Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሕክምና ሚሲዮናዊነት ሥራ በከተማዎች

    የህክምና መልዕክች ሥራ በብስለትና በአዋቂነት መካሄድ አለበት፡፡ የተቀደሰው የነፍሳትን ማዳን ሥራ በትህትናና በትጋተ መሠራት አለበት፡፡ ታዲያ ሠራተኞቹ አነማን ናቸው? ከልባቸው የተሠለሱ፣ የዕውነቱ ብርሃን ወለል ብሎ የተገለጠላቸው ሰዎች የሥራው መሪ ይሁነ፡፡ ለሥራው ሰዎች ሲመረጡ በጥንቃቄና በጥልቅ አመዛዛኝነት ይመረጡ፡፡ እግዚአብሔርን የሚወዱና በፊቱ በትህትና የሚራመዱ፤ የሰውን ዘር ለማዳንና ከፍ ለማድረግ ለእግዚአብሔር መሣሪያ መሆን የሚችሉ ሰዎች ይሁኑ፡፡GWAmh 236.1

    የሕክምና መልዕክትኞች ለአዲስ ሥራ ቆርቋሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የወንጌላዊ ሥራ በሐኪም ዕርዳታ መደገና: ይገባዋል፡፡ ክርስቲያን ሐኪም ሞያውን አንደ ወንጌላዊነት ሊቆጥረው ይገባል፡፡ የወንጌላዊና የሀኪምን ሥራ አጠቃልሎ በመያዙ ኃላፊነቱ አጽፍ ድርብ ነው፡፡ ሞያው የተቀደሰ፣ የተክበረና ተፈላጊ ነው፡፡ ወንጌላዊና ሐኪም የሥራቸውን ተመሳሳይነት ተገንዝበው መስማማት፣ መመካከርና መረዳዳት ይገባቸዋል፡፡ በሀብረት ከሠሩ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ወደዚት ምድር መጥቶ መሞቱን ለሰዎች በግልጽ ያስተምራሉ፡፡GWAmh 236.2

    ከተራ ሀኪሞች ኘፕሎታቸው በለጥ ብሎ የሜገኝ ሀኪሞች በከተማ ውስጥ ቢሠሩ መልካም ነው፡፡ ከፍተኛ ሰዎችን ሊገናኙ ይትላሉ፡፡ የአነቢህን ሀኪሞች አገልግሎት ለድሆች ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ በነሮአቸው ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ሰዎች በወንጌል በኩል ቀራቢ አላገኙም፡፡ የወንጌል መልዕክት ለሁሉም ስለሆነ ከሀብታሞች መካከል መልዕክቱን የሚቀበሉ አይታጡም፡፡ በዙ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሲመለሱ ሥራውን በቀራጥነት ያካኒዱታል፡፡GWAmh 236.3

    በኋላፊነት የተቀመጡትን፣ የማስተዋል ችሎታ ያላቸውን እግዚአብሔር መክሊታቸውን ለመልካም ሥራ እንዲያውሱት . ይፈልጋል፡፡ ሠራተኛቻችን እነኪህን ሰዎች ሲያስተምሩ የሥራችን አቋም በግልጽ መናገር አለባቸው፡፡ ሥራውን ለማካሄድና ድሆችን ለመርዳት ምን እንደሚያስፈልገን ሳይሰሰጉ ይንገሩአቸው፡፡ ያን ጊዜ ሥራቸው መሠረቱ ይጸናል፡፡ አንዳንዶቹ በመንፈስ ቅዱስ ይነኩና የጌታን ሥራ ለመርዳት ይነሱ ይሆናል፡፡ በታላላቅ ከተማዎች አማካይ ቦታ ያቋቁሙሙና የጌታን ፈቃድ ይፈጽማሉ፡ ለሥራው ናፍቆት ያደረባቸው ወንጌላዊያን በልዩ ልዩ የሥራ መስመር ይሰለፋሉ፡፡GWAmh 236.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents