Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለወንጌላዊነት ምርጫ የሚደረግ ምርምር

    እግዚአብሔር ለሥራው አንደጠራቸው ሳይረጋገጥ ሰዎች ወንጌላዌያን እንዲሆነ መገፋፋት አይገባቸውም፡፡ ሰዎች ብቁ ካልሆነ እግዚአብሔር ሥራውን በአደራነት አይሰጥም፡፡ እግዚአብሔር ለሥራው የሚያሰልፋቸው ሰዎች ጥልቅ የክርስትና ስሜት ያላቸው፤ የተፈተኑና የተመረመሩ፤ የማመዛዘን ችሎታ ያላቸው፣፤ ኃጢዓትን በትህትና ሊገስጹ የሚችሉ፣ መንጋውን መመገብ የሚሜችሉትን ነው፡፡ አግዚቢአብሔር ልብን ስለሚያውቅ የሚመርጠውንም ያውቃል፡፡ ወንጌላዊያንን ለመምረጥ በቂ ምርምር ስሳልተደረገ ቤተ ክርስቲያን በሙሉ ልባቸው ያልተመሰሱ፤ ሠርተው የማያጠግቡ፤ ክርስቲያናትን በማነቃቃት ፋንታ እንዲተኙ ምክንያት የሆነ. ሠራተኞችን ለእግዚአብሔር ሥራ አሳልፋለች። ወደ ጸሎት ቤት ሲመጡ ያንኑነ የተለመደ ጸሎት እየደጋገሙ የሚጸልዩ ብዙ ወንጌላዊያን ከሳምንተ ወደ ሳምንት ከወር ወወደ ወጠር ያንነኩ ደረቅ ስብከታቸውን በመደጋገም ይሰብካሉ፡፡ ከመለኮታዊ ጸጋ ተካፋይነት ስለ ሌላቸው ለጉባዔው የሚያሰሙት አዲስ ትምህርት አልተቀበሉም፡፡ ክርስቶስ በሃይማኖት አማካይነት በልባቸው ውስጥ አይገኝም፡፡ የእግዚብሔርን ሕግ አያስተማሩ የማይጠብቁ ሰዎች ላመኑም ላላመነም አንቅፋት ናቸው፡፡GWAmh 292.1

    የእግዚአብሔርን ሕግና የየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕትነት በቀሳሱ መመልክት አግዚአብጨጤርን አንደመስደብ ይቆጠራል፡፡ ይህን የተስፋፋ ክፉ ነገር ማረም የሚቻለው #ቃለ- እግዚአብሔርን ለማስተማር የሚሰለፈውን ሰው ጠንቅቆ በመመርመር ነው፡፡ ይህ ኃላፊነት የተጣለባቸው ሰዎች ሰውየው እምነት ከተቀበለ ጊዜ አንስቶ ያለውን የሕይጦት ታሪኩን ይከታተሉ፡፡ የክርስትና ሕይወቱ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ፅውቀቱ መመዘን አለበት፡፡ በእግዚአብሔር ሕግና ትፅዛዝ የጸና አቋም አንዳለው ሳይታወቅ በፊት፤ ማንም ለወንጌላዋነት አይሰለሩ፡፡GWAmh 292.2

    መጽሐፍ ቅዱስን ለዓለም ለማስተማር የሚፈልጉ ሰዎች ብቁነታቸው በሥራው ላይ ልምድ በአላቸው ዕውነተኛ ሰዎች ሳይመዘን በፊት ይህን ቅዱስ ተግባር አይጀምሩ፡፡ ትንሽ ልምድ ካገኙ ተቀባይነት ማግኘት አለማግኝግታቸው እንዲታወቅ በጸሎት አማካይነት በእግዚአብሔር ፊት ይቅረቡ፡፡ ሐዋርያው «በማንም ላይ ፈጥነህ አጆችህን አትጫን» (1ኛ ጢሞ. 5:22) ይላል። በሐዋርያት ጊዜ የእግዚአብሔርን አገልጋይ ሰመምረጥ በራሳቸው ግምት ብቻ አይተማመኑም ደህና ግምት የጣሉባቸውን ሰዎች መርጠው ያቀርቡና እግዚአብሔር ወኪሎቹ አንዲሆነ መርጧቸው እንደሆን ይጠይቁታል፡፡ አሁንም ቢሆን እንደዚሁ መደረግ አለበት፡፡GWAmh 292.3

    በብዙ ቦታዎች ብዙ ሰዎች ላልተዘጋጁበት ማዕረግ በችኮላ ይጠራሉ፡፡ ራሳቸውን አንኳን በሚገባ መግዛት አልተማሩም። ምሣሌነታቸው መልካም አይደለም፡፡ በመሪዎቹ ጉድለት ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ ከችግር አትወጣም፡ በእንደነዚህ ባሉት ሰዎች ላይ እጅ በኝሻኮላ ተጭናባቸዋል፡፡GWAmh 293.1

    የእግዚአብሔር አገልጋዮች መልካም ስም ያላቸውና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሚገባ የሚያካሂዱ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ለቅፃሙበት የሥራ ቦታ በውርደት ፋንታ ክብርን የሚያቀዳጁ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡GWAmh 293.2

    በተለይ ወንጌላውያን ለዘመኑ ሊታወጅ የሚገባውን መልዕክት ማስተዋላቸው ሊታሰብበት ይገባል፡፡ እንዲህ ከሆነ ስለትንቢቶችና ስለሌላ ተፈላጊ ትምህርቶች የተብራራ መግለጫ ሊሰጡ ይትላሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት በሚገባ ማስተማር ካልቻሉ ራሳቸው በበለጠ መማር ያስፈልጋቸዋል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ዕውነት ዘርዝረው ማስተማር አንዲችሉ በትጋትና በጸሎት አጥንተው በሚገባ ማጠዋ አለባቸው፡፡ ወደ ሥራው ቦታ ሠራተኞቹ ሳይላኩ በፊት ነገሩ በብርቱ ይታሰብበት፡፡GWAmh 293.3

    ጳውሎስ ጢሞቴዎስን የሥራውን ቅዱስነት የተገነዘበ፤ በኘግርና በስደት የማይደነግጥ፣ ለመማር ፈቃደኛ የሆነ አድርጎ ገመተው። ነገር ግን ያሳለፈውን ሕይወቱን ሳይመረምርና በጥብቅ ሳይፈትን ጢሞቲዎስን በአባቱ በኩል ግሪክ፣ በአናቱ በኩል ደግሞ አይሁድ። ከሕፃንነቱ ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስን ተምሯል፡፡ በቤቱ ውስጥ እያየ ያደገው መንፈሣዊነት የሚያስደስት ነበር፡፡GWAmh 293.4

    የአናቱና የሴት አያቱ ዕምነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም በረከት አስገንዝቦታል። እነዚህ ሁለት መንፈሳዊያት ሴቶች ጢሞቴዎስን እየመሩ ያሳደጉት በእግዚአብሔር ሕግ ነበር፡፡ ከእነርሱ ያገኘው የመንፈሳዊ ትምህርት ኃይል በአነጋገሩ ጨዋ፤ እንዲሆንና በአካባቢው ባለው ክፉ ነገር እንዳይበከል አረዳው፡፡ ስለዚህ በቤቱ ውስጥ ያሳደጉች መምህራኑ ለእግዚአብሔር ሥራ ኃላፊነት ለመሸከም ብርቱ እንዲሆን አዘጋጁት፡፡GWAmh 294.1

    ጳውሉስ የጢሞቴዎስን ታማኝነት፣ ጽ፳ጽናትና ዕውነተኛነት ተመልክቶ ለሥራ ጓደኝነት መረጠው፡፡ ጢሞቱዎስን በልጀነቱ ወራት ያስተማሩት አናቱና አያቱ የታሳቹቁ ሐዋርያ የሥራ ባልደረባ ሲሆን በማየታቸው የሥራቸውን ጥሬ ተመለከቱ፡፡GWAmh 294.2

    ጳውሎስ ጢሞቴዎስን «በሃይማኖት እንደ ልጁ» (1ኛ ጢሞ. 1፡2) አድርጎ ወደደው፡፡ ታላቁ ሐዋርያ ወጣቱን ተማሪውን ስለ መጽጠባና፡ ቅዱስ በመጠየቅና በማስተማር በመንገድ ሲጓዙ ያሠለጥነው ነበር፡፡ ጳውሎስና ሲላስ የጢሞቴዎስን አስተሳሰብ በበለጠ ለማብሰል ስለሥራው ቅዱስነትና ታላቅነት አዘውትረው ያስተምሩት ነበር፡፡GWAmh 294.3

    ጢሞቴዎስ በየጊዜው የጳውሉስን ምክር ለሥራው ይሻ ነበር፡፡ ከመንገዱ ሳይደርስ ጠለቅ አድርጎ በማሰብ በየጊዜው ትክክለኛው የእግዚአብሔር መንገድ ይህ ነው ወይ? አያለ ይጠይቅ ነበር፡፡GWAmh 294.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents