Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወጣት ሚሲዮናዊያን

    ሚሲዮናዊያን ለመሆን የሚከጅሉ ወጣቶች ጥብቅ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ያልተማሩ፤ ያልሰለጠኑ፣ ያልተሞረዱ ወጣቶች ብዙ ተቃዋሚ ባለበት የሥራ መስክ ገብተው ሊያገለግሉ አይችሉም:: የፍልስፍናና የጥቅስ ውሽንፍር ዕውነተኛውን ትምህርት ሊያወናብድ በሚሞክርበት ቦታ በመጠነኛ ዕውቀት ሲያገለግሉ አይችሉም፡፡ ለወንጌላዊነት ጉጉት ያላቸው ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ የበሰለ ዕውቀትን መያዝ ተቀዳሚ ግዴታ መሆኑን መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ሥራውን በቆራጥነት መጀመርና ሲማሩም ትህትናንና ገርነትን ከታላቁ መምህር መማር ተገቢ ነው፡፡GWAmh 50.2

    ቃል ኪዳንን ጠባቂው አምላክ ለሚጸልዩ ሁሉ የጽድቅ አገልጋይ ይሆኑ በዘንድ መንፈሱን አንደሚያፈስላቸው ተናግሯል፡፡ ሀሰትን ከሰዎች አስተሳሰብ አስወጥቶ ዕውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘር በሰዎች ልብ ውስጥ የመዝራት ታላቅ ሥራ አለ:: ወጣቶችን ለልዩ ልዩ የሚሲዮናዊነት ሞያ ማሰልጠን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትዕዛዝ ስለሆነ ኮሌጆች አቋቁመናል፡፡ ብቁ ሠራተኞች አንዲሰለፉ የአምላክ ፈቃድ ነው::: ሰይጣን ግን ይህን ሐሳብ ለማጨናጐል ለአምላክ ሥራ ብዙ ሊጠቅሙ የሚችሉትን ለራሱ አስቀርቷል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ብዙ ሊጠቅሙ የሚችሉትን ለራሱ አስቀርቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ብዙ ሰዎችን ለሥራው ማዘጋጀት ሲገባት አጥሯን አጥብባ በአጭሩ ብትወሰን ለጠፉት ሰዎች ተጠያቂ ትሆናለች፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶች ለሥራው መዘጋጀት ነበረባቸው፡፡GWAmh 50.3

    የመስቀሉን ድል አድራጊነት የሚያበሥሩ፣ በችግርና በመከራ ልባቸው የማይሰበር፤፣ ለሚስዮናዊ ሥራ ንቃትና ሃይማኖት ያላቸው ቆራጥ ወጣቶች ያስፈልጉናል፡፡GWAmh 50.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents