Go to full page →

ምዕራፍ 42—ከሌላ ሕዝብ ጋር ስለመጋባት የተሰጠ ምክር Amh2SM 343

ሁላችንም ወንድማማቾች ነን፡፡ ትርፉ ወይም ኪሳራው ምንም ቢሆን በአምላካችንና በአዳኛችን ፊት በጨዋነትና በድፍረት መሥራት አለብን፡፡ ሰዎች ሁሉ፣ ነጮችና ጥቁሮች፣ ነጻ እና እኩል መሆናቸውን እንዲቀበሉ ክርስቲያኖች ለዚህ መርህ እንገዛ፣ በዓለምና በሰማያዊ ኃይሎች ፊት ፈሪዎች አንሁን፡፡ ለነጭ ሰው የምንሰጠውን አክብሮት ለጥቁር ሰውም እንስጥ፡፡ አሁን በቃልና በምሳሌነት ሌሎችን ወደዚህ አቅጣጫ መማረክ አለብን፡፡ Amh2SM 343.1

ነገር ግን የነጭና የጥቁር ዝሪያዎችን ጋብቻ በተመለከተ ተቃውሞ አለ፡፡ ልጆቻቸውን ተጎጂ በሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ የማድረግ መብት እንደሌላቸው ሁሉም መገንዘብ አለባቸው፡፡ ለእድሜ ልክ ውርደት የሚዳርጋቸውን ነገር እንደ ብኩርና አድርገው የመስጠት መብት የላቸውም፡፡ ከእንደዚህ ዓይነት ቅልቅል ጋብቻ የሚወለዱ ልጆች ይህን የዕድሜ ልክ ውርስ በሰጧቸው ወላጆች ላይ የመማረር ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት፣ ሌሎች ምክንያቶች ባይኖሩ እንኳን፣ በነጭ እና በጥቁር ዝርያ መካከል ጋብቻ መፈጸም የለበትም፡፡ Manuscript 7, 1896. Amh2SM 343.2