Go to full page →

ለመስተንግዶ ዋጋ መክፈል GWAmh 65

ወጣት ወንጌላዊያን በእየሄዱበት ንቁ መሆን አለባቸው፡፡ ሰዎችን በአየቤታቸው ሰ.ጉበኙ አስተናጋጆቻቸውን ከመርዳት ዝም ማለት የለባቸውም:: ሁሉም የጋራ ግዴታ አለባቸው:: ለመርዳት ዕድል ሲያጋጥማቸው ወንጌላዊ ዕድሉን ማሳለፍ የለበትም፡፡ አስተናጋጁ የትልቅ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ይሆንና ሥራ ይበዛበት ይሆናል፡፡ የሥራው ተካፋይ በመሆን ጠንጌላዊው የሰዎችን ልብ ስቦ ዕውነትን ለመዝራት ምቹ ጊዜ ያጋጥመው ይሆናል፡፡ GWAmh 65.2

ወንጌላዊ ለምቾትና ለስንፍና ወዳድ ከሆነ አይሳካለትም፡፡- ሰወንጌል ሥራ የሚዘጋጁ አጥልቆ ማሰብን ይማሩ ዘንድ ከበድ ያለ የጉልበት ሥራ መሥራት አለባቸው: ወጣቶች በችግር ጊዜ ሊሲያገለግሏቸው የሚችሉ ትርፍ የሥራ ዘርፎች ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ የእጅና የጉልበት ሥራ መማር በጭንቅ ጊዜና ችግር በተነሳ ጊዜ አገልግሎቱ ከፍተኛ ነው:: GWAmh 65.3