Go to full page →

ንግድ ነክ ጉዳይ GWAmh 266

ስብሰባዎቻችን መንፈሣዊ ነክ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡ የንግድ መለዋወጫ ክጋጣሚ ጊዜያት መሆን የለባቸውም፡፡ ከልዩ ልዩ ቦታና ከልዩ ልዩ የሥራ መስመር የመጡ ሰዎች ስላሉ በየመስመሩ ስላለው የሥራ ዘርፍና ስለማካሄጃው ቢነጋገሩ መልካም ነው፡፡ GWAmh 266.3

ይህ ዓይነት ውይይት ዋናውን የወንጌል ጥረት ካላደናቀፈ በቀር በጣም ጠቃሜ ነው፡፡ ወንጌላዊያን ከዋናው ሥራቸው ተወግደው በጥቃቅን ነገሮች የተወሰነ አንደሆን ግን የስብሰባው ዓላማ ቀረ ማለት ነው፡፡ በብዙ ስብሰባሥች መጨረሻ ሳላይ የተካፈለው ሕዝብ ሁሉ ሰልችቶ ይወብል : ብዙዎች ከስብሰባው የጠበቁትን እርዳታና መታደስ ስላላገኙ አዝነው ይመለሳሉ፡፡ የበለጠ እውቀት ሽተው የመጡት ስብሰባውን ከመካፈሳቸው በፊት የነበራቸው ዕውቀት ሳይሻሻል፣ ለቤተሰባቸውና ለቤተ ክርስቲያናቸው የበለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚችሉ ይመለሳሉ፡፡ GWAmh 266.4

ንግድ ነክ ነገሮች ያው ሥራ መስመራቸው የሆነ ሰዎች ብቻ ይነጋገሩባቸው፡፡ ለሕዝቡ የሚገለጡት በሰንበት ቀን መሆን የለበትም፡፡ ስለ መጽሐፍና መስጥ፣፤ ስለ ስንበት ትምህርት ሥራ ስለጽሑጡፍ ማደልና ስለ ሚሲዎናዊነት በተለየ ቦታ፣ በተለየ ሥባ:ራ፤ ልዩ ትምህርት መሰጠት አለበት፡፡ ለባለትና ትምህርትም በዚያው አቋም መዘጋጀት አለበት፡፡ እነዚህ ሁሉ በበኩላቸው መልካም ቢሆነም የስብሰባውን ጊዜ መያዝ የለባቸውም፡፡ GWAmh 267.1

የልዩ ልዩ ሰበካዎች ኃላፊዎችና ወንጌላዊያን የሕዝቡን መንፈሳዊ ይዞታ መከባከብ ስላለባቸው ከእንዲህ ያለው የሥራ ስብሰባ ነዓ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወንጌላዊያን በተፈሰገ ጊዜ በስብሰባው ውስጥ መምህራንና መሪዎች ሆነው ሲሰሩ ይችላሉ፤ ግን ከመጠን በላይ መድከም የለባቸውም፡፡ የመንፈስ መታደስና ደስታ ሲሰማቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰስብሰባው መሳካት ሊረዳ ይችላል፡፡ የማበረታቻና የማደፋፈሪያ ቃላት በመናገር በታመኑ ልቦች ውስጥ የእውነት ዘር ሊዘሩ ይችላሉ፡፡ GWAmh 267.2