Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወጣቶች ቀንበር ሲሸከሙ

    « ብርቱዎች ስለሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል ስለሚኖር ክፉውን ስላሽነፋችሁ አጽፍላችሁአለሁ::” (፲ዮሐ. 2:14) ሥራው በአእያቅጣጫው እንዲፋጠን እግዚአብሔር የወጣቶችን ብርታት፣ ፍላጐትና ድፍረት ይፈልጋል፡ ለሠራው ግሥጋሴ ወጣቶችን መርጧል፡፡ በግልጽ ለማቀድ በድፍረትም ለመግፋት ያልዛለ ትኩስ ኃይል ያስፈልጋል፡፡GWAmh 41.1

    ባልተበላው ጉልበታቸው ሠርተው፤ ባልዛገው አዕምሮአቸው አስበው፤ ባልጐለደፈው አንደበታቸው ተናግረው ለጌታቸው ክብርን፣ ለሰዎች መዳንን አንዲያስገኙ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ታላቁን መጠራት ችላ ብለው፤ ወጣቶች ለክብርና ለምቾት መሯራራጥ የለባቸውም፡፡ የነፍሳት መዳን ሰሥራ ሊያነቃቃቸው ይገባል፡፡ ከአምላክ በተሰጣቸው ኃይል አማካይነት ባሪያ አድርጐ ከሚያሰራቸው ልምድ ነፃ መውጣት አለባቸው፡፡ በአጉል መንገድ ተራምደው ራሳቸው ጠፍተው ተከታዮቻቸውንም አንዳያጠፉ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡GWAmh 41.2

    ማንም ለራሱ ብቻ የሚኖር ቢሆን ለክፉ ምሣሌነቱ ይታያል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ወጣቶች ረጋ ያለ መንፈስ እንዲኖራቸው ይመክራቸዋል፡፡ አንዲያ ካልሆኑማ ራስን ክዶ ለመስዋዕትነት ማቅረብ በሚያስፈልገው በክርስቶስ ሥራ እንዴት ተካፋይ ሊሆኑ ይችላሉ? ለጢሞቴዎስ የተነገሩት ቃላት ለዛሬ ወጣቶችም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ «የዕውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍር ሠራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ፡፡ ከክፉ የጐልማሰነት ምኞት ግን ሽቨ› በንጹህም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ ዕምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ አጥብቀህ ተከተል፡፡» «በቃልና በኑሮ በፍቅርም በዕምነትም፣ በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሣሌ ሁን አንጅ ማንም ሕፃንነትህን አይናቀው፡፡› (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15:22፤ ፲ኛ ጢሞቴ 4:12)GWAmh 41.3

    ቀንበሩን የተሸከሙት በሞት እየተለዩን ናቸው። ሥራውን ያቋቋሙት ሥጋዊ ኃይላቸውና የአእምሮ ብርታታቸው አየተዳከመ ነው:: ዋናው ጥያቄ ማን በቦታቸው ይተካ የሚለው ነው፡፡ የቤተ-ክርስቲያኗ ተስፋ በማን ላይ ይረፍ?GWAmh 41.4

    ኃላፊነትን አንዲሸከሙ፣ በሥራው አንዲተኩ በተስፋ የምንጠባበቀው የዘመኑን ወጣቶች ነው:: እኛ ከተውንበት ሥራውን ማንሳት አለባቸው፡፡ ግብረገብ በልጽጐ ሃይማኖት እንዲጐለምስ ወይም ግብረገብ ወድቆ አለማመን አንዲነግሥ የእነርሱ ሥራ ይወስናል፡፡ ታዲያ ወጣቶችን ለኃላፊነት የሚያዘጋጁአቸውና የሚገሯቸው ታላላቆች ናቸው:: ምክንያቱም በወጣቶች ላይ የተጣለውን ክባድ ኃላፊነት መሸከም አንዲችሉ ነወ፡፡GWAmh 42.1

    ወጣቶቹ ራሳቸውን ገዝተው በንጽህና እግዚአብሔር ካቀደላቸው ሙሉ ሰውነት ሊደርሱ ይችላሉን? የክፉን ሁሉ ምንጭ ለማቋቋም ኃይል አላቸውን? ችግሩ ከዚህ ላይ ነው:: ማንም ወጣት ራሱን በተስተካከለ ጠባይ ሳይመራ ለኃላፊነት መታጨት የለበትም፡፡ እንዲህ ማድረግ ወይን፣ ከአሜካላ በለስ ለመልቀም እንደማሰብ ይቆጠራል፡፡GWAmh 42.2

    መልካም ጠባይ የሚገነባው ቀስ በቀስ ነው:፡ በወጣቱ ሰውነት ውስጥ የሚፈለጉት ጠባዮችን፤ በትጋት በመስራት፣፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ማንኛውንም መክሊት በማሻሻል፣ በበለጠም ከጥበብ ምንጭ ጋር ቀርቦ ግንኙነት በማድረግ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ወጣቶች ዝቅ ባለ በጠባይ ደረጃ በቃኝ ማለት የለባቸውም፡፡ የዮሴፍና የዳንኤል ታሪኮች ለወጣቶች ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ከሁሉም የበለጠ የመድኃኒታችን ታሪክ ፍጹም ምሣሌነታቸው አራአያ ነው፡፡GWAmh 42.3

    ሁሉም ራሱን ለማሻሻል ዕድል : ሁሉም በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የተመደበላቸውን ቦታ ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ሳሙኤል ልበ-ንጹህ ስለነበር እግዚአብሔር ከልጅነቱ ጀምሮ ለአገልጋይነት ተቀበለው/መረጠው/፡፡ ለእግዚአብሔር በሥጦታ ስም ተሰጠ፡፡ አምላክም የብርሃን መቅረዝ አድርጐ ተጠቀመብት፡፡ ወጣቶች አንደ ሳሙኤል ቢሆኑ አምላክ ይጠቀምባቸዋል፡፡GWAmh 42.4

    ስለ ሕይወታቸው ከባለመዝሙሩ ጋር እንዲህ ለማለት ይችላሉ:: «አምላኬ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኘ፡፡ እስከዛሬ ታምራትህን እነግራለሁ፡፡»GWAmh 42.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents