Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስለ ጸሎት ሊኖረን የሚገባ አስተያየት

    በግልም ሆነ በጉባዔ ጸሎት በአምላካችን ፊት ተንበርክክን ፍላጐታችን የመናገር መብት አለን:: የሱስ ምሣሌያችን «ተንበርክኮ ጸለየ” (ሉቃስ 22፡41) ደቀመዛመሙርት ፊት «ተንበርክከው ጸልየዋል” (የሐ. 8፡40፤20፣፤ 36፤21፣5፣ ኤፌ 3፡14) ጳውሎስም ተንበርክኮ መጸለዩን ይናገራል፡፡ የእሥራኤሎችን ኃጢያት ለመናዘዝ «አዝራ ተንበረከከ» (እዝ. 9:5): «ዳንኤልም በቀን ሶስት ጊዜ እየተንበረከከ ለፈጣሪው ምሥጋናና ጸሎት ያደርስ ነበር፡፡” (ዳንኤል 6፡10)GWAmh 111.1

    ለእግዚአብሔር ተገቢውን አክብሮት የምንሰጠው በአጠገባችን መገኘቱንና ታላቅነቱን ስንገነዘብ ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው አምላክን በልቡ ማክበር አለበት፡፡ እግዚአብሔር ስለሚገኝበት የጸሎት ቦታ ቅዱስ ነው፡፡ የአክብሮት ስሜት ያደረበት ሰው መንፈሱ ይነቃቃል፡፡ ባለመዝሙሩ «ስሙ ክቡርና ቅዱስ ነው» (መዝሙር 111:9) ይላል፡፡ መልአክት ስሙን ሲጠሩ ፊታቸውን ይሸፍናሉ:: ታዲያ እኛ ኃጢዓተኞችና የወደቅን እንዴት ስሙን በበሰጠ ልናክብረው ይገባናል?GWAmh 111.2

    እግዚአብሔር የሚገኝበትን ቦታ ቅዱስነት በመጽሐፍ ቅዱስ አስረጀነት ለአዋቂዎችና ለልጆች ማስረዳት ተገቢ ነው፡፡ «አትቅረብ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከአግርህ አውጣ አለው” (ዘፀዓት 3:35፤ ያዕቆብ የመሰላሉን ራዕይ ባየ ጊዜ «በዕውነት እግዚአብሔር በዚህ አለ፣ እኔ አላየትሁም ነበር : የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ይህም የሰማይ ደጅ ነው፡፡› (14ጥረት 28፤ 16:17):GWAmh 111.3

    «እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፡፡ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል” አንደ ድርሰት በቃል የተጠና ጸሎት አስፈሳጊነቱ ትንሽ ነው:: አጭር የሃይማኖት ጸሎት የሰዎች ልብ ያርሳል፡፡ ረዥም ጸሎት ግን ሰሚዎችን ያሰለቻል፡፡ ወንጌላዊው በጉባዔ ከመጸለዩ በፊት በግል ክፍሉን ዘግቶ ከፈጣሪ በረከት መቀበል አለበት፡፡ ይህን ካደረገ ለራሱም ለሕዝቡም መልካም በረከት ያገኛል፡፡GWAmh 111.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents