Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ውሳኔና ቆራጥነት

    በሐሳብ መንጃ የማይነዱ ራሳቸውን የቻሉ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ሥራቸው ሠልቶ አንዲቀርብላቸው የሚፈልጉ፣ ለተወሰነ ደሞዝ የተወሰነ ሥራ ለማከናወን የሚፈልጉ፣ ሰዎች፣ ሳይሠለጥኑና ችግር ሳይገጥማቸው አንዲሳካላቸው የሚፈልጉ ሰዎች እግዚአብሔር እንዲሠሩለት አይፈልጋቸውም፡፡ ችሎታውን በችግር ቦታ ቢሆንም ለማሳየት የማይችሉ ወንጌላዊያን አገልግሎት ገጣሚ አይደሉም፡፡ በጠባያቸው የጸኑ፣ የሀሳብ ሽባነት የሌለባቸው ሰዎች ጌታን ሊያገለግሉ ይችላለ፡፡ በአላቸው ሥጦታ ሳይሠሩበት አጋጣሚና ምቹ ጊዜ ቢያገኙ ትልቅ ሙያ የሚፈጽሙ መሆናቸውን የሚያወሩ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡ በሣል አሳቢነትና ራስን መቻል በአሁኑ ዘመን በጣም ይፈለጋሉ፡፡ የግልን መታወቂያ አጥፍቶ ሌላውን ለመምሰል መሞከር፣ ማንም ሳይሆኑ የሚያስቀር አደገኛ ልምድ ነው፡፡GWAmh 81.2

    ለእግዚአብሔር ሥራ የሚገጥሙ ሰዎች ትክክለኛውን መንገድ ወዲያ ተመልክተው ሳያመነቱ የሚሠሩ ናቸው:: በችግር ጊዜ በማውጣት በማውረድ ብዙ ጊዜ ብታሳልፍ የምትፈጽመው በጣም ጥቂት ነው፡፡ በየአቅጣጫው ችግር ያጋጥምሃል፡፡ ካልተቋቋምከው በቀር የችግር ማዕበል ያሰጥምሃል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሀሰትና ዕውነት ተደባልቀው የማይለዩ ሲሆን ጥብቅ የምርጫ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡ ተገቢውን ተግባር በተገቢው ጊሼ መፈጸም መልካም ነው፡፡ ነገር ማመዛዘን መልካም ቢሆንም መወጠላወጠል ሲበዛ የሚፈጸመጡ ሥራ አጭር ይሆናል፡፡ ብዙ ማመንታት መላእክትን ያሠለቻል፡፡ ዘለዓለም በምርጫ አማካኝቶ ሲያነክስ ከሚኖር ይልቅ አንድ ነገር አከናውኖ ከስህተቱ የሚማር ይሻላል፡፡GWAmh 81.3

    መሸነፍ ሊደርስ ወይም ድል መንሳት ሊገጥም የሚችል በደቂቃ በሚወሰን አጭር ጊዜ ውስጥ መሆኑን ተገልጦልኛል፡፡ እግዚአብሔር ሳናወላውል እንድንሠራ ይፈልገናል፡፡ መዘግየት፤ ጥርጥር፣ ማመንታትና አለመወሰን ለጠላት ምቹ ጊዜ ይሰጡታል፡፡GWAmh 82.1

    ጊዜን ጠብቆ መሥራት ለወንጌል ሥራ ዕድገት ይሠጠዋል፡፡ ብዙ የድል አጋጣሚዎች ጊዜ በማሳለፍ አምልጠዋል፡-: በዚህ ምክንያት ችግር ይነሣል፡፡ የማያዳግምና ቆራጥ ሥራ ክቡር ድልን ሲያስገኙ ማመንታትና ግዴለሽነት አውቆ እግዚአብሔርን አንደማዋረድ ይቆጠራል፡፡ ፈጣን አንቅስቃሴ የጠላትን ኃይል ይበትናል፡፡ ምክንያቱም የተቃና ተቃውሞ ለማቀድ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡GWAmh 82.2

    በአደጋ ጊዜ አለመወላወል ተፈላጊ መሣሪያ ነው: መልካም ውጤት ለማግኘት አስቦ ማቀድ ተፈላጊ ቢሆንም፤ ፈጥኖ ተፈላጊውን ነገር አለመመልከት በጣም ይጐዳል፡፡GWAmh 82.3

    አእምሮአችን ተፈላጊ ውሳኔ አንዲወስን ማሠልጠን ተገቢ ነው: ጥንቃቄ ማስፈለጉ አይጠረጠርም፡፡ አጥብቆ መቸኮል ይጎዳል፡፡ ቢሆንም ላድርግ ልተው በማለት ጊዜን ማባከን ተገቢ አይደለም፡፡ ጥንቃቄ በመጠኑ ሲሆን ያገለግላል፣ ግን በችኮላ ከደረሰው ጥፋት ይልቅ በማመንታት ያለፈው መልካም አጋጣሚ ይበልጣል፡፡GWAmh 82.4

    የራሳቸውን የደስታ ፍላጐትና አጉል ምኞት ለጊዜው የተቋቋሙ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ:: ለጊዜው ቁምነገረኞች ይመስሉና ያን ጠባያቸውን የዕለት ተግባር ማድረጉ ያታክታቸዋል፡፡ ግዴለሽነት ቀስ በቀስ ይጠጋቸዋል፡፡ ዓይናቸውን ዘግተው (ጨፍነው) ስህተትን እንዳላዩ ዝም ይሉታል፡፡ ፈተናን በመቋቋም ፋንታ ድል ይሆኑለታል፡፡GWAmh 82.5

    በእግዚአብሔር ቃል የተጠረገ ጐዳና ከሀሰት መንገድ ጋር ለመስማማት አይደራደርም/ጊዜ አይወስድም፡፡ የክርስቶስ ጥረት ሰዎችን በሙሉ ወደእርሱ ለማቅረብ ነው፡፡ ዓለም አንዲያንቀላፉ ለማድረግ አልመጣም፡፡ ነገር ግን ለሰዎች ጠባቧን የሕይወት መንገድ አመላክቶ በእርሷ አንዲጓዙ ለማድረግ መጣ፡፡ መሪያቸው እርሱ ሲሆን ተከታዮቹ በዕምነት መከተል አለባቸው፡፡ ምንም ዓይነት መስዋዕትነት ቢጠይቅ፣ ምንም ያህል አድካሚ ቢሆን፣ በእየለቱ ከራሳቸው ጋር መዋጋት አለባቸው፡፡GWAmh 82.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents