Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የስኬት ምስጢር

    ለሌሎች እያቀረቡ ያሉት የተቀደሰ እውነት ለእርስዎም ሕያው ሐቅ ሆኖ ልቦችን ይነካ ዘንድ ጸሎትዎም ሆነ ስብከትዎ በቅንአት የተሞላና ልባዊ ይሁን፡፡ ለየሱስ የሚያደርጉት ማንኛውም ነገር በቅንአትና በሙሉ ኃይልዎ እንዲሆን ምኞት ይደርብዎ፡፡ ቀጣይ ዕድገት ከማይኖረው የመጨረሻው ከፍታ ላይ እንደወጡ አድርገው አያስቡ፡፡ . . እውነትን የሰዎችን ልብ በሚማርክ መልኩ ማቅረብ ይችሉ ዘንድ አእምሮዎ ከአገልግሎት ጋር የተቆራኘ ይሁን፡፡ ልብ የሚነኩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለሌሎች ማካፈል እንዲችሉ በቃልዎ ይያዝዋቸው፡፡ በቀጥታ ወደ ዋናው ነጥብ በማምራት የአድማጭዎን ትኩረት ለመሳብና ጌታ በተጠቀመበት መንገድ ለማስተማር ጥረት ያድርጉ፡፡--Review and Herald, July 26, 1887.ChSAmh 197.2

    መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጡትን ቃላት እንዳሉ በማቅረብ ብቻ ታላቅ ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ እያንዳንዱ ደጃፍ ይዘው በመሄድና በግልጽ የቀረበውን ልእክት ወደ እያንዳንዱ ሕሊና የማድረስ ተነሳሽነት በማሳየት አዳኙ ባዘዘው መሰረት “መጻሕፍትን” ይመርምሩ፡፡ መለኮታዊውን ዕውቀት ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ እንዳለ ሊወሰድ እንደሚገባ በጥብቅ ያስገንዝቡ፡፡ የብርሐን ጮራ ፈንጥቆ ነፍሳት እያንዳንዱን የከበረ ጨረር በደስታ ሲቀበሉ ያለ ፍርሐት ለውጤቶቹታማኝ ይሆናሉ፡፡— Testimonies, vol, 5, p. 388. ChSAmh 197.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents