Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአሥራት አጠቃቀም

    አሥራትን እንዴት አንደምንጠቀምበት እግዚአብሔር የተለየ መምሪያ ሰጥቶናል፡፡ በገንዘብ አጦት ምክንያት ሥራው አንዲስተጓጎል አይፈልግም፡፡ ድንግርግርና ችግር አንዳይፈጠር ግልጽ ያለ ደንብ ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር ለራሱ ለይቶ ያስቀመጠው የሀብታችን ክፍል ካቀደለት ሥራ ለሌላ ሞያ እንዲውል አይፈልግም፡፡ ማንም አሥራቱን አስቀርቶ ራሱ እንደመሰለው ሲጠቀምበት አይፈቀድለትም፡፡ አስቀርቶ ለችግር ማዋል ወይም መልካም ለመሰላቸው ነገር መጠቀም አይችሉም፡፡ ወንጌላዊ የአሥራትን ቅዱስነት በጥብቅ ማስረዳት ይገባዋል፡፡ እርሱ ራሱ ወንጌላዊ ስለሆነ በመሰለው መንገድ የሚጠቀምበት መስሎት እንዳይታለል፡፡ የራሱ ሀብት አይደለም፡፡ የራሱ መስሎ የሚሰማውን ሁሉ እንደመሰለው ለማድረግ ነጻነት የለውም፡፡ አሥራትን እግዚአብሔር ካቀደለት መስመር ውጭ በሌላ ሥራ ላይ በማዋል ወንጌላዊ መጥፎ ምሣሌ መሆን የለበትም፡፡ በእግዚአብሔር መዝገብ ተጠብቆ እግዚአብሔር በፈቀደው የሥራ መስመር መዋል አለበት፡፡GWAmh 142.1

    እግዚአብሔር መጋቢዎቹ ሁሉ የእርሱን ትዕዛዝ አክብረው እንዲያስከብሩ ይፈልጋል፡፡ እንደመሰላቸው ምጽዋት በመመጽዎት ወይም ሌላ ደግ መስሎ የታያቸውን ሥራ በመሥራት የእግዚአብሔርን ህግ ማቃወስ የለባቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ እንደመሰላቸው ለዋውጠው እንደሚስማማቸው ቢያደርጉት ሰዎችን ገደል ገቡ እንደ ማለት ነወ፡፡ እግዚአብሔር ማንኛውንም ሰው ሕጉን አንዲያከብር ይፈልጋል፡፡ እቅዱን ለሁሉ : የእርሱ ተባባሪ ለመሆን የሚፈልጉ ሁሉ የደነገገውን ደንብ መከተል አንጂ ሰማሻሻል መሞከር የለባቸውም፡፡GWAmh 142.2

    እግዚአብሔር ሙሴን ስለ እሥራኤሎች እንዲህ አለው «አንተም መብራቱን ሁል ጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ የወይራ ዘይት ያመጡልህ ዘንድ የአሥራኤልን ልጆች እዘዛቸው፡፡(27፡20) የእግዚአብሔር ቤት ለአገልግሉት የሚያስፈልገው አእንዳይጎድልበት ይህ የዘለዓለም ትዕዛዝ ዛሬም ሕዝቦቹ የእግዚአብሔር ቤት የእርሱ ሀብት መሆኑን አውቀው ያለማቋረጥ ሊሠራለት አንደሚገባ ይገንዘቡ፡፡GWAmh 142.3

    ምንም ቢሆን ለቤተ ክርስቲያን ሕንጻ መሥሪያ የአሥራት ገንዘብ አያገለግልም፡፡ ለሕዝባችን አንዳስተላልፈው ግልጽ መልዕክት ተሰጥቶኛል ምንም አንኳን መልካም ሥራዎች ቢሆኑ አሥራት እግዚአብሔር ላላዘዘው ሥራ መዋሉን አስጠንቅቆኛል፡፡ አሥራትን በዚህ መንገድ የሚጠቀሙበት ሰዎች ከእግዚአብሔር መንገድ መራቃቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለፍርድ ያቀርባቸዋል፡፡GWAmh 143.1

    አንዳንዶች የአሥራት ገንዘብ ሰትምህርት ቤት ሥራ ይዋል ይላሉ፡፡ ሌሎችም ለመጽሐፍ መሸጥ እንጠቀምበት ብለው ሐሳብ ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን የአስራት ገንዘብ ትክክለኛ ሥራው ለወንጌላዊያን አበል ነው፡፡ አሁን አንድ ወንጌላዊ ባለበት ቦታ በደንብ የሠለጠኑ አንድ መቶ ወንጌላዊያን መኖር ነበረባቸው፡፡GWAmh 143.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents