Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ግልጽ አነጋገር

    ስትናገሩ የዐረፍተ ነገሩ ቃላት በሙሉ መሰማት አለባቸው፡፡ አንዳንዶቹ ሲናገሩ ከዐረፍተ-ነገሩ ወደ መጨረሻ ያሉት ቃላቶቻቸው አይሰሙም፡፡ ስለዚህ የሀሳቡ ትርጉም አይጨበጥም፡፡ የቃላት አገልግሎት የሚጠቅመው ቃላቱ በግልጽ ሲነገሩ ብቻ ነው::: አዋቂነታችሁን ለማሳወቅ የቃላትን መሣሪያነት መጠቀም ይቅርባችሁ፡፡ ቀላል ቃላት ስትናገሩ ሰዎች ያስተውሉአችኃል፡፡GWAmh 54.3

    ወጣቶች፣ እግዚአብሔርን ለማገልገል በልባችሁ ውስጥ ምኛት አለ ወይ? እንዲህ ከሆነ ለሌሎች ቃለ-እግዚአብሔርን ለማዳረስ አንድትችሉ የአነጋገር ችሎታችሁን አሻሽሉ፡፡ ፀሎታችሁ ተርጓሚ. እስከሚያስፈልገው ድረስ አታልጐምጉሙ:: በግልጽ፤ ቃል ለመምረጥ ሳትጨነቁ ጸልዩ፡፡ ድምጽን ዝቅ አድርጐ አንዳይሰማ ማድረግ የትህትና ምልክት አይደለም፡፡GWAmh 54.4

    የወንጌልን አገልግሎት ሥራቸው ለማድረግ ለጠሰኑ ሰዎች ንግግራችሁን ለማሻሻል ታገሱ እላለሁ፡፡ ይህን ታላቅ ተግባር ለመፈጸም ትችሉ ዘንድ አምላክን ለምኑ፡፡ በጉባዔ መካከል ስትጸልዩ እግዚአብሔርን መጥራታችሁን አትርሱ፡፡ ሰዎቹ ከእናንተ ጋር አምላካቸው ልባቸውን ሊያነሱ የሚችሉት የምትናገሩትን መስማት ሲችሉ ነው፡- በችካላ የሚዣዥጐድጐድ ጸሎት ለእግዚአብሔር ክብር ካለመሆኑ በላይ ለሰዎችም አይጠቅምም፡፡ ወንጌላዊያን ቢሆኑ ወይም ማንኛውም በጉባዔ የሚጸልይ ሰው የሚያሳርገው ጸሉት ለአምላኩ ክብር፣ ለሕዝቡ ጥቅም እንዲያስገኝ ያስብበት፡፡GWAmh 55.1

    የሚሰሙት ሰዎች «አሜን» ለማለት ይችሉ ዘንድ በዝግታና ሙኸ ብለው ይጸልዩ፡፡ አንዳንድ ችሎታ ያላቸው ወንጌላዊያን ከድምፃቸው መኮሰስ የተነሳ ራሳቸውን ይጐዳሉ:: የእግዚአብሔርን ሕግ ለሰዎች ሲያስተምሩ ራሳቸው ሕጉን መጣስ የለባቸውም፡፡ ወንጌላዊያን ቀጥ ብለው ቆመው በደንብ አየተነፈሱ መናገር አለባቸው:: ይህን ቀላል ሕግ ቢከተሱ መልካም አገልግሎት በተሳካ ሁኔታ ሊያበረክቱ ይችላሉ፡፡GWAmh 55.2

    ወንጌላዊያን ትክክለኛውን የጤና ሕግ ካልተከተሉ ሕይወታቸው ከአደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ሰዎችም «ለእውነት ሲያገለግሉ አንደሞቱ ሰማዕት» ይቆጥራቸዋል፡፡ ግን አንደ እውነቱ ከሆነ ሕግን በመተላለፍ አንደሞቱ ይቆጠራል፡፡ እግዚኣብሔር ኖረው ቢያገለግሉት ይወድ ግን ሳያውቁት ራሳቸውን ይገድላሉ፡፡GWAmh 55.3

    የአቀራረብ ዘዴዎች የወንጌልን ተቀባይነት ይወሰናሉ፡፡ ለዚህ ታላቅ ዓላማ የተሰለፉ ሰዎች በነገሩ በርትተው ጉድለታቸውን ማስወገድ አንጂ ጉድለታቸው በሚያስከትለው ውጤት ተስፋ ቆርጠው ከዕውነት መራቅ የለባቸውም፡፡ ወንጌላዊያንና መምህራን ራሳቸውን አሠልጥነው ከልሳናቸው የሚወጣውን እያንዳንዱን ቃል ግልጽ ማድረግ አለባቸው፡፡GWAmh 55.4

    ጉሮሮአቸውን አንቀው፣ አፍንጫቸውን በጥድፊያ ቃል በቃል ላይ የሚናገሩ ሰዎች ከተናገሩት ግማሹ ሳይስተዋል በከንቱ ይቀራሉ፡፡ አጅ አግሩን አያወራጨ፤ አየተንቀቁራጠጠ የሚናገር ወንጌላዊ ለሥራው ትጋትና ንቃት አለው ማለት አይቻልም፡፡ «ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና» (15 ጢሞ. 4:8) ይላል ጳውሎስ፡፡GWAmh 55.5

    የዓለምን አዳኝ የሚወክል የወንጌል አገልጋይ ነው፡፡ አምላኩን በሚገባ ለመወከል ከአምላክ ጋር ቀረብ ብሎ ባነጋገርም በአኗኗርም መታረም አለበት፡፡ በመሪያችን በክርስቶስ ላይ ያልታረመ መጥፎ ጠባይ ታይቶ አያውቅም፡፡ ከሰማይ የተላከ ወኪል ተከታዮቹም እንደ እርሱ መሆን አለባቸው፡፡ አምላክ በመንፈሱ አማካይነት ሰውን አነጋገሩን አንዲያሻሸል ይረዳዋል፡፡ ግን በዚህ ዓይነት ዘዴ ተናገር ብሎ ማንንም አያስገድድም::GWAmh 56.1

    አምላክ የማመዛዘን ችሎታና ራሳችንን የማሻሻል ምርጫ አድሎናል፡፡ የተቻለንን ከሞከርን በኋላ ከአቅማችን በላይ የሆነውን ወደ አምላካችን በጸሎት አማካይነት ብናቀርብ ያምራል፡፡GWAmh 56.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents