Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የኃጢዓት ይቅርታ

    ክርስቶስ «ሃኃጢዓታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል» (የሐ. 20:23) አለ፡፡ ክርስቶስ ይህን ሲል አንዱ ሰው በሌላው ላይ እንዲፈርድ ነፃነት መስጠቱ አይደለም፡፡ ይህንማ በተራራው ላይ ስብክቱ አውግዞታል፡፡ ፍርድ ለእግዚአብሔር ብቻ የተጠበቀ መብትና ሥልጣን ነው፡፡ ግን በተደራጀችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ አባሎች ኃላፊነት ጥሎባቸዋል፡፡ የተሳሳቱትን አባሎቿን የማስጠንቀቅ፣ የማስተማር ቢቻልም የመመለስ ግዴታ በቤተ ክርስቲያን ላይ ተጥሉባታል፡፡ አምላክ «እየታገሰህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም» (2ኛ ጢሞ. 4፡2) የሚሳሳቱትን በታማኝነት ቅረባቸው፡፡ በአዳጋ ላይ የሚገኘውን እያንዳንዱን ነፍስ አስጠንትቅ፡፡ ማንም ራሱን ሲያታልል እያየህ ዝም አትበል፡፡ ኃጢዓትን በስሙ ጥራው፡፡ እግዚአብሔር ስለ መዋሸት፣ ስለ ሰንበትን መሻር፣ ስለ ስርቆት፣ ስለ ዝሙት፣ ስለሌላም የኃጢዓት ዓይነቶች ያወጀውን አዋጅ በግልጽ ተናገር፡፡ «እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፡፡» (ገላ. 5፡21) በኃጢዓታቸው በአንተ አማካይነት የተነገራቸው ፍርድ በሰማይ ይጸናባቸዋል፡፡ ኃጢዓት መሥራት ከመረጡ የክርስቶስ አይደሉም፡፡ ቤተ ክርስቲያን አለመስማማቷን ካልገለጠች እርሷም የክርስቶስ አይደለችም ማለት ነው፡፡ ስለ ኃጢዓት እግዚአብሔር የተናገረውን መናገር አለባት፡፡ እግዚአብሔር አንደመራት በኃጢዓት ላይ እርምጃ ከወሰደች እርሱ ሥራዋን ያጸድቅላታል፡፡GWAmh 337.5

    ነገር ግን ባንድ በኩል ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ «ኃጢዓቱን የተዋችሁለት ሁሉ ይቀርለታል፡፡» ይህ ሀሳብ የበላይነት ይኑረው፡፡ የተሳሳተውን ለመርዳት ሁሉም ዓይኑን በክርስቶስ ሳይ : የአምላክ መንጋ ጠባቂዎች ሁሉ ትሁታን ይሁኑ፡፡ ለተሳሳተው ሰው ስለ መድኃኒታችን መሀሪነት ይንገሩት፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን «ከኃጢዓታችን ብንናዘዝ እርሱ የታመነና ጻድቅ ነው ኃጢዓታችንን ይቅር ይለን ዘንድ ከግፍም ሁሉ ያነጻን ዘንድ፡፡» (1ኛ ዮሐ. 1:9) ይበሉ፡፡GWAmh 338.1

    የሚመለሱ ሁሉ ከዚህ በታች የተሰጠው ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል፡፡ «ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፤ ኃጢዓታችንም በባሕር ጥልቅ ይጥለዋል፡፡»GWAmh 338.2

    ቤተክርስቲያን የተመለሰውን ኃጢዓተኛ በደስታ ትቀበለው፡፡ የተመለሰው ስህተተኛ በሃይማኖትና በጽድቅ ፋና እየተመራ ከጨለማ ይውጣ፡፡ የሚዝለውን እጁን በክርስቶስ ክንድ ላይ ያስደግፍ ይህ ዓይነት ይቅርታ በሰማይ ዘንድ ተቀባይነት አለው፡፡GWAmh 338.3