Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወጣቱ ወንጌላዊ

    ወጣቶች የክርስቶስ ተባባሪዎች ሆነው ለወንጌሉ ሥራ መሰለፍ አለባቸው፡፡ «እነርሱም ደግና” በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ፡፡» ራሳቸውን ለክርስቶስ ቢያስረክቡ ነፍሳትን ለማዳን መሣሪያ ያደርጋቸዋል፡፡ ለወንጌል አገልግሎት የተጠራ ወጣት ጥሪውን ከፍ አድርጐ በመገመት ጊዜውን፣ ጉልበቱን፣ ጥረቱን ለዚህ ቅዱስ ሥራ ለማዋል ይወስን፡፡GWAmh 63.5

    የቀደሙት ሲያልፉ ሥራው አንዳይታጐል ወጣቶች ክፍት በሚሆነው የሥራ ቦታ ለመተካት ይዘጋጁ:: ብርቱ ጦርነት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ወጣትነትና ብርታት ያላቸው ሰዎች የጥፋት ጥላ ያጠላባቸውን ነፍሳት ከጨለማወው ዓለም ማውጣት አለባቸው፡፡GWAmh 64.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents