Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ብርቱ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ስህተት

    ነፍሳትን የማዳኑ ሥራ በወንጌል አገልግሎት ላይ ብቻ መተማመን ያደርጋል ብሎ መገመት ብርቱ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ስህተት ነው፡፡ የወይን ተክሉ ጌታ የነፍሳትን ሸክም ያኖረበት ትሑቱና ቅዱሱ አማኝ ከፍ ያለ ኃላፊነት በተሰጣቸው ወገኖች ሊበረታታ ይገባል፡፡ የአዳኙ ተልዕኮ በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ የመሰጠቱን እውነታ በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በመሪነት የተሰየሙ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እጅ ተጭኖባቸው ወደ አገልግሎት ያልገቡ አያሌዎችን እግዚአብሔር ወደ ወይን ተክሉ ያሰማራቸዋል፡፡-The Acts of the Apostles, p. 10.ChSAmh 95.2

    የወንጌል አገልጋዩ ማንኛውንም ሸክም በራሱ ማከናወን ይኖርበታል የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ መሥራት ከሚገባው በላይ በመሥራቱ የዛለውና መላ እርሱነቱ ከጥቅም ውጪ የሆነው አገልጋይ በእግዚአብሔር እቅድ መሰረት ሸክሙን የሚጋራው ሲኖር ምድራዊ ሕይወቱ ይረዝማል፣ በአጭር ከመቀጨትም ይተርፋል፡፡ሠራተኞች የክርስቶስን አካሄድ ተከትለው በመሥራት ሁሉም ሸክም እንዲጋራ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን መሰጠት ይኖበታል፡፡-- Testi monies, vol, 6, p. 435ChSAmh 95.3

    የወንጌል ሠራተኛው መልእክት መስጠት፣ ማገልገልና መጸለይ የእርሱ ተግባር ብቻ አድርጎ መውሰድ የለበትም፡፡ ይልቁንም በያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያንእገዛ ሊሰጡ የሚችሉ ወገኖችን ማሰልጠን ይኖርበታል፡፡ ለየት ያሉትመርኀ ግብሮችን እንዲመሩና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዲያነቡ ሲበረታቱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊቶች እየተጠቀሙ እግረ መንገዳቸውን የአገልጋይነት ሥልጠና መውሰድ ይችላሉ--Gospel Workers, p. 197.ChSAmh 96.1

    የወንጌል አገልጋዮች የቤተ hርስቲያን ሥራዎችን በመውሰድ ራሳቸውን የሚያደከሙና ሌሎችን ከአገልግሎት የሚያግዱ ተግባራት መፈጸም የለባቸውም፡፡ አባላት ለቤተ ከርስቲያናቸውም ሆነ ለማኅበረሰባቸው እንዴት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ሊያስተምሯቸው ይገባል፡፡-- Historical Sketches, p. 291.ChSAmh 96.2

    እምነታችንን አማኝ ላልሆኑ ለማቅረብ የሚያስችለን ጥረት በሚደረግበት ወቅት ብዙውን ጊዜ የቤተ hርስቲያን አባላት የአገልግሎቱ አካል በመሆናቸው ደስተኞች ያልሆኑ ይመስል ሸከሙን ሁሉ በአገልጋዩ ላይ ትተው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ፡፡ በዚህ የተነሳ መልካም ክህሎት ያላቸው ሠራተኞቻችን የሥራ አፈጻጸም አልፎ አልፎ አነስተኛ ሲሆን ይስተዋላል፡፡- Gospel Workers, p. 196.ChSAmh 96.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents