Go to full page →

ራስን የመቻል መንፈስ GWAmh 326

አውስትራሊያን ሳልሰቅ በፊት፣ ወደዚህ አገር ከተመለስሁም በአሜሪካ ብዙ ሲሠራ የሚገባው ሥራ መናሩ ተነግሮኛል፡፡ መደመሪያ ሥራውን የቆረቁሩት ሠራተኞች እያለፉ ናቸው፡ ለሥራው ግንባር ቀደም ከነበሩት ጥቂቶች ብቻ ከመካከላችን ይገኛሉ፡፡ ዱሮ የሥራ ልምድ ባላቸው ሰዎች ይካሄዱ የነበሩ ኃላፊነቶች ለወጣቶች ተላልፈዋል፡፡ GWAmh 326.1

ይህ ኃላፊነት ለወጣቶች የመተላለፍ ጉዳይ መሰናክል ስለሚገጥመው ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ ዓለም ለበላይነት በመተናነቅ ላይ ነው፡ ከሥራ ባልደረቦች የመለየት መንፈስ፣ የመፍረስ ስሜት ፅለታዊ ትርኢት : ለአንዳንዶቹ ድርጅት መቋቋም የግልን ነፃነተ አንደ መግፈፍ ሆና ይሰማቸዋል፡-፡ የተታለሱ ሰዎች ራሳቸውን ችለው መሥራታቸውን ወይም ለመሥራት መሞክራቸውን እንደመልካም ነገር ቆጥረውት ጉራ ይነዛሉ፡፡ የማንንም አባባል እንደማይቀበሉና በማንም እንደማይመሩ ይናገራሉ፡፡ ከወንድሞቻቸው ምክር ተለይተው በመኖር እግዚአብሔር የፈሰገባቸውን የፈጸሙ የሚያስመስላቸው ሰይጣን መሆኑ ተነግሮኛል፡፡ GWAmh 326.2

ሥራችን አንዳይፋፉ የሚያደርግ አደጋ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚፈሩ መሪዎች አማካይነት በማስተዋል መራመድ. አለብን፡፡ ብርታትና ደህንነት የምናገኝ በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡ GWAmh 326.3