Go to full page →

4—የዘመናዊ ቤተሰብ ምሳሌ CLAmh 17

ወንጌል አስገራሚ የሆነ የሕይወት ችግር አቃላይ ነው፡፡ ትምህርቱን ብንከተል ብዙ ችግር ስለሚያቃልልልን ብዙ ስህተት ከመሥራት እንድናለን፡፡ ዘላለማዊውንና አላፊውን ነገር ለይተን እድናውቅና ዘላለማዊነት ያለውንም ነገር ለማግኘት እንድንጥር ያስተምረናል፡፡ ትዳር የማቋቋም ኃላፊነት ያለባቸው ሁሉ ይህ ዓይነት ትምህርት ያሻቸዋል፡፡ ከፍ ወዳለው ዓላማ ከማነጣጠር መመለስ የለባቸውም፡፡ የዚህ ዓለም ቤታችን የሰማዩ ቤት ምሳሌና ለሰማዩ ቤት መዘጋጃ መሆኑን ማስታወስ ይገባቸዋል፡፡ ሕይወት ወላጆችም ሆኑ ልጆች ለሰማዩ ኑሮ የሚሰለጥኑበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ቤት የሚሰራበት ቦታ በሚመረጥበት ጊዜ በዚህ ሐሳብ መመራት ያስፈልጋል፡፡ በብልጽግና ምኞት፣ በአለባበስ ዓይነትና (ፋሽን) በኅብረተሰብ ልምድ አለመገደድ ነው፡፡ ሊታሰቡ የሚገባቸው ግን ንጽህና፣ ጤንነትና ጠቃሚነት ናቸው፡፡ CLAmh 17.4

በመላው ዓለም በየከተማው አመጽ እየበዛ ሔዷል፡፡ በየቦታው ዝሙትና ገንዘብ ማባከን እየበዛ ሄዷል፡፡ ወንጀል በዝቷል፡፡ በየቀኑ ስርቆት፣ ነፍስ መግደል፣ የራስን ሕይወት ማጥፋትና ሌላም ወንጀል መደረጉን አንሰማለን፡፡ CLAmh 18.1