Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በጸሎት ጊዜ አክብሮት

    አንዳንዶች ለሰው እንደሚናገሩ አድርገው ወደ እግዚአብሔር መጸለያቸውን እንደትህትና ይቆጥሩታል፡፡ ያለጥንቃቄ ‹ኃያል እግዚአብሔር ሆይ!» በማለት ስሙን ያረክሱታል፡፡ ይህ ቅዱስ አጠራር በአክብሮትና በጥንቃቄ ካልሆነ በቀር በሰዎች አፍ ሊነገር አይገባውም::GWAmh 110.1

    የንግግር ማማር ለቤተሰብ ሆነ ለቤተክርስቲያን ጸሎት ተፈላጊነቱ አጭር ነው:: በተለይ በጉባዔ ጸሎት ተሳታፊዎቹ አስተውለውት በልመናው እንዲተባበሩ በቀላል አነጋገር መጸለይ ይገባዋል፡፡GWAmh 110.2

    በሰማይ ተሰሚነት አግኝቶ መልስ የሚቀበል ጸሎት ከልብ የመነጨና በሃይማኖት የተጸለየ ጸሎት ብቻ ነው:: እግዚአብሔር የሰዎችን ፍላጐት ያውቃል፡፡ ሳንጠይቀው በፊት የምንመኘውን ያውቃል፡፡ ከጥርጥርና ከፈተና ጋር ያለውን የነፍስ ትግል ያያል፡፡ የጸሎት አቅራቢውን እውነተኛነት ይመረምራል፡፡ የነፍስን ትህትና ይቀበላል፡፡ «ወደዚህ - ወደትሁት፣ መንፈሱም ተሰበረ፡ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው አመለከታለሁ፡፡”GWAmh 110.3

    በመንፈስ ተነቃቅተን በሃይማኖት የመጸለይ መብት አለን፡፡ በጉባዔው ያሉ ሁሉ ዕምነታችን አንደሚረዱ አድርገን በሃይማኖት ስንጸልይ ተስፋው አንደሚፈጸምልን ማረጋገጣችንን ማሳየት አለብን፡፡ የእግዚአብሔርን በቦታው መገኘት ያምኑበትና በረከቱን ለመቀበል ልባቸውን ይሰጡታል፡፡ በቁም ነገረኛነታችን እምነታቸው ያድርጋሉ፡፡ የሚነገረውን ትምህርት በብሩህ ሕሊና ይቀበላሉ፡፡GWAmh 110.4

    ጸሎታችን በፍቅር የተሞላ መሆን አለበት:: የመድኃኒታችን ፍቅር በበለጠ ለማወቅ እግዚአብሔር ጥበብ እንዲሰጠን እንለምነዋለን፡፡ ልብን የሚያነሳሳ ጸሎትና አገልግሎት (ስብከት) በአሁኑ ዘመን በጣም ያስፈልጋል፡፡ ፍጻሜው ተቃርቧል፡፡ አምላክን በፍጹም ልቦና የመሻት አስፈላጊነቱ ቢታየን እንዴት በተጠቀምን? በኋላ ልናገኘው እንችል እግዚአብሔር ራሱ ሕዝቡን እንዴት አንደሚጸልዩ ያስተምራቸው፡፡ የትምህርት ቤታችን መምህራን፣ የቤተ ክርስቲያናችን ወንጌላዊያን በክርስቶስ ትምህርት ቤት ይማሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ዕውነተኛ ጸሎት ጸልየው መልስ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ቃሉን በመሉ ኃይል ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡GWAmh 110.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents