Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወንጌላዊ በቤቱ ውስጥ

    የእግዚአብሔር ፍላጎት መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምር መምህር በቤቱ ውስጥ መልካም ምሣሌነት አንዲያሳይ ነው፡፡ የአንድ ሰው ሥራው ከንግግሩ ይልቅ አብነት (ምሣሌነት) አለው፡፡ በየዕለቱ የሚታየው መንፈሣዊነት በሕዝብ ላይ ምሣሌነት አለው፡፡GWAmh 127.5

    ትዕግስት፣ ሙሉነትና ፍቅር በስብከት የማይነሳሳውን መልካም ስሜት ያነሳሳሉ፡፡ የወንጌላዊ ግዳጅ ቦታና ጊዜ ሳይመርጥ በቅርብም በሩቅም ነው፡፡ ግን የመጀመሪያ ግዳጆቹ ልጆቹ ናቸው፡፡ በውጭ ሥራ በዛብኝ ብሎ ልጆቹን ማስተማር ችላ ማለት የለበትም፡፡ የቤቱን ተግባር እንደቀላል ይመለከተው ይሆናል፤ ነገር ግን ለሕበረተሰቡ ደህንነት መሰረቱ ቤተሰብ ነው:: አብዛኛውን ጊዜ የሰዎች ደስታና የቤተ ክርስቲያን ዕድገት የሚወሰነው በእያንዳንዱ የቤተሰብ ይዞታ : ዘለዓለማዊ ወይም ዘላቂ የሕይወት አመራር በእየቀኑ የአኗኗርን ዘዴ ይወስናል፡፡ ዓለም ከታላላቅ ፈላስፋዎች ይልቅ በየቤቱ መልካም አራአያነት የሚያሳዩ ደጋግ ሰዎች ያስፈልጉታል፡፡GWAmh 127.6

    ለውጭ ብሎ የውስጡን የዘነጋ ወንጌላዊ ምንም ዓይነት ምክንያት ሊያቀርብ አይችልም፡፡ በመጀመሪያ የቤተሰቡን መንፈሣዊ ጤንነት መቆጣጠር አለበት:: በመጨረሻ የፍርድ ቀን በሥልጣኑ ሥር የተሰጡትን ሰዎች እንዴት እንዳስተዳደራቸው ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡ ለሌሎች የፈጸመው መልካም ሥራ ለቤተሰቡ ያለበትን ዕዳ ሊሠርዝለት አይችልም፡፡ በግብር በሚገለጥ አገልግሎት ወንጌልን ለሌሎች የሚያስተምር ህብረት በወንጌላዊ ቤት መታየት አለበት: ወንጌላዊውና ባለቤቱ በመቆጣጠር፤ በመማረም፤ በመምከር፣ በመምራት፤ በቤታቸው ውስጥ ቅን ሥራ ሲያካሂዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመሥራት ተገቢዎች ይሆናሉ፡፡ በዚህ ምሣሌነታቸው የቤተ ክርስቲያንን ሠራተኞች ያበራክታሉ፡፡ የቤተሰብ አባሎች ለከፍተኛው የቤተሰብ አባሎች ምሳሌ ይሆናሉ፡፡ ታላቅ ምሣሌነትን በማሳየት መልካም ለመሥራት ተጨማሪ ኃይል ይሆናሉ፡፡GWAmh 128.1

    ልጆቹን ስድ ሰዶ እንደፈለጉ የሚተዋቸው ወንጌላዊ በልጆቹ ምክንያት በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ተሰሚነቱ ይቀንሳል፡፡ ቤተሰቡን በሚገባ የማያስተዳድር ወንጌላዊ በቤተክርስቲያን ተገቢ አገልግሎት ሰጥቶ ከክርክርና ከጭቅጭቅ ሊያድናት አይችልም፡፡GWAmh 128.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents