Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስህተትን መታገስ

    በደረሰብን ወይም የደረሰብን በመስለን በደል መበሣጨት የሰለብንም፣ ክሁሉ አብልጠን ልንፈራው የሚገባ ጠላታችን ራሳችን ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ካልተገዛ ሰብዓዊ ፍቶት የበለጠ ጠባይን የሚያበላሽ ነገር የለም፡፡ ራሳችን ድል ከመንሣት የበለጠ ክቡር ድል ልንቀዳጀ አንችልም፡፡GWAmh 317.3

    ስሜታችን በቀላሉ አይቁሰልብን፡፡ ልንኖር የሚገባን ስሜታችን ለማስደሰት ወይም ስማችን ለሰመጠበት ሳይሆን ነፍሳትን ለመመለስ ነው፡፡ ነፍሳትን ለመመለስ ስንነሳሳ በመካከላችን የሚነሳውን ቀላል አለመግባባት ከጉዳይ አንቀጥረውም፡፡ ሌሎች የፈለጉትን ቢናገሩና ቢያስቡ ከክርስቶስ ጋር ያለንን አንድነት፤ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለንን ህብረት ሊያደፈርስብን አይገባም፡፡ «ኃጢዓት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋኝሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሱ፤ ይህን ነገር በእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል፡፡» (1ኛ ጴጥ. 2፡20)GWAmh 317.4

    አትበቀለሉ፤ በተቻላችሁ መጠን ላለመግባባት ምክንያት የሚሆኑትን ነገሮቸ ለማስወገድ ሞክሩ፡፡ ክፉን ለማስወገድ ችላ አትበለ፡፡ ሕሌናችሁን ሳትክዱ ክሌሎች ጋር ሰመታረቅ ማንኛውንም ነገር አድርጉ፡፡ «እንግዲህ መባህን በመሰዊያው ላይ ብታቀርብ፣፤ በዚያም ወንድምህ ባንተ ላይ አንዳች አንዳለው ብታስብ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሄድ፣ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ በኋላ መጥተህ መባህን አቅርብ፡፡» (ማቴ. 5፡23፤24)GWAmh 318.1

    የቁጣ ቃላት ሰው ቢናገርህ በዚያ መንፈስ ሆነህ አጸፋውን አትመልስ፡፡ «ለስላሳ ምላስ ቁጣን ታበርዳለች» (ምሳ. 15፡1) የሚለውን አስታውስ፡፡ ዝም በማለት አስገራሜ ኃይል አለ፡፡ ለተቆጣ ሰው መልስ መስጠት ማባባስ ነው፡፡ ግን በቁጣ የተነሳን ሰው በጸጥታ ሲቀበሉት ቁጣው ይበርዳል፡፡GWAmh 318.2

    የሚከነክን የስድብ ቃል ሲሰነዘርብህ የእግዚአብሔርን ቃል ካንተ ዘንድ አትለይ፡፡ ልብህና አእምሮህ በእግዚአብሔር ተስፋዎች ይሞሉ፡፡ ክፉኛ ብትበደል ወይ በሀሰት ብትከሰስ እንዲህ የሚሉትን የከበሩ ተስፋዎች ለራስህ ደጋግም፡፡ «ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትስነፍ፡፡› (ሮሜ 12፡21)GWAmh 318.3

    «መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ በርሱም ታመን እርሱም ያደርግልፃል፡፡ ጽድቅህን አንደ ብርሃን፤ ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣል፡፡» (መዝ. 37:5-6)GWAmh 318.4

    « ግን የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም፡፡»› (ሉቃስ 12፡2) «በራሳችን ላይ ሰውን አስረገጥኸን በአሳትና በውኃ መካከል አሰፍን፤ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን፡፡» (መዝ. 62:12) ወደ ክርስቶስ በመመልከት ፋንታ ከሰዎች ዘንድ ማጽናኛንና ማበረታቻን አንፈልጋሰለነን፡፡ በክርስቶስ አንድንተማመን ሰ.ል እግዚአብሔር የተማመንባቸውን ሰዎት አንዲተውን ይፈቅዳል፡፡ በዚህ በኩል ሥጋ በሰበሰ ክንዱ ታምኖ መደገፍ ስህተት መሆኑን አንረዳለን፡፡ በሙሉና በትህትና በጌታ እንተማመን፡፡ ልንገልጸው የማንችለውን የልባችን ሀዘንና ጭንቅ እርሱ ያውቀዋል፡፡ ዙሪያው ሲጨልምበብህና ነገሩ አልስተዋልህ ሲል «እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም ግን ታስተውለዋለህ» ዘየሐ. 13፡7) ያለውን የክርስቶስ ቃል አትርሳ፡፡GWAmh 318.5

    የዮሴፍንና- የዳንኤልን ታሪክ አጥፍ እግዚአብሔር ሊጎዲትቸው ያሰቡትን ሰዎት አድማ አልክለከለም፡ በችግር ጊዜ ታማኝነታቸጡ ላልላላው፤ ዕምነታቸው ላልተጓደለው አገልጋዮቹ ሁሉንም ሰደህንነታቸው አደረገሳቸው፡፡GWAmh 319.1

    በዓለም ውስጥ እስካለን ድረስ ተቃዋሚ አናጣም፡፡ ጠባያችን ለመፈተን አበሳጪ ነገሮች ይገጥሙናል፡፡ የክርስትና ጸጋዎች የሚጎለምሱ እነዚህን አጋጣሚዎች በትክክለኛ መንፈስ በመቀበል ነው፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ካለ በችግርና በፈተና ጊዜ ታጋሾች፣ ደጎች፣ ደስተኞች ልንሆን እንችላለን፡፡ ቀን በቀን ራሳችንን በመግታት ጀግኖች እንሆናለን፡ የተጣለብን ተግባር ይህ ሲሆን ከክርስቶስ ዘንድ ቁርጥ ውሳኔ፣ የማይወዛወዝ አሳብ፤ የማይቋርጥ ትጋት፣ የዘወትር ጸሎት ካልተቀበልን አንዘልቀውም፡፡ ሁሉም የግል ጦርነት መዋጋት ግዴታው ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ካልተባበርን እርሱ ጠባያችን ጨዋ፣ ነሮአችን ጠቃሚ ሊያደርገው አይችልም፡፡ ትግሉን ችላ የሚሉ ብርታት ያጡና የድል ደስታ ይቀርባቸዋል፡፡GWAmh 319.2

    በሰማይ ሰለተጻፉ ሰማያዊ ጥንቃቄ ስለሚደረግላቸው ፈተናችን፣ ችግራችንና ሐዘናችን ትካዜያቸንም መመዝገብ አያስፈልገንም፡፡ መጥፎ መጥፎውን በኩል ብቻ ስናስብ ብዙ መልካካም ነገሮች ይረሱናል፡፡ በየጊዜው የሚጠብቀን የእግዚአብሔር ምህረት፣ መልዓክት በኛ ላይ የሚደነቁበት ፍቅር ይኸውም ክርስቶስ ለኛ ሲል መሰጠቱን እንዘነጋለን፡፡ ክሌሎቹ የበለጠ ችግርና ፈተና የተጋፈጥህ ቢመስልህ ከነዚያ ችግርን ፈርተው ከሰሱት የበለጠ ሰላም እንደተቀበልህ አስታውስ፡፡ ለክርስቶስ መሥራት ደስታና መጽናናት አለበት፡፡ ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያለው እንደማይወድቅ ዓለም ይወት፡፡GWAmh 319.3

    ደስታ የማይሰማህ ብትሆን የልብህን አትናገር፡፡ በሌሎች ሰዎች ሕይወት ላይ ጥላ አትጣልባቸው፡፡ ቀዝቃዛና ብሩህ ያልሆነ ዕምነት ወደ ክርስቶስ ሲያቀርብ : በዚህ መንገድ ሰዎች ወደሰይጣን ወጥመድ ይወድቃሉ፡፡ ችግርህን በማሰላሰል ፋንታ በክርስቶስ ልታገኘው የምትችለውን ኃይል አስብ፡፡ በሀሳብህ ያልታዩትን ነገሮች ለማየት ሞክር፡፡ አስተሳሰብህ ክርስቶስ ወደገሰጠልህ ታላቅ ፍቅር ይመራ፡፡ ሃይማኖት ፈተናን ሊቋቋም፤ ችግርን ሊታገሥ፣፤ በሀዝን ጊዜ ይችላል፡፡ ክርስቶስ አማላጃችን : የሚያማልደው ምልጃ ሁሉ ለኛ ደህንነት ነው፡፡ ክርስቶስ ለርሱ በፍጹም ልባችን የሚሰሩትን የማያከብር ይመስላጊል? እንደተወደደ ዮሐንስ ለርሱ ሲሉ በግዞትና በስደት ያሉትን የማይኀኅበኝ ይመስላችኋል? እግዚአብሔር አንዱንም ከልብ ከሚሠሩለት አገልጋዮቹ መካከል ብቻውን ታግሎ አንዲስነባ: አይተወውም፡፡ ሕይወቱ ከክርስቶስ ጋር የተሳሰረውን ማንኛውንም ሰው ከአንቁ አብልጦ ይጠነቀቅለታል፡፡ ለእንደዚህ ላሉት «መርጨሃለሁና እንደቀለበት ማተሚያ አደርግፃዛለሁ፡፡» (ሐጌ 2፡23) ይለሰዋል፡፡GWAmh 320.1

    ለተሳታፊዎቹ፣፤ ስለ ክርስቶስ በረከት ተናገር፡፡ ለአንዳፍታም ቢሆን አይረሳንም፡፡ የችግር ጊዜ ሲያጋጥመን ትምክህታችን በክርስቶስ ሲሆን የልብ ደስታ ይሰማናል፡፡ ክርስቶስ ስለ ራሱ እንዲህ «የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁ ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ፡፡ የላከኝም ክኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁፍ አብ ብቻዬን አይተወኝም፡፡» (ዮሐ. 8፡ 28፣29)GWAmh 320.2

    ስለ ሌሎች መልካም መናገርን ልመድ፡፡ አብረውህ የሚኖሩትን ሰዎች መልካም ጠባይ ተመልከት አንጂ ስህተታቸውን ለማውጣት አትጣጣር፡ አንድ ስው ስለሠራው ወይም ስለተናገረው ስህተት ለማጉረምረም ስትፈተን ያ ሰው ያደረገውን መልካም ነገር ለማመስገን ሞክር፡፡ አመስጋኝ መሆንን ተማር፡፡ ክርስቶስ አንዲሞትልን እንዲሰጠን ያደረገውን የእግዚአብሔርን ግሩም ፍቅር አትርሳ፡፡ ተጎዳን ወይም ተበደልን አያልን ማውራት አይጠቅምም፡፡ በምሥጋና እንሞላ ዘንድ እግዚአብሔር ምህረቱንና ወደር የሌለውን ፍቅሩን እንድናስብ ይፈልጋል፡፡GWAmh 320.3

    ከልብ የሚሠሩ ሠራተኛች ስህተት ለማሰላሰል ጊዜ የላቸውም፡፡ የሌሎችን ውድቀትና ስህተት በማውረድ በማውጣት ልንኖር አይገባንም፡፡ መለያየትን ጥልን የሚዘራ ለራሱ የሞትን ምርት ያፍሳል፡፡ የሌሎችን ስህተት በመከታተል የሚናሩ በራሳቸው ሕይወት ክፋትን ያሳድጋሉ፡፡ የሌሎችን ኃጢዓት በማኘክ አንደነርሱው ሆነን አናርፋለን፡፡ ግን ስለ ክርስቶስ ፍቅር : ወደርሱ በመመልከት እንደርሱ አንሆናለን፡፡GWAmh 321.1

    በፊታችን ያስቀተመጠልንን ከፍተኛ መመሪያ በመከተል ወደ እግዚአብሔር ዝፋን ልንቀርብ አንትላለን፡፡ እንዲህ ክሆነ ከኛ የሚፈነጠቀው ብርሃን በአካባቢያችን ላሉት ያበራል፡፡ ሌሎችን በመተቸትና በሌሎች ላይ በመፍረድ ፋንታ «ስለራሴ ደህንነት ማሰብ አለብኝ፤ ነፍሴን ለማዳን ከሚሻ መድኃኒቴ ጋር ሰመተባበር ራሴን በትጋት መቆጣጠር አለብኝ፡-፡ ስህተቴን ሁሉ ማስነፍ አለብኝ፡፡ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይገባኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ከክፉ ጋር የሚታገሱትን በማዳከም ፋንታ በመልካም ቃላት ላበረታቸው እችላለሁ» በል፡፡GWAmh 321.2

    እርስ በርሳችን ለመረዳዳት እናፈገፍጋለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሥራ ባልደረቦቻችን ብርታትና ድጋፍ አንደሚያስፈልጋቸው አይስተዋለንም፡፡ ድጋፋችሁ እንደማይለያቸው አረጋግጡላቸው›፡፡ በጸሎታችሁ አትርሷቸው፤ እንደምትጸልዩላቸውም ይወቁ፡፡GWAmh 321.3

    የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ በመምህርነታቸውና በመልዕክትኛነታቸው ምክንያት ልዩ ልዩ ያስተሳስብ ችሎታ ያላቸው ሰዎች አንደሚያጋጥሟቸው ይገንዘቡ፡፡ የተማሩና ያልተማሩ፤ ኩሩና ትሁት፣ መንፈሣዊያንና ከሕዲዎች፣ ሐብታምና ጨዋና ባሰጌ ያጋጥሟች፲3ል፡፡ እነዚህን ሁሉ የፍቅርና የርህራሄ መንፈስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከነርሱ ጋር ስንገናኝ የኛም አስተሳሰባችን የተስተካክለ፤ ንግግራችን የታረመ መሆን ይገባዋል። በሰብዓዊ ወንድማማችኘነት ስለተሳሰርን መረዳዳት ያስፈልገናልና አንዱ ለሌላው ድጋፍ ነው፡፡GWAmh 321.4

    ክርስትና ለዓለም የሚታወቀው በማህበራዌ ያኗኗር ዘዴ ነው፡፡ ስለ ክርስቶስ ያወቀ ማንኛውም ሰው ላሳጠቁት ብርሃን ያብራ፡፡ በክርስቶስ መንፈስ የተቀደሰ የማህበራዊ ነሮ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ በመመለስ ለሊሻሳል ይገባዋል፡፡ ክርስቶስ በተቀበለው ሰው ልብ ውስጥ የተደበቀ መገዘበብ ሆና ሊቀመጥ አይገባውም፡፡ ክርስቶስ በውስጣችን የሚፈለፍል የሕይዎት ምንጭ ይሁን፡፡፡ ከኛ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ሁሉ የሚያረካ ይሁን፡፡GWAmh 322.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents