቅታቸው ሰዎች በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ ያላቸው አምነት ይቀንሳል፡፡GWAmh 97.4

    አንዳንድ ሠራተኞች ስለሕግ ሲናገሩ ኃጢዓተኞችን በጥብቅ ይነቅፋሉ፡፡ ክርስቶስን ለዓለም እንዲሞትና አንዲሰጥ ያደረገው የአብ ፍቅርም ተደብቆ ይቀራል፡፡ የእውነት መምህር ነኝ የሚል ሁሉ እግዚአብሔርን በእውነት ያስተዋውቅ፡፡ የጠፋውን ልጅ ለመቀበል የሚጓጓ፣ ክስ የማይደረድርበት፤ ለመመለሱ የደስታ ምልክት ድግሥ የሚያዘጋጅ የፍቅር አባት መሆኑን ያስረዳ፡፡ ነፍሳትን ለመመለስ የእግዚአብሔርን መንገድ ሁላችንም ብናውቀው እንዴት መልካም ነበር?GWAmh 97.5

    እግዚአብሔር የሰዎችን አስተሳሰብ በራሳቸው የአእምሮ የመመዘን ከሚያገኙት እውነት መልሶ በፀጋ የተሞላ ክቡር እምነት ያድላቸዋል፡፡ የሰዎች ምርምር፤ ተፈጥሮን በመመልከት በፈጣሪነቱ ምክንያት ለእግዚአብሔር ሊሰጥ የሚገባውን ክብር ያጠፋዋል፡GWAmh 98.1

    አንዳንድ ወንጌላዊያን አገልግሎታቸውን በሙሉ አከራካሪ ያደርጉታል፡፡ ከሰሚዎቹ መካከል በሰሙት ልባቸው የሚነካና የሚደሰቱ አሉ፡፡ የክርስቶስ አዳኝነት ቢነገራቸው የተዘራው ዘር በልባቸው በቅሎ ፍሬ ይሠጥ ነበር:: ግን የክርስቶስ መስቀል አብዛኛውን ጊዜ ለሕዝቡ አይቀርብም፡፡GWAmh 98.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents