Go to full page →

ሁሉም በክርስቶስ አንድ ናቸው Amh2SM 342

ከሰብአዊ ቤተሰብ ውስጥ ማናቸውም ቢሆኑ ራሳቸውን ለክርስቶስ ቢሰጡ፣ ማናቸውም ቢሆኑ እውነትን ቢሰሙና ቢታዘዙ፣ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ይሆናሉ፡፡ ሞኞችና ጠቢባን፣ ሐብታምና ደሃ፣ አህዛብና ባሪያ፣ ነጭ ወይም ጥቁር ቢሆን ኢየሱስ የነፍሳቸውን ዋጋ ከፍሎላቸዋል፡፡ በእርሱ ካመኑ የሚያነፃው ደሙ በእነርሱ ላይ ይደረግላቸዋል፡፡ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ከነጭ ሰው ስም አጠገብ የጥቁር ሰው ስም ተጽፏል፡፡ ሁሉም በክርስቶስ አንድ ናቸው፡፡ ትውልድ፣ ቦታ፣ ዜግነት ወይም ቀለም ሰውን ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደርግ አይችልም፡፡ የሰውን ማንነት የሚወስነው ባሕርይ ነው፡፡ ቀይ ሰው (የአሜሪካ ሕንድ)፣ ቻይናዊ ወይም አፍሪካዊ በመታዘዝና በእምነት ልቡን ለእግዚአብሔር ከሰጠ ከቆዳ ቀለሙ የተነሳ የክርስቶስ ፍቅር አይቀንስበትም፡፡ እጅግ የተወደድክ ወንድሜ ብሎ ይጠራዋል፡፡ Manuscript 6, 1891. Amh2SM 342.4