Go to full page →

የቋንቋ ችግር GWAmh 51

ከመካከላችን የውጭን ቋንቋ ማጥናት የማይቸግራቸውና መልዕክቱን በቀላሉ ሲያዳርሱ የሚችሉ አሉ፡፡ በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ጊዜ ሚሲዮናዊያን ታምራዊ የቋንቋ ችሎታ ስለተሰጣቸው የወንጌልን ፀጋ ለብዙ አገሮች በቀላሉ አዳረሱ፡፡፡ እግዚአብሔር የጥንት አገልጋዮቹን ከረዳ እኛንስ የአገሬውን ሰዎች ለአስተማሪነት አሠልጥነን ለአገራቸው ስዎች በራሳቸው ቋንቋ እንዲያስተምሩ እንድናደርግ የማይረዳን ይመስላችኋል? GWAmh 51.1

በውጭ አገር የሥራ መስኮች የሚሠሩ ሠራተኞች የወጣቶች ችሎታ ተከታትለው ቢያሠለጥኑ ኖሮ ብዙ ሠራተኞች በተገኙ ነበር:: ወጣቶች የውጭ ቋንቋዎች ቢማሩ አይጐዳም፡፡ ይህ ሊደረግ የሚቻለው ከሰዎቹ ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመሥረት ነው፡፡ ነገር ግን እድሜአቸው የገፋ ሰዎች አዲስ ቋንቋ ማጥናት ያስቸግረዋል፡፡ ግን በዚህ ምክንያት መልካም ልምድ ያላቸው ጠና ያሱ ሰዎች ሚሲዮናዊያን አይሁኑ ማለት አይደለም፡፡ GWAmh 51.2