Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለወንጌል ሥራ መከናወን ቁልፍ ነው

    በወንጌል ሥራ የተሰለፉ ወይም ገና የሚሰለፉ ወጣቶች ብሉይንና ሐዲስን ተንትነው ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ ይህን ያደረጉ እንደሆን አዕምሮዋቸው ይሰፋል ዕውቀታቸው ይጠልቃል፡- አእምሮዋችን ካልሠራንበት ይዝጋል።- የማሰብ ልምድ ከሌለው አዲስ ሀሳብ ሊያመነጭ አይችልም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት ክባድ ጥያቄዎች ጋር አእምሮውን የሚያታግል ወጣት የአእምሮ ብስለቱ ይጐለምስለታል፡፡GWAmh 60.1

    ቃለ-እግዚአብሔርን ጠለቅ አድርጐ ካጠና፣ በሚያስተምረው ትምህርት አማካይነት ሰዎች ዕውነትን ከሀሰት እንዲለዩ ይረዳቸዋል፡-: በቂ ዕውቀት ሳይኖረው ሊያስተምር የሚሰለፍ ወንጌላዊ መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል፡፡ ግን ባለው ዝቅተኛ ዕውቀት የቻለውን ያህል አየሠራ ለከፍተኛ ዕውቀት የሚጣጣር ከፍተኛ ሥራ ለመፈጸም ተስፋ አለው:: ሰራሱ ተጨማሪ በብርሃን አንደተቀበለ መጠን ለሌሎች ሰማያዊ የብርሃን ሙራ ሊያሳይ ይችላል፡፡- በወንጌላዊነት ጉድለቶች መወገድ አለባቸው:: ምክንያቱም የምናዳርሰው የወንጌል መልዕክት በጣም ኃይለኛ ነው፡፡ አሳዛኙ ነገር ብዙ ወንጌላዊያን ቃለ-እግዚአብሔርን ጠለቅ አድርገው ለማጥናት አይጨነቁም፡፡ ሌሎችን ለመርዳት የሚያስችል ኃይል ሰመቀበል ከፈለጉ ይህን የስንፍና ስሜት ማስወገድ አለባቸው፡፡GWAmh 60.2

    ወንጌላዊያን በፍጹም ልባቸውና በሙሉ ሀሳባቸው የመጽሐፍን ትርጉም ቢሹ ታላቅ ኃይል ይታደላሉ፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ከልቡ ሲፈልግ መለኮታዊ ፀጋ በሕይወቱ ውስጥ ይሰጠዋል፡፡ በልቡም እንዲህ ሊል ይችላል፡፡ «ነፍሴ ሆይ ለእግዚአብሔር ተገዥ” (መዝሙር ፅ2፡፡5)፡፡GWAmh 60.3

    ነፍሳትን ለማዳን እንዲሳካላቸው የሚሹ ወንጌላዊያን ጸሎትኞችና መጽሐፍ ቅዱስን ተመራማሪዎች መሆን አለባቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ሳያጠኑ ቃለ-እግዚአብሔርን ለሌሎች አስተምራለሁ ማለት ኃጢዓት ነው፡፡ የነፍሳትን ክቡርነት የሚገነዘቡ ወንጌላዊያን ሳያጠኑ ለማስተማር መሞከርን በነፍሳት አውቆ አንደመጫወት ይቆጥሩታል፡፡ ለራሳቸው የሥራ ዕርምጃም አንቅፋት መሆኑን ያምኑበታል፡፡ ከላይ ለሥራቸው ማስተማመኛ ምልክት ካላገኙ አያርፉም፡፡GWAmh 60.4

    ሠራተኛው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሲተዋወቅ ሥራው ይሳካለታል፡፡ ሳያቋርጥ ዕውቀቱ ስለሚጨምር ክርስቶስን ለሰዎች ማስተዋወቅ አይከብድበትም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የዕውነት ዕውቀት በአዕምሮው ስለታተመ የሚያስተምራቸው ሰዎች ይባረካሉ፡፡ በዚህ መንገድ ለሥራው ሠልጥኖ የተገኘ ወንጌላዊ ብዙዎችን ወደ ጽድቅ ለሚመለሱ የሚሰጥ ዋጋ አያልፈውም፡፡GWAmh 61.1

    በሌሎች የተደረሱ መጻሕፍትን ማንበብ፤ የሊቃውንትን ንግግር ማዳመጥ በጣም ተፈላጊና የሚረዳ ነው:: ግን ይህ ለአእምሮአችን የተፈለገውን ከፍተኛ ብርታት አይሰጠውም፡፡GWAmh 61.2

    አአእምሮን ለማበልጸግና ለማስፋት መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ከሚገኙት መጻሕፍት ሁሉ ይበልጣል፡፡ እርሱን ማጥናት አእምሮን ያሠራል፤ ማስተዋልን ያሻሽላል፤ የማስታወስን ችሎታ ያጐለምሳል፡፡ የሚያወሳቸዉ፡ ታላላቅ ቁም-ነገሮች፥ የእነዚህ ቁምነገሮች ግልጽ አቀራረብ፣ ስለ ኑሮ የተሰጡት ፍቱን መፍትሄዎች የማስተዋልን ችሎታ ያፋፋሉ፡፡GWAmh 61.3

    በፊታችን በተደቀነው ታላቅ ጦርነት ድል ለመንሣትና ለክርስቶስ ታማኝ ሆኖ ለመገኘት የሚፈልግ ሁሉ ሀሳቡ ከዓለማዊ ትምህርትና ወግ መላቅና መጥለቅ አለበት፡፡ ለወጣቶች ሆነ ጠና ላሉ ወንጌላዊያን የምሰጠው ምክር «በጸሎት ትጉ፤ መጽሐፍን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ ከጊዜአችሁ ከፍላችሁ አምላክን ለመገናኘት መድቡ፡፡ እንዲህ ብታደርጉ መንፈሣዊ ብርታት አግኝታችሁ ሀሳባችሁ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ይሰምራል፡፡ ከፍተኛ የሥራ አንቅስቃሴ ሊሰጣችሁ የሚችል፣ ጠባያችሁን ሊያሻሸለው የሚችል እርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደ እርሱ ብትቀርቡ ንጹህ ልብ ግልጽ አስተሳሰብ ይሰጣችኋል» የሚል ነው::GWAmh 61.4

    የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሊስተዋል የሚችል በተሰጠበት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡ ከፍ ያለ ዕውቀት ለማግኘት፣ እንደሚያዘን መኖር አለብን:: የእግዚአብሔር ቃል የሚያዘንን ሁሉ መፈጸም አለብን፡፡ በኋላ የተሰጠውን ተስፋ ሁሉ ወራሾች አንሆናለን:: በእግዚአብሔር ዕርዳታ የተፈለገብንን ልንፈጽም እንችላለን:: መጽሐፍ ቅዱስ ሊጠና የሚችለው በዚህ ዘዴ ነው፡፡GWAmh 61.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents