Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወንጌላዊያን የጤና አጠባበቅ ሲያስተምሩ

    ወንጌላዊያኖቻችን በጤና አጠባበቅ ትምህርት አዋቂዎች መሆን አለባቸው፡፡ የአካልን አንቅስቃሴ የሚገታውን ሕግ አውቀው አካል ከአእምሮ ጋር ያለውን ግንኙነት ማስተዋል አለባቸው፡፡ በብዙ ሺህ የሚቀጠሩ ሰዎች እግዚአብሔር ስለሰጣቸው አስገራሚ አካል የሚያውቁት ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ እንዴት አንደሚንከባከቡት በፍጽም አያውቁም፡፡ ሌላ አነስተኛ ጥቅም ያላቸውን ነገሮች ወደ መማሩ ያዘነብላሉ፡፡ ወንጌላዊያን በዚህ መስመር አቢይ ተግባር አላቸው፡፡ ትምህርት ላይ የተስተካከለ ዕውቀት ሲኖራቸው ተሳካላቸው ማለት ነው:: ትክክለኛ የኑሮ ደንብን በመከተልና በጤና በመኖር በቤታቸውና በኑሮአቸው የጤናን ሕግ ማስከበር አለባቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ሕዝቡን ወደ ከፍተኛ የጤና አኗኗር ለመምራት ቢያስተምሩና ቢናገሩ ያምርባቸዋል፡፡ ራሳቸው በብርሃን በመኖር ብርቱ ምክር ለሚያሻቸው ጠቃሚ መልዕክት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡GWAmh 146.3

    ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎታቸው ጋር ወንጌላዊያን የጤናን ትምህርት ቢያስተምሩ ክቡር በረከትና መልካም የኑሮ ዕድገት ያተርፋሉ፡፡ ምዕመናን ስለጤና ትምህርት የበራ ዕውቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህ ሥራ ከመናቁ የተነሳ ብዙዎች የጤናን ሕግ ችላ በማለት ባመጡት ጠንቅ ሊሞቱ ያጣጥራሉ፡፡GWAmh 146.4

    የመሥሪያ ቤታችን ኃላፊዎች ይህን ጠቃሚ ትምህርት አስፋፍተው ከሆነ በትክክለኛው መንገድ መራመዳቸውን ይወቁት፡፡ ካላስተማሩ ግን እንደሆን ተሳስተዋል ማለት ነው፡፡ መምህራንና ወንጌላዊን የተገለጠላቸውን ብርሃን ለሌሎች ያዳርሱ፡፡ ይህ ሥራ በየትኛውም መስመር ተፈላጊ ነው፡፡ የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ሲሉ ከትክክለኛው መንገድ የማይወጡትን በእውነት ጸንተው የሚኖሩትን ሰዎች እግዚአብሔር ያበረታቸዋል፡፡GWAmh 147.1

    እግዚአብሔር ስለጤና አጠባበቅ የሰጠው መምሪያና ማስጠንቀቂያ ግልዕ ነው: ሰዎች የሚመዘኑትና የሚፈተኑት በዚሁ መምሪያ አማካይነት ነው:: እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያንና ቤተሱበ ደንቡን ማክበር አለበት፡፡ ሁሉም ጤናን ሳያቃውሱ መብላትና መጠጣትን መማር አለባቸው፡፡ በዓለም የመዝጊያ ምዕራፍ ስንኖር ስለ ሰንበትን አክባሪዎች ሊኖራቸው የሚገባውን የሕይወት ንጽህና ሊኖረን ይገባል፡፡ ሰዎችን ስለጤናቸው ከመምክር ችላ የሚሉ ሰዎች፣ የታላቁ ሐኪም የክርስቶስ ተከታዮች አይደሉም፡፡GWAmh 147.2

    የወንጌልና የሕክምና ሥራዎች ጎን ለጎን ሆነው መራመድ አለባቸው፡፡፡ ወንጌል በትክክለኛው የጤናማ አኗኗር አማካኝነት መገለጥ አለበት፡፡ ክርስትና በሥራ መገሰጥ አለበት፡፡ ከልብ የመነጨ እውነተኛ የመታደስ ሥራ ሊካሄድ ይገባዋል፡፡ የእውነተኛ ሃይማኖት ዓላማ የእግዚአብሔርን ከፍተኛ ፍቅር ለወደቀው የሰው ዘር መግለጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ተግባር በዘመናችን ያሱ ሰዎችን በትክክለኛ አና በእውነተኛ አረማመዳቸው ወደ ብርሃን መምራት ነው፡፡ የጤናን ደንብ የቻልነውን ያህል በንግግርና በሥራ ለሰዎች ማሳየት ይገባናል፡፡GWAmh 147.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents