Go to full page →

ዘዴኛነት (ብልሐተኝነት) GWAmh 71

ነፍሳትን በማዳን ተግባር ጥበብና ዘዴ ያስፈልጋል፡፡ ጌታችን ዕውነትን ሳይደብቅ በፍቅር ይናገር:ከሰዎች ጋር ሲገናኝ ከፍተኛ ብልሀት ነበረው፡፡ ሁልጊዜም ቸርና አጥልቆ አሳቢ በፍጹም ብልግና አላሳየም፡፡ ሳያስፈልግ ከባድ አነጋገር አልተናገረም፡፡ የሰዎችን ስሜት አልጐዳም፡፡ ቢሆንም የሰብዓዊን ደካማነት አልከዳደነም፡፡ ግብዝነትን፣ ክፋትን፣ አለማመንን፣ አጥላልቶ ቢነቅፍም ሰዎችን ሲገሥዕ አይኖቹ እንባ ያዝሉ ነበር: እውነትን ቢናገርም ጨካኝ አልነበረም፡- ለሰው ያለውን ርህራሄ በግልጽ አሳይቷል፡፡ በእርሱ ግምት የማንም ሕይወት ክቡር ነው:: ሰውነቱ መለኮታዊ ክብር የሰፈነበት ቢሆንም ሁሉን የአምላክ ቤተሰብ አባል በትህትና : ሁሉንም ነፍሳት ማዳን፣ የተላከበት ተግባር መሆኑን ተገነዘበ፡፡ GWAmh 71.5