Go to full page →

ወጣቱ ወንጌላዊ GWAmh 63

ወጣቶች የክርስቶስ ተባባሪዎች ሆነው ለወንጌሉ ሥራ መሰለፍ አለባቸው፡፡ «እነርሱም ደግና” በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ፡፡» ራሳቸውን ለክርስቶስ ቢያስረክቡ ነፍሳትን ለማዳን መሣሪያ ያደርጋቸዋል፡፡ ለወንጌል አገልግሎት የተጠራ ወጣት ጥሪውን ከፍ አድርጐ በመገመት ጊዜውን፣ ጉልበቱን፣ ጥረቱን ለዚህ ቅዱስ ሥራ ለማዋል ይወስን፡፡ GWAmh 63.5

የቀደሙት ሲያልፉ ሥራው አንዳይታጐል ወጣቶች ክፍት በሚሆነው የሥራ ቦታ ለመተካት ይዘጋጁ:: ብርቱ ጦርነት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ወጣትነትና ብርታት ያላቸው ሰዎች የጥፋት ጥላ ያጠላባቸውን ነፍሳት ከጨለማወው ዓለም ማውጣት አለባቸው፡፡ GWAmh 64.1