Go to full page →

ክርስቶስን ረዳትህ አድርገው CLAmh 17

ሰው በክርስቶስ እርዳታ ቢጠቀም እግዚአብሔር እንደሚፈልገው ለመሆን ይችል ነበር፡፡ ሰብአዊ ጥበብ ሊያደርገው የማይችለውን ነገር ራሳቸውን ለሚሰጡት ሁሉ እግዚአብሔር በጸጋው ያከናውንላቸዋል፡፡ በጸጋው መለኮታዊ በሆነ ፍቅር ልባችንን ያቆራኛል፡፡ ፍቅርም የመደለያና የማታለያ መሣሪያ አይሆንም፡፡ አንድ ልብ ከሌላው ጋር በፍቅር ገመድ ለዘለዓለም ይቆራኛል፡፡ CLAmh 17.3