Go to full page →

ህብረት (ጽናት) GWAmh 86

በአሁኑ ዘመን የተፈተነ ድፍረትና የማይናወጥ ጽናት ያላቸው፣ስለ እውነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለመናገር የማይፈሩ ሰዎች ያስፈልጋለ፡፡ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ «ሥራችሁ ሁሉ ጽናት ያለው ይሁን” እላለሁ፡፡ በኃላፊነታችሁ የሚዋጠው አሥራትና ገንዘብ ወዲያውኑ ተገቢ ቦታውን ይያዝ፡፡ በኋላ አተካዋለሁ ብሎ ለእግዚአብሔር ሥራ የተዋጣን ገንዘብ ለግል (ተግባር) ማዋል ክልክል ነው፡፡ GWAmh 86.4

ለእግዚአብሔር ሥራ ለተከፈለ ገንዘብ ቀንና ዓ.ም. የተጻፈበት ደረሰኝ ኃላፊው (ተቀባዩ) ለከፋዩ ወዲያው መስጠት አለበት፡፡ ከዚያ ተቀባዩ ፈተና አንዳይመጣበት ወዲያውኑ ገንዘቡን ተገቢውን ቦታ ያስይዘው፡፡ GWAmh 86.5