Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስለ ክርስቶስ ማስተማር

    ተናጋሪዎች ሁሉ በንግግራቸው ስለ ክርስቶስ ከመናገር ይልቅ ስለሕግ በማስተማራቸው ብዙ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል፡፡ ይህ አባባል እውነት አይሆንም፣ ግን ለአባባሉ ምክንያት የለውም ወይ? ስለእግዚአብሔር ሥራ በቂ ዕውቀት የሌላቸው፤ የክርስቶስን ጽድቅ ያልለበሱ ሰዎች በመናገሪያው ቦታ ላይ ቆመው አያውቁምን? አብዛኛዎቹ ወንጌላዊያን ማስተማራቸውን በክርክር መልክ ከማቅረብ በቀር ስለ ክርስቶስ የማዳን ኃይል እምብዛም አያብራሩም፡፡GWAmh 96.4

    በአገልግሎታቸው የክርስቶስን ደም የማንጻት ኃይል ይዘሉታል፡፡ መሥዋዕታቸው ከቃየል መሥዋዕት ጋር ይመሳሰላል፡፡ የፍሬ መሥዋዕት ማቅረቡ በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ አልነበረም:: ግን የታረደው በግ ያለውን ምሣሌነት ያህል ስለ ክርስቶስ መሥዋዕትነት ትርጉም አልነበረውም፡፡ ክርስቶስ የማይነሳበት የማይወሳበት አገልግሎት (ስብከት) እንደዚሁ ነው:: የሰዎች ልብ አይነካበትም፡፡ እድን ዘንድ ምን ላድርግ? የሚለው ጥያቄ ዕረፍት አይነሳቸውም፡፡GWAmh 97.1

    ሰባተኛውን ቀን አክባሪ አድቬንቲስት የሆኑ ክርስቲያናት ሁሉ ክርስቶስን በዓለም ፊት አልቀው ማሳየት አለባቸው፡፡ የሶስተኛው መልአክ መልዕክት የሰንበትን ዕውነተኛነት ያረጋግጣል፡፡ በዚህ መልዕክት ውስጥ የሰንበት እውነተኛነት ሊታወጅ ይገባል፣ ቢሆንም ክርስቶስ መዘንጋት የለበትም፡፡ ምህረትና እውነት፣ ጽድቅና ሰላም የተዋሃዱ በክርስቶስ መስቀል ላይ ነው፡፡ ኃጢዓተኛው ወደ ቀራኒዮ መስቀል ሊመለከት ይገባዋል፡፡ በመድኃኒታችን ደግነት እንደ ልጅ ሊተማመን ይገባዋል፡፡ ጽድቅን ይቀበል፣ ምህረቱንም :GWAmh 97.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents