Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ተጠንቀቁ»

    ጳውሎስ ለጢሞቴዎሥስ የሰጠው ምክር ለማንኛውም ጠጣት ወንጌላዊ ይጠቅማል፡፡ «ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፡፡› ፤፲ ጢሞ. 4፡16 «ለራስህ” የሚለው ሐረግ የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፡፡ መጀመሪያ ጌታ አንዲያነጻህና አንዲቀድስህ ራስህን አስረክበው፡፡ ከማይገለጽ ከማራኪ ንግግር ይልቅ የተቀደሰ ሕይወት ታላቅ ምሣሌነት (አብነት) አለው፡፡ የነፍስህን ፋኖስ ወልውልና በመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላው፡፡ የተሳካ ሥራ ሊያሠራ የሚችለውን የማስተዋል ፀጋ ከክርስቶስ ዘንድ: ሕይወቱን ለለወጠላቸው መሥራት ምን ማለት መሆኑን ከእርሱ ተማር፡፡GWAmh 64.2

    መጀመሪያ ለራስህ፤ ከዚያም ለትምህርትህ «ተጠንቀቅ» ልብህን በኃጢዓት አታደንድን:: ልምድህንና ጠባይህን ተመራመር፡፡ በእግዚአብሔር ቃል አየመዘንህ የማይገጥመውን ጠባይህን አስወግድ፡፡ ቃሉ እንዲስተዋልህ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከህ በፀሎት ተማጸነው፡፡ እውነትን ከልብህ የምትከተል ከሆንህ ተከራካሪ ሲያጋጥምህ መላዕክት በአፍህ ላይ ሆነው የምትመልሰውን ያቀብሉሃል፡፡ - ቀን በቀን የሱስን ከተገናኘህ ቃልህና ሥራህ ታላቅ አብነት ይኖረዋል፡፡GWAmh 64.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents