Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሀብት ናት

    የሱስ ባረገ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ቅዱስ ሀብት (ውርስ) አድርጎ ለተከታዮቹ ተወላቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥራ ለኃላፊዎች ወይም ለወንጌላዊያን ብቻ የተሰጠ አይደለም፡፡ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ቢሆን ለአምላክ ሊሠራ ቃል እንደገባ እያንዳንዱ ሰው የሚሠራው የሥራ ድርሻ፣ የሚሸከመው ሸክም አለው፡፡ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አባሎች የግል ኃላፊነት ቢሰማቸው ሥራው በበለጠ ይገሠግሣል፡፡ የኃላፊነት ሸክም የሚሰማቸው ስዎች እግዚአብሔር ፀጋና ብርታት አንዲሠጣቸው ሁል ገዜ ይማጸኑታል፡፡ የቤተክርስቲያን ስራ የሚሳካው በምትመለምላቸው ታላላቅ ባለሙያዎች፤ ወይም በመዘገበቻቸው የአባሎች ቁጥር ሳይሆን ባሏት ትጉህና ታማኝ ሠራተኞች ብዛት ነው፡፡ በንግግር ወይም በስብከት ከሚከናወነው ሥ'ራ ይልቅ መስዋዕትነትን በሚጠይቅ የግል አገልግሉት የሚካሄደው ሥራ ያመዝናል (ይበልጣል)፡፡GWAmh 125.1

    ወንጌላዊያን ለአባሎች፣በመንፈስ ሊጎለምሱ የሚችሉት ነፍሳትን ወደ እውነት የመምራት ኃላፊነት ሲሰማቸው መሆኑን ያስተምራቸው፡፡ ኃላፊነታቸውን ችላ የሚሉ ሰዎች ሊያነጋግራቸው፣ ሊጣርላቸውና ሊጸለይላቸው ይገባል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላትን በወንጌላዊያን ላይ አንዲተማመኑ አታድርጓቸው፡፡ ይልቅስ በአካባቢያቸው ላሉት የእግዚአብሔርን ቃል የማዳረስ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስተምሩአቸው፡፡ ይህን ሲፈጸሙ የመልአክትን ዕርዳታ ከማግኘታቸው በላይ ሃይማኖታቸው ይጎለምሳል፤ እግዚአብሔርንም በበለጠ ይጠማጠማሉ፡፡GWAmh 125.2

    የወንጌላዊ ሚስት (ባለቤት)GWAmh 125.3

    በጥንት ጊዜ የወንጌላዊያን ሚስቶች ችግርና ፈተና ደርሶባቸው ችለውታል፡፡ ባሎቻቸው ሲታሠሩ አንዳንድ ጊዜም ሲገደሉ የስቃዩ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ለባሎቻቸው የሚሰጠው የክብር ዋጋ ለእነዚያ ቆራጥ ሴቶችም ይታደላል አንጂ አይቀርባቸውም፡፡ ወይዘሮ ቦረድማንና ወይዘሮ ጀድሰን ከባለቤቶቻቸው ጋር ተሰቃይተዋል፡፡ በጨለማ ለነበሩት መብራት ለማብራት ባሎቻቸው ሲነሱ እነርሱም ዘመድ አዝማዳቸውን፣ ቤት ንብረታቸውን ትተው ተከተለው ሄዱ፡፡ ይህን ያደረጉት ለተሠወረባቸው የጌታን ቃል ምሥጢር ለመግለጥ ነበር፡፡ ኑሮአቸው የስቀቀን ኑሮ ነበር:: ዓላማቸው ነፍሳትን ለማዳን ስለነበር የመጣ ቢመጣ አልተከፉም፡፡GWAmh 125.4

    የወንጌላዊ ሚስት ከባሏ ጋር ወደሌላ አገር ብትጓዝ አገር ለመጎብኘትና ራሷ ለመደሰት ሳይሆን ለመሥራት አስባ መሄድ አለባት፡፡ መልካም ለመሥራት ከባሏ ጋር የሕብረት ሃሳብ ሊኖራት ይገባል፡፡ ከቤት ሥራ የተረፈውን ጊዜዋን ነፍሳትን ለመመለስ ባሏን በመርዳት ማዋል አለባት፡፡ በየቀኑም ቢሆን በትህትናና፣ በገርነት፣ በማስተዋልም መስቀሏን ተሸክማ ታላቅ ምሣሌነት ማሳየት አለባት፡፡ ሰዎች የሚጠባበቁ ይህን ነው፡፡ ሊጠባበቁም ይገባቸዋል፡፡ ይህ የባለቤቱ አገልግሉት ካልተጨመረበት የወንጌላዊው ሥራ ግማሹ ተበላሸ ማለት ነው፡፡ የወንጌላዊ ሚስት ከፈለገች ብዙ ልታከናውን ትትላለች፡፡ የራሷን ጥቅም ፈላጊ ካልሆነች፣ ነፍሳትን የመመለስ ፍቅር ካደረባት ከባሏ ያላነሰ ሥራ ልትስራ ትችላለች፡፡ ከእህቶቻችን መካከል የወንጌል ሠራተኛ ከተገኘች ወንጌላዊው የማይደርስበትን የአህቶቻችን ችግር ልታቃልል ትችላለች፡፡GWAmh 126.1

    በቀላሉ ልታልፈው የማትችል ኃላፊነት በወንጌላዊ ሚስት ላይ ተጥሎባታል፡፡ እግዚአብሔር ያደላትን መክሊት እንድትሠራበት ይፈልጋል፡፡ ነፍሳትን ለማዳን ከባሏ ጋር ተባብራ በታማኝነት ከልቧ መሥራት ይገባታል፡፡ በባሏ ሥራ አለመደሰቷን፣፤ መናፈቋን ፍቅር እንዳላት መናገር አይገባትም፡፡ የተፈጥር ስሜቶች ሁሉ መወገድ ይገባቸዋል፡፡ ያለ ማያቋረጥ የሚቀጥል የሕይወት ዓላማ ሊኖራት: ይህ ቅዱስ ሥራ ከጊዜአዊ ፍላጎቶች ጋር ቢጋጭስ? ነፍሳትን ለማዳንና መልካም ለመስራት ይህ ሁሉ ሊካድ ይገባዋል፡፡GWAmh 126.2

    የወንጌላዊ ሚስቶች የተቀደሱና ጸሎት አዘውታሪዎች ይሁኑ: አንዳንዶቹ መስቀል (መከራ) የሌለበት ሃይማኖት እንዲኖራቸውና ድካም እንዳይደርስባቸው ይሻለ፡፡ የራሳቸውን ጨዋነት ጠብቀው በመኖር፣ በእግዚአብሔር ብርታት በመደገፍ፣ የግል ኃላፊነታቸውን በማካሄድ ፋንታ በሌሎች ትከሻ ላይ ተደግፈው መንፈሳዊ ኑሮ ከሌሎች ለመዋስ ይሞክራሉ፡፡ ልጅ በአባቱ እንደሚተማመን ሁሉ በእግዚአብሔር ብቻ ቢታመኑ፤ ፍቅራቸው በየሱስ ጸንቶ ኑሮአቸውን በእርሱ ላይ ቢመሠርቱ ምን ያህል መልካም ሥራ ባከናወነ፡፡ ረዳትነታቸው ለሌሎች እንዴት በጠቀመ! ለባሎቻቸው ደጋፊነታቸው እንዴት በጠነከረ! በመጨረሻስ እንዴት ያለ ታላቅ ዋጋ በተከፈላቸው!GWAmh 126.3

    «መልካም አደረግህ አንተ የታመንህ ባሪያህ የሚለው ምስጋና በጆሮአቸው አንደመልካም ሙዚቃ በደወለ «ግባ ወደ ጌታህ ደስታ” የሚለው ግብዣ ድካማቸውን ሺህ አጥፍ አድርጎ ይክሳቸው ነበር :GWAmh 127.1

    ባለትዳር ወንጌላዊ የቤተሰቡን ኃላፊነት ለባለቤቱ ትቶ ለወንጌል ሥራ ቢወጣ ይህች ሜስትና እናት የሆነች ሴት ከባሏ ያላነሰ ሞያ ማከናወኗ አይካድም:: ወንዱ በውጭ ሚሲዮናዊ ቢሆንም ሴቷ ቤት ለቤት ሜሲዮናዊ ነች፡፡ ሰቀቀኗ፣ ጭንቀቷታና ፍርሃቷ ከባሏ የበለጠ ኃላፊነት ጥሎባታል፡፡ ሥራ አድካሚና ተፈላጊ ነው:: የልጆችን ጠባይና አስተሳሰብ በትክክል መምራት፣ ለዚህና ለሚመጣው ዓለም ገጣሚ ሕይወት እንዲኖራቸው ማሠልጠን ቀላል ኃላፊነት አይደለም፡፡GWAmh 127.2

    በአደባይ የሚውለው ባሏ በሥራው ሲከበር እርሷ ግን ድካሟን ማንም አያውቅላትም ይሆናል፡፡ ግን ኃላፊነቷን ስትዘነጋ ሕይወቷን ለፈጣሪ አስገዝታ የልጆችን ኑሮ ወደሰማይ ብትመራ መልአክት ከታላላቅ ሚስዮናዊያን ጋር መድበው ስሟን ይመዘግቡላታል፡፡GWAmh 127.3

    ልቧ በክርስቶስ ፍቅር ከተነካ የወንጌላዊው ሚስት ለባሏ ቀኝ አጅ ልትሆን ትችላለች:: ቃለ እግዚአብሔርን ለልጆቿ ልታስጠና : የቤቷን ሥኑሥርዓት በደንብ ልታካሂድ ትችላለች:: ከባሏ ጋር በመተባበር ልጆቿን ስለኑሮ አቋም ልታስጠናችውና ፍላጎታቸውን አንዲቆጣጠሩ ልታስጠናቸው ትችላለች፡፡GWAmh 127.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents