Go to full page →

ልጆችን ማስተማር (ለልጆች መስበክ) GWAmh 130

በማንኛውም አጋጣሚ የየሱስ የፍቅሩ ታሪክ ተደጋግሞ ይነገራቸው፡፡ በማንኛውም አገልግሉት ለእነርሱ የሚሆን ትምህርት ሳይሰጥ አይታለፍ፡፡ የክርስቶስ አገልጋይ ከእነርሱ ጋር የማይረሳ ወዳጅነት ሊኖረው ይገባል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸው የላቁ እንዲሆኑ ከማስተማር አይቦዝን፡፡ ይህ ዘዴ ከተገመተው በላይ የሰይጣንን አካሔድ ያደናቅፍበታል፡፡ ልጆች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በደንብ ከተዋወቁ ተጠራጣሪነት አያጠቃቸውም፤ ጠላትን «ተጽፏል” በሚል ጋሻ ሊከላከሉት ይችላሉ፡፡ GWAmh 130.5

ወጣቶችንና ልጆችን የሚያስተምሩ ሰዎች አሰልቺ ንግግር ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው፡፡ ንግግራቸው አጠር መጠን ብሎ ተፈላጊውን ትምህርት ያጠቃለለ ይሁን:: ብዙ ሊሰጥ የሚገባው ትምህርት ካለ ከፋፍሎ ማስተማር ነው፡፡ ሁሉን ትምህርት በአንድ ጊዜ ከመጫን በየጊዜው እየከፋፈሉ ማስተማር ዋጋ አለው:: ረዥም ንግግር የወጣቶችን አእምሮ ያደክማል፡፡ ብዙ ንግግር መንፈሳዊ ትምህርትን አንዲጠሉ ደርጋቸዋል።፡ ልክ ከመጠን በላይ ሲበሉ አህል አንደሚያስጠላ ማለት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትምህርታችን በተለይ ለወጣቶች የሚሰጠው ከዚህ ትንሽ ከዚያ ትንሽ፣ መስመር በመስመር ቃል በቃል ላይ መሆን አለበት፡፡ ልጆችን ወደሰማይ ለማቅረብ የሚረዳ , ግልምጫ ሳይሆን ፍቅርና ደግነት ነው፡፡ GWAmh 131.1