Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የወጣቶችን ስሜት ማስተዋል

    የወጣቶችን ስሜት ልናስተውል የምንችል የደስታና የሐዘናቸው፤ የትግልና የድላቸው ተካፋይ በመሆን ነው፡፡ የሱስ ካመኑትና ከተቸገሩት ርቆ በሰማይ ተቀምጦ ዝም አላለም፡፡ የወደቀውን የሰው ልጅ ዘር ደካማነት፣ ሥቃይና ፈተና ለማወቅ ወደ ምድር መጣ፡፡ እኛን ለማንሳት የወደቅንበት ድረስ መጣ፡፡ ወጣቶችንም ለመርዳት ከፈለግን ያሉበት ድረስ መሄድ አለብን፡፡ ወጣቶች ፈተና ሲደርስበቸው በክርስትና ሕይወታቸው የገፉ ሰዎች በጥላቻ ዓይን አይመልከቷቸው፡፡ እነርሱን ለመርዳት አያመንቱ፡፡ እናንተ ራሳችሁ ፈተናን ለመቋቋም ያላችሁ ኃይል በጣም የተዳከመ መሆኑን አትዘንጉ:: ሌሎች ሊታገሥአችሁ እንደምትፈልጉት እናንተም ወጣቶችን ታገሠ:፣ ማንም ብርቱ ቢሆን እግዚአብሔር ሲፈጥረው:፡ እርዳታ የሚያሻው አድርጎ ነው ታዲያ ልጆች እንዴት የበለጠ ዕርዳታና ድጋፍ ያስፈልጋቸው ይሆን? የደከመውንና የተፈተነውን ልጅ እንኳን የፍቅር አስተያየት ብርታት ይሰጠዋል፡፡ የሱስ ማንኛውንም ወጣት «ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ” (ምሳሌ 23:26) ይለዋል፡፡ ‹ከዳተኛች ልጆች ሆይ ተመለሱ፣ ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ» ይላል (ኤር 3:22):GWAmh 131.2

    የክርስቶስ ፍቅር የማይሰማው ወጣት ፍጹም ደስታ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ከመንገድ የራቁትን ሲመለሱ ለመቀበልና ነዛዜአቸውን ለማዳመጥ የሱስ በደግነት ይጠባበቃል፡፡ እናት ክልጅዋ (ከሐዘኗ) የፍቅር ፈገግታ አንደምትጠባበቅ እርሱም ከወጣቶች የምሥጋና ቃላትን ለመስማት : ታላቁ አምላካችን አባታችን ብለን እንድንጠራው መብትና ሥልጣን ሰጥቶናል፡፡ በችግራችንና በፈተናችን ጊዜ ልቡ አንደማይዘነጋን አንድናውቅ ይፈልጋል፡፡ «አባች ለልጆቹ አንዲራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፡፡» (መዝ. 103፡13) እግዚአብሔር የሚፈልገውንና የሚጠማጠመውን ነፍስ ከሚረሳ አናት ልጅዋን ብትረሳ ይቀላል፡፡GWAmh 132.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents