Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የቅዱስ ዕቃዎች ደንብ

    የወንጌል ነቃፊዎች በአሁኑ ዘመን በርክተዋል፡፡ የክፉ ኃይል አንደ ዘመናችን ሆኖ ተባብሮ አያውቅም፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ ለማፍረስ ሰይጣንና ሰው ተባብረዋል፡፡ ልምድና ሀሰት ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ልቀዋል፡፡ ከራዕይ ይልቅ ምርምርና ሳይንስ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡ የሰዎች ችሎታ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይልቅ ታምናበታል፡፡ ከአምልኮ ይልቅ ወግና ልምድ በርትቷል፡፡ አለማመን ተለምዲል፡፡ ታስበው የሚሠሩ ኃጢዓቶች ሰውን ከአምላክ ለይተውታል፡፡ የብቡዎቹ አነጋገር «የዚህን ሰው መሪነት አንፈልግም» የሚል ሆኖአል፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ድምፃቸውን አንደመለከት ድምጽ ከሩ አድርገው በማንሳት የሕዝቡን አመፀኛነት ማስታወስ አለባቸው:: በተለምዶ የሚሰጡት ቀዝቀዝ ያሉ አገልግሉቶች ወጤታቸው ቀላል ነው:: የእግዚአብሔር ቃል በሚገባ ስላልተነገረ ወደ ሰዎች ልብ ሠርፆ አልገባም::GWAmh 91.5

    ዕውነቱን ተክትለናል የሚሉ አንዳንድ ሰዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይጠይቃሉ፡፡ ዕውነቱን በግልጽ መናገር ምን ይጠቅማል? ዮሐንስ ለፈሪሣዊያን «እናንት የዕባብ ልጆች ከሚመጣው መቅሰፍት አንድትጠነቀቁ ማን አመለከታችሁ” ማለት ያስፈልገው ነበር እንዴ? ሄሮድስን ከስህተቱ ስለገሠጸው ከሞት በቀር ምን አተረፈ? የሄሮድስን ቁጣ ሳያስነሳ አንዲሁ ቢኖር ምን ይመጣበት ነበር?GWAmh 92.1

    ሰዎች በታማኝነት ፋንታ የራሳቸውን ደንብ እስከ ማቋቋም ድረስ ተከራክረዋል፡፡ ኃጢዓት ተቃውሞ ሳይኖረው ባንናአል፡፡GWAmh 92.2

    በቤተከርስቲያን ወስጥ ‹ያ ሰው አንተ ነህ» የሚል ታማኝ ድምጽ የሚሰማ መቼ ይሆን? እነዚህ ቃላት ተደጋግመው ቢነገሩ ኖሮ የእግዚአብሔር ኃይል በበለጠ ሲሠራ በታየ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ሠራተኛች ኃጢዓትን በስሙ እስከጠሩ፤ ሰዎችን ለማስደሰት ብቻ መልካም ቃላት አየመረጡ መናገርን እስከተው አና እግዚአብሔር ሰላም ነው ሳይል ሰላም አንደሰፈነ አስመስለው መደለል እስካቆሙ ድረስ ሥራችን ውጤት አጣ ብለው ማገረምረም የለባቸውም፡፡GWAmh 92.3

    እያንዳንዱ ወንጌላዊ የእግዚአብሔርን ቅዱስነትና የሥራውን ታላቅነት ቢገነዘብ ጠቃሚ ነው:: ወንጌላዊያን በመለኮት ሥልጣን የተሾሙ ከባድ ኃላፊነት የተጣለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ታዛዦችን እያበረታቱ፤ የማይታዘዙትን እያስጠነቀቁ በክርስቶስ ፋንታ ሆነው የሰማይን ሚሥጥር የሚገልጡ መጋቢዎች ናቸው፡፡ ዓለማዊ ደንብ በሥራቸው ላይ ኃይል ሊኖረው አይገባም:: እግዚአብሔር ይራመዱበት ዘንድ ከጠረገላቸው ጐዳና ዝንፍ ማለት አይገባቸውም፡፡ ምስክሮች እንደ ደመና እንደ ከበቧቸው አምነው (ተገንዝበው) በሃይማኖት መገሥገሥ አለባቸው፡፡ የራሳቸውን ቃልና ሀሳብ ሳይሆን ከላይ እንዲናገሩ የታዘዙትን መናገር አለባቸው፡፡ መልዕክታቸው «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” መሆን አለበት፡፡GWAmh 92.4

    እግዚአብሔር፡- ያለፍርሃት፣ የመጣ ቢመጣ ሳያመነቱ፣ ቢያስፈልግም ያላቸውን ሁሉ ለመስዋዕትነት አቅርበው መልዕክቱን የሚያደርሱ እንደ ናታን፤ ኤልያስና ዮሐንስ ያሉ መልዕክተኞች ያስፈልጉታል፡፡ (2ኛ ሳሙኤል 12፡7 ተመልከት)GWAmh 92.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents