Go to full page →

ምዕራፍ 2—የቀድሞው ወግ አጥባቂነት ሊደገም ነው፡፡ Amh2SM 25

የወሰን ምልክቶችን መንቀል (ማስወገድ) Amh2SM 25

ሕዝባችን ለእምነታችንና ባለፉት ጊዜያቶች ለነበሩን ልምምዶቻችን ምክንያቶቹ ምን እንደሆኑ ማስተዋል አለበት፡፡ ብዙዎች ከዚህ በፊት የነበሩ ልምምዶቻችንን ለመንቀልና አሮጌ ምልክቶችን ለማስወገድ የሚያዘነብሉ ንድፈ ሀሳቦችን በሚያቀርቡ ሰዎች ላይ ገደብ የለሽ የሆነ እምነት መጣላቸው እንዴት አሳዛኝ ነው! እንዲህ በቀላሉ በሀሰት መንፈስ መመራት የሚችሉ ሰዎች ከእምነት እየተለዩ መሆናቸውን እስካላወቁ ድረስ ወይም በእውነተኛው መሠረት ላይ እየገነቡ እስካልሆኑ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ ትክክለኛ ያልሆነ መሪን ሲከተሉ እንደነበሩ ያሳያሉ፡፡ ሁሉም በደንብ እንዲያዩና የእምነትን እውነተኛ ምሶሶዎች እንዲለዩ መንፈሳዊ መነጽሮቻቸውን እንዲያደርጉና ዓይኖቻቸውን እንዲኳሉ ማደፋፈር አለብን፡፡ ያኔ «ይህ ማህተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት» (2ጢሞ. 2፡19) ጸንቶ መቆሙን ያውቃሉ፡፡ አንዴ ለቅዱሳን የተሰጡትን አሮጌ የእምነት ማስረጃዎች ማነቃቃት አለብን፡፡ {2SM 25.1} Amh2SM 25.1

እውነት እንዳላቸው በሚያስቡ ሰዎች እያንዳንዱ ሊታሰብ የሚችል ብልጭልጭና አታላይ አስተምህሮ ይቀርባል፡፡ አሁን አንዳንዶች በአዲስቷ ምድር ልጆች ይወለዳሉ ብለው እያስተማሩ ናቸው፡፡ ይህ የወቅቱ እውነት ነው ወይ? እንዲህ ዓይነቱን ንድፈ ሀሳብ እንዲያቀርቡ እነዚህን ሰዎች ያነሳሳው ማን ነው? ጌታ ለማንም ቢሆን እንደ እነዚህ ያሉ ሀሳቦችን ሰጥቷልን? አልሰጠም፡፡ የተገለጡት ነገሮች ለእኛና ለልጆቻችን ናቸው፣ ነገር ግን ባልተገለጡ ጉዳዮችና ከድነታችን ጋር ግንኙነት በሌላቸው ነገሮች ላይ ዝምታ ትክከለኛ ነገር ነው፡፡ እነዚህን እንግዳ የሆኑ ሀሳቦች እንደ አስፈላጊ እውነቶች ማስተማር ይቅርና መጠቀስ እንኳን የለባቸውም፡፡ {2SM 25.2} Amh2SM 25.2

ነገሮች በትክክለኛ ስማቸው መጠራት ወዳለባቸው ጊዜ ደርሰናል፡፡ በቀድሞዎቹ ዘመናት እንዳደረግነው ሁሉ እንነሳና በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር ስር ሆነን የማታለያ ሥራን እንገስጸው፡፡ አሁን እየተንጸባረቁ ያሉት አንዳንድ ሀሳቦች ወደ ፊት ሊቀርቡ ላሉ አንዳንድ እጅግ ጽንፈኛ ለሆኑ ሀሳቦች መጀመሪያ ናቸው፡፡ ከ1844 በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከተጋፈጥናቸው ትምህርቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ትምህርቶች በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ወሳኝ ቦታ በያዙ በአንዳንድ ሰዎች እየተስተማሩ ናቸው፡፡ {2SM 26.1} Amh2SM 26.1

በኒው ሀምሻዬር፣ ቨርሞንት እና በሌሎች ቦታዎችም ይህን ቀስ ብሎ እየመጣ ያለውን አታላይ የወግ አጥባቂነት ሥራ መከላከል አለብን፡፡ የድፍረት ኃጢአቶች ተፈጽመዋል፣ አንዳንዶች እርካታ ለማግኘት በሚል ሽፋን እርኩስ የሆኑ ፍትወቶችን በነጻነት ፈጽመዋል፡፡ መንፈሳዊ ነጻ ፍቅር የሚል አስተምህሮ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ «በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያዳመጡ ኃይማኖትን ይክዳሉ» (1ጢሞ.4፡1) የተባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲፈጸም እንመለከታለን፡፡ --The Southern Watchman, April 5, 1904. {2SM 26.2} Amh2SM 26.2