Go to full page →

ላለማወቅ (ለድንቁርና) ምክንያት የለም GWAmh 64

አንዳንድ ወንጌላዊያን- የኃላፊነታቸው ከባድነት አይሰማቸውም፡፡ የወንጌላዊነት ብቁነታቸው የተሳሳተ ነው፡፡ ወንጌላዊ ለመሆን መጠነኛ የሰነፍ ጥረትና የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት በቂ ይመስላቸዋል፡፡ ኣንዳንድ ወንጌላዊያን አንድ ጥቅስ በቃላቸው መጥቀስ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል አንደፈለጉ በማወላገድ ኃጢዓት ይሠራሉ፡፡ «ያልተጻፈ በማንበብ” የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛ ትርጉም ያበላሻሉ፡፡ GWAmh 64.4

አንዳንዶቹ «አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ካደረበት መጽሐፍ አዋቂነቱ እምብዛም ተፈላጊ አይደለም” ይላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንቁርናን ለመካስ መንፈሱን አይልክም፡፡ ለመማር አድል ያላገኙትን ይባርክ ይሆናል፡፡ ደካምነታቸውንም በብርታቱ ይደግፍላቸዋል፡፡ ቢሆንም ማንም ቃለ-እግዚአብሔርን የመማር ግዳጅ አለበት፡፡ በሳይንስ አለመራቀቅ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥናት ችላ ለማለት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሳይንስ ዕውቀት የሌለው ሰው አንብቦ ሊረዳው ይችላል፡፡ GWAmh 65.1