Go to full page →

የስኬት ምስጢር ChSAmh 197

ለሌሎች እያቀረቡ ያሉት የተቀደሰ እውነት ለእርስዎም ሕያው ሐቅ ሆኖ ልቦችን ይነካ ዘንድ ጸሎትዎም ሆነ ስብከትዎ በቅንአት የተሞላና ልባዊ ይሁን፡፡ ለየሱስ የሚያደርጉት ማንኛውም ነገር በቅንአትና በሙሉ ኃይልዎ እንዲሆን ምኞት ይደርብዎ፡፡ ቀጣይ ዕድገት ከማይኖረው የመጨረሻው ከፍታ ላይ እንደወጡ አድርገው አያስቡ፡፡ . . እውነትን የሰዎችን ልብ በሚማርክ መልኩ ማቅረብ ይችሉ ዘንድ አእምሮዎ ከአገልግሎት ጋር የተቆራኘ ይሁን፡፡ ልብ የሚነኩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለሌሎች ማካፈል እንዲችሉ በቃልዎ ይያዝዋቸው፡፡ በቀጥታ ወደ ዋናው ነጥብ በማምራት የአድማጭዎን ትኩረት ለመሳብና ጌታ በተጠቀመበት መንገድ ለማስተማር ጥረት ያድርጉ፡፡--Review and Herald, July 26, 1887. ChSAmh 197.2

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጡትን ቃላት እንዳሉ በማቅረብ ብቻ ታላቅ ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ እያንዳንዱ ደጃፍ ይዘው በመሄድና በግልጽ የቀረበውን ልእክት ወደ እያንዳንዱ ሕሊና የማድረስ ተነሳሽነት በማሳየት አዳኙ ባዘዘው መሰረት “መጻሕፍትን” ይመርምሩ፡፡ መለኮታዊውን ዕውቀት ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ እንዳለ ሊወሰድ እንደሚገባ በጥብቅ ያስገንዝቡ፡፡ የብርሐን ጮራ ፈንጥቆ ነፍሳት እያንዳንዱን የከበረ ጨረር በደስታ ሲቀበሉ ያለ ፍርሐት ለውጤቶቹታማኝ ይሆናሉ፡፡— Testimonies, vol, 5, p. 388. ChSAmh 197.3