Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገዛት

    ስለ በሽተኞች ስንጸልይ «አንደሚገባን መጸለይ አንደማንችል” (ሮሜ 8፡ 26) መዘንጋት የለበትም:: የምንጠይቀው ጥያቄ ይጎዳን፣ ይጥቀመን አናውቅም፡፡ ስለዚህ በምንጸልይበት ጊዜ «ጌታ ሆይ የእያንዳንዱን ሰው ምሥጢር ታውቃለህ፤ እነዚህን ሰዎች በሚገባ ታውቃቸዋለህ፤ የሱስ አማላጃቸው ሕይወቱን ለውጦላቸዋል፡፡ ከምንወዳቸው በጣም አብልጦ ይወዳቸዋል፡፡ መዳናቸው አንተን የሚያስከብርና የሚጠቀም በየሱስ ክርስቶስ ስም እንድትምራቸው አለምንህአለን:: መዳናቸውን የማትፈቅድ ከሆንህ ግን ፀጋህና ኃይልህ ችግራቸውን ያስችላቸው፡፡› ማለት መልካም ነዉ፡፡GWAmh 137.2

    እግዚአብሔር ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የሚሆነውን ያውቃል፡፡ የእያንዳንዱን ሰው ሀሳብ ይመረምራል፡፡ የሚጸለይላቸው ሰዎች በሕይወት መኖር ቢቀጥሉ የሚደርስባቸውን ፈተና መቋቋም መቻል አለመቻላቸውን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ኑሮአቸው ለዓለምና ለራሳቸው መርገም ወይም በረከት ሊሆን መቻሉን ለይቶ ያውቃል፡፡ ስለዚህ በምንጸልይበት ጊዜ «ፈቃድህ እንጂ ፈቃዴ ይሁን አልልም» ማለት ይገባናል፡፡ የሱስ በጌተሰማኔ ሲጨነቅ «ይህች ጽዋ፣ አባት ሆይ ከእኔ ትለፍ»›” (ሉቃስ 22:42 ማቴ. 26፡39) ሲል ከላይ የተጠቀሰውን ሐረግ በጸሎቱ ላይ ጨምሮአል፡፡ የዚህን ዓይነት ጸሎት ክርስቶስ ከፀለየ እኛማ ሟቾቹ በበለጠ ያስፈልገናል፡፡GWAmh 137.3

    ዋናው ተግባራችን ራሳችን ለጌታ አደራ ሰጥተን ካስገዛን በኋላ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ማመን : እግዚአብሔርን እንደ ፈቃዱ ከጠየቀነው አንደሚሰማን እናውቃለን፡፡ ለእግዚአብሔር ሳንታዘዝ ልመና መደርደር የቀና አይደለም፡፡ ጸሎታችን ትዕዛዛዊ ሳይሆን በአክብሮት የተሞላ ጥያቄ ሊሆን ይገባል፡፡GWAmh 137.4

    እግዚአብሔር የታመሙትን በመለኮታዊ ኃይሉ የሚፈውስበት ጊዜ አለ፤ ነገር ግን የታመመ ሁሉ ይድናል ማለት አይደለም፡፡ ብዙዎች በጌታ ያንቀላፋሉ፡፡ ዮሐንስ በጳጥሞስ ደሴት ሆኖ እንዲህ ብሎ አንዲጽፍ ታዝዟል፡፡ «ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን መንፈስ፡ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸው ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ፡፡› ይህ አባባል የሚያስረዳን ታመው ያልዳኑትን ሰዎች ሃይማኖት አንደ ጎደላቸው እንዳንቆጥር ነው::GWAmh 137.5

    ሁላችንም ጸሎታችን በፍጥነት አንዲመለስልን ስለምንፈልግ የዘገየብን ወይም ያልተመለሰልን ሲመስለን ተስፋ አንቆርጣለን፡፡ ግን ጥበበኛው እግዚአብሔር ለጸሉታችን መልስ በፈለግነው ጊዜና አንደፈለግነው አድርጎ ለመመለስ አይፈቅድም፡፡ በጥበቡና በአምላክነቱ ከተማመንንበት ፈቃዳችን አንዲያሟላልን ከመጠየቅ ይልቅ ፈቃዱን ለማድረግ መጣጣር አለብን:: ምኞታችንና ፍላጎታችን በእርሱ ፈቃድ ሥር መሆን አለባቸው፡፡GWAmh 138.1

    አምነትን የሚፈትኑ እንዲህ ያሱ ልምምዶች ይጠቅሙናል፡፡ በዚህ መንገድ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ የቆመ መሆኑ፣ ወይም ከጊዜ ሁኔታዎች ጋር የሚወዛወዝ ያልጸና መሆኑ ይለይለታል፡፡ ሃይማኖት የሚጠነክር ሲሠሩበት ነው፡፡ በትዕግስት ጌታን የሚጠባበቁ ዋጋ አንደሚያገኙ በመገንዘብ ትዕግስትን መማር አለብን፡፡GWAmh 138.2

    ግን ይህን ሥርዓት የሚያስተውሉት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ወዲያው እንደጸለዩ ጌታ የምህረት ዘይቱን ካልቀባቸው ሃይማኖታቸው ጉድለት ያለበት መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ ስለዚህ በሕመም የተያዙ ሰዎች የተፈጥሮን ልምድ እንዲገነዘቡ በብልሃት መመከር አለባቸው፡፡ የሚጠነቀቁላቸውንና አብረዋቸው የሚልፉትን ግዳጅ ችላ ማለት የለባቸውም፡፡ ደግሞ ጤናቸውን ለማግኘት የተፈጥሮን ሕግ ከመከታተል አይቦዝኑ፡፡GWAmh 138.3

    እዚህ ላይ ትልቅ ስህተት አለ፡፡ በጸሎት እንፈወሳለን ብሰው በማመን አንዳንዶች ሃይማኖት ጉድለት ይመስልብናል በማለት ተፈላጊውን ዝግጅት አያደርጉም፡፡ ምናልባት ከወዳጆቻቸው ቢለዩ የሚናገሩት የመሰናበቻ ንግግር ማዘጋጀትን ይፈራሉ፡፡GWAmh 138.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents