Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምግሣብና ጤና

    ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው በተለይ መንፈሳዊያን መሪዎች ፈጣን የማስተዋል ችሎታና ሙሉ ስሜት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ከሌሎች የበለጡ በአመጋገባቸው የመሳትን መግዛት ደንብ የተከተሉ መሆን አለባቸው:: በምግብ ገበታቸው ላይ የቅንጦትና የዘመናይ ምግብ መቅረብ የለበትም፡፡GWAmh 144.4

    በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በየቀኑ ሥራቸው ዋጋ ያለው ውጤት አንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በፍጥነት ማሰብ መቻል ይኖርባቸዋል፣ ይህን ማድረግ የሚችሉም ምግባቸው መጠነኛ ሲሆን ነው፡፡ አእምሮ የሚጎለምስ አካል ተገቢ ይዞታ ሲኖረው ነወ:፡ ቁጥጥሩ ከመጠን በላይ ካልሆነ አዲስ ኃይል ይገኛል፡፡ ታላቅ ሥራ በፊታቸው የተደቀነባቸው ሰዎች በአመጋገባቸው ጉድለት ሥራቸው ተገቢውን ቦታ ሳይዝ ሊቀር ይችላል፡፡GWAmh 145.1

    ሥርዓት የጎደለው የሆድ ዕቃ ያልተስተካከለ አስተሳሰብን ያስከትላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ብስጭትን፣ ጭካኔንና ጠማምነትን ያስከትላል፡፡ በተሳሳተ አመጋገብ በተፈጠረ መጥፎ አስተሳሰብ ምክንያት ለዓለም በረከት ሊሆን የሚችል ሥራ ተጓድሏል፡፡ ብዙ የጭካኔ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፡፡ የአእምሮ ሥራ ለሚያከናውኑ ሁሉ የሚከተለው ምክር ቀርቦላቸዋል፡፡ የግብረ-ገብ አቋማቸው የበረታና ራሳቸውን መቆጣጠር የሚችሉ ሰዎች ይሞክሩት፡፡ በአንድ የምግብ ጊዜ ከሁለት ሦስት የበለጠ ቀላል የምግብ ዓይነት አትመገብ፡፡ የምግብ ፍላጎትህ ከተገታ በኋላ አንዲሁ አትብላ፡፡ በእየቀኑ የሰውነት ማጠንከሪያ ልምምድ አድርግ፤ እነዚህን ሞክርና ውጤቱን ተመልከት፡፡GWAmh 145.2

    አንዳንድ ወንጌላዊያን የአመጋገባቸውን ሥርዓት ለመቆጣጠር አያስቡትም፡፡ በአንድ ጊዜ በብዛትና በዓይነት በጣም በርከት ያለ ምግብ ይበላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ወንጌላዊነታቸው በስም ብቻ ነው፡፡ ምግባቸውን የሚቆጣጠሩበት ደንብ ስለሌላቸው በዋናዎቹ የምግብ ጊዜአት መካከል ደረቁን ያግበሰብሳሉ፡፡GWAmh 145.3

    በአመጋገባቸው ጉድለት አስተሳሰባቸው ይቀንሳል፤ ስሜታቸው ሽባ ይሆናል፣ አንቅልፍ እንቅልፍ ይላቸዋል፡፡ እነዚህ በአመጋገብ ጉድለታቸው ተጎድተው ፊታቸው የገረጣ አና የምግብ ፍሳጎታቸውን ሊገቱ ያልቻሉ ወንጌላዊያን ለጤና አጠባበቅ ምሣሌነታቸው አደገኛ ነው፡፡GWAmh 145.4

    አንዳንድ ጊዜ ሥራ ሲበዛ በቀን አንድ የምግብ ጊዜ መተው መልካም ነው:፥ የጤናን አጠባበቅ ለማስተማር ከስብከተ ይልቅ ሠርቶ ማሳየቱ ይበልጣል፡፡ ወዳጆቻቸው ከእምነታቸው ውጭ የሆነ ምግብ ሲያቀርቡላቸው ዝም ብለው በይሉኝታ የሚመገቡ ሰዎች አሉ: ነገር ግን በዚህ ፈንታ ቅመማ ቅመም የበዛበት ምግብ፣ ሻይንና ቡናን የመሰሉ መስተንግዶዎች ሲቀርቡላቸው አለመፍቀዳቸውን ቢያሳዩ ምሣሌ ሆኑ ማለት ነው::GWAmh 145.5

    ለምግብ መስገብገብና ከሚፈለገው በላይ መብላት የአእምሮን የማሰብ ችሎታ ይቀንሳል፤ መንፈሣዊ ስሜትንም ያደንዛል፡፡ የሰውነት ማጠንከሪያ ልምምድ ስለማያደርጉና የአመጋገብ ሥኑሥረዓት ስለሚጎድላቸው አንዳንድ ወንጌላዊያን የአእምሮ ችሎታቸውና የግብረገብ ይዞታቸው ተጎሳቁሏል፡፡ ብዙ ለመብላት የሚፈልጉ ሰዎች ፍላጎታቸውን መግታት እንጂ ያማራቸውን ሁሉ በልተው አካላቸውን እና፣ አእምሮአቸውን ማስነፍ የለባቸውም፡፡GWAmh 146.1

    ከመጠን በላይ መብላት ጠቅላላውን የሰውነት ኃይል ምግብን አንዲያደቅ ወደ ሆድ አካባቢ በመውሰድ ሰዉየውን ደካማ ያደርጋል፡፡GWAmh 146.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents