Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወንጌል ለአህጉር ሁሉ

    ሰዎች ልባቸው እንዲመለስ የዕውነት ብርሃን መብራት: በአህጉር ሁሉ ወንጌል መታወጅ አለበት፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በቅርብና በሩቅ መሥራት አለባቸው፡፡ የወይኑ ቦታ መስፋት: ቀኑ አልፎ ሌሲት ሳይተካ ጠንክረው መሥራት አለባቸው፡፡ ኃጥዓን አዳኝን ሊያዩ: ከብዙዎች ልሣን «አነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግድ” የሚለው ድምፅ መነገር አለበት። ቤተክርስቲያኖች ተቋቁመው የተቋቋሙት አቢያተ-ክርስቲያናት የታሰበበት ጠቃሚ ሥራ መሥራት አለባቸው፡፡ ዮሐንስ 1:29::GWAmh 15.4

    በጥፋት አፋፍ ላይ ለደረሱት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የሚማጸኑ ራሳቸውን የሚክዱ ሰዎች ያስፈልጋለ፡፡ ሳይዘሩ መከር፤ሳይጥሩ ውጤት አይገኝም፡፡ አብርሃም ከቤቱ ወጥቶ ለአህዛብ መብራት እንዲያበራ ተጠራ፡፡ ያለጥያቄ ታዘዘ «የሚሄድበትን ሳያውቅ ወጣ፡፡› ዛሬም የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር ሲጠራቸው በዕምነት መከተል አለባቸው፡፡GWAmh 16.1

    የዓለም ታላቁ ችግር የክርስቶስ ሞት በከንቱ መስሎ መታየቱና ሠይጣን ድልን የተጐናጸፈ መስሎ መታየቱ ነው፡፡ ከምድር ኗሪዎች አበዛኛዎቹ ለሠይጣን ታማኝነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻ ጊዜ በምድር ሳይ የሚደርሰው ክፋት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል፡፡ የትንቢትን ፍጻሜ ስንመለክት የክርስቶስ መንግሥት ድል አድራጊነት ይገባናል /ይስተዋለናል/:: የተጣለብንን የሥራ ክፍያ በድፍረት ማከናወን አለብን፡፡GWAmh 16.2

    የማስጠንቀቂያው ቃል በአስቸጋሪ ቦታዎችና በኃጢዓት በተበከሉ ከተማዎች ውስጥም መታወጅ አለበት፡፡ ሁሉም ወደበጉ ሠርግ መታደም /መጋበዝ/ አለበት፡፡ ለይምሰል ሳይሆን ከልብ መልዕክቱ ከአገር ወደ አገር ከከተማ ወደ ከተማ መዳረስ አለበት፡፡ ክርስቶስ አንዳደረገው ወንጌሉ በቃልና በምግባር የተገለጸ አንደሆን ተቀባይነትና ትርጉም ይኖረዋል፡፡ በዚህ ዘመን እያንዳንዱ ሠራተኛ ከሕይወት ምንጭ ዕውነተኛ ሕይወት መቀበል አለበት፡፡ የአገልግሎታችን ታላቅነትና ስፋት በቀላሉ እንገምተዋለን፣ የማያወዛውዝ ዕምነትና የማይናጋ ድፍረት ያስፈልገናል፡፡ የሥራ ጊዜአችን በማጠሩ ከልባችን ጠንክረን መሥራት አለብን፡፡ «አርሻው ይህ ዓለም ነው::» ይህ አባባል ምን ያህል ቦታ አንደሚያጠቃልል ከሐዋርያቱ ይልቅ ሰእኛ ግልጽ ነው፡፡ ወንጌልን ሰዓለም ማዳረስ ከባድ ሥራ ነው፡፡ ግን ዱሮ አስቸጋሪ የነበሩ ቦታዎች ዛሬ በቀላሉ የሚደርስባቸው መሆኑ ያስደሰታል፡፡ ዕብራዊያን 11:8 ማቴዎስ 13:38፡፡GWAmh 16.3

    ዱሮ ዝግ የነበሩ አገሮች አሁን በራቸውን ለወንጌል እየከፈቱ ናቸው፡፡ አንዲያውም ቃለ-እግዚአብሔር እንዲብራራላቸው ይለምናሉ፡፡ ነገሥታትና ልዑላን በአገራቸው የመስቀሉ ታሪክ ይወራ ዘንድ ፈቅደዋል፡፡ አሁን በቅንነትና በደግነት የተካሄደ ሥራ ዘለዓለማዊ ዋጋውን ያገኛል፡፡GWAmh 16.4

    ረድዔት አልተለየንም፣ከሰው ጥረት ጋር ወሰን የሌለው ኃይል ይሠራል፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ በግልጽ ለመመልከት የማይችሉ ዓይኖች ከዕውር ይቆጠራሉ፡፡ ቸሩ ጠባቂ በጐቹን ሲጠራ የማይሰሙ ጆሮዎችም ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ እያንዳንዱን ሰው አንዲያውቀው ይፈልጋል፡፡ የእርሱ ጠባይ በአያዳንዱ ሰው ላይ እንዲታተም ይፈልጋል፡፡ በዚህ ምድር ሳለ መንግሥቱ ዓለምን በሙሉ እንዲያጠቃልል ሥራና ሕብረት ማስፈለጉን በደንብ አስገነዘበ፡፡ ይህች ዓለም ሰዎችን ነፃ ለማውጣት የገዛት ሀብቱ :GWAmh 17.1

    «በፊቱ ስላለው ደስታ” «መስቀልን ለመሸከም አላፈፈም” ወደመሬት ያደረገው ከዘመቻ በክንቱ ሳይሆን ነፍሳትን ለማትረፍ ስለሆነ አስደሰተው: ለአብና ለበጉ ክብርን የሚጨምር ድል ለመጎናጸፍ ገና ብዙ የሚሠራ ሥራ አለ፡፡ አሕዛብ ወራሾቹ ይሆናሉ፡፡ ምድር ከዳርቻዋ እስከዳርቻዋ ድረስ የእርሱ ትሆናለች:: ክርስቶስ የነፍሱን ዋጋ ሲመለከት ይደሰታል፡፡GWAmh 17.2

    «ብርሃንሽ መጥቷልና የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሽ አብሪ አነሆ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፡፡ ነገር ግን በአንች ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንች ላይ ይታያል፡፡ አህዛብም ወደብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ፡፡ አይኖችሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከች:: እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንች ይመጣሉ: ወንዶች ልጆች ከሩቅ ይመጣሉ:: ሴቶች ልጆችሽን በጫንቃቸው ይሸከሙአቸዋል፡፡ በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንች ስለሚመለስ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንች ስለሚመጣ አይተሽ ደስ ይልሻል፡፡ ልብሸም ይደነቃል ይሰፋማል፡፡ ዕብራዊያን 1፲2:3፤ ኢሣይያስ 53:11.GWAmh 17.3

    «ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፤ ገነትም በሯን እንደምታበቅል እንዲሁ እግዚአብሔር ጽድቅና ምሥጋናን በአሕዛብ ፊት ያበቅላል፡፡”GWAmh 17.4

    ለደቀመዛሙርቱ የተሰጠው መሪ ቃል ለእኛም ተሰጥቶናል፡፡ ዛሬም እንደዚያን ጊዜው ሞቶ የተነሳው የሱስ በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ ማለት አለበት: ጌታ ቀሳውስትን መምህራንንና ወንጌላዊያንን ይጠራል፡፡ አገልጋዮቹ በእየአገሩ የመዳንን መልዕክት ሊያበሥሩ ይገባል፡፡ ለነገድ፣ ለወገንና ለቋንቋ ሁሉ በክርስቶስ አማካይነት የተገኘውን የይቅርታ የምሥራች መናገር አለባቸው፡፡ መልዕክቱ ሊነገር የሚገባው በቀዘቀዘ መንፈስ ሳይሆን ክልብ በሆነ በሚያነቃቃ ጥልቅ ስሜት ነው፡፡ ሕይወታቸውን ለማዳን የሚረዳቸውን ማስጠንቀቂያ ለመስማት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ይጠባበቃሉ:፣ ዓለም በክርስቲያኖች ላይ የክርስትናን ኃይል ማየት አለበት፡፡ በተለዩ ቦታዎች ሳይሆን በዓለም ዙሪያ የምህረት መልዕክት መዳረስ :GWAmh 17.5

    የክርስቶስን ፍቅር በግልጽ ሊያይ የቻለ ሰው ሀሳቡ ጥልቀትና ምጥቀት ይኖረዋል፣ ልቡ ይነፃል፣ ጠባዩም ይለወጣል፡፡ ለዓለም የክርስቶስት ፍቅር የሚያንጸባርቅ ብርሃን ይሆናል፡፡ የክርስቶስን መስቀል ከፍተኛ ግምት ስንሰጠው ከሐዋርያው ጋር እንዲህ ማለት እንችላለን፡፡GWAmh 18.1

    «ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት፣ እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሴላ ትምክህት ይራቅ::”GWAmh 18.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents