Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አንጸባራቂዎቹ ከዋhብት

    በእያንዳንዱ አገር ከተሰራጩ የምድር ነዋሪዎች መካከል ጉልበቶቻቸውን ለበዓል ያላንበረከኩ ወገኖች አሉ፡፡ የሰማይ ከዋከብት አመሻሽ ላይ ጥርት ብለው እንደሚታዩ ሁሉ ምድር በድቅድቅ ጨለማ ተሸፍና በሰዎች ላይ ከባድ ጽልመት ሲወድቅእነዚህ ታማኞች ያበራሉ፡፡ እግዚአብሔር--ባዕድ አምልኮ በሚዘወተርባት አፍሪካ፣ የካቶሊክ እምነት በተንሰራፋበት አውሮፓና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በቻይና፣ በሕንድ፣ በተለያዩ ደሴቶችና በሁሉም የምድር ማዕዘናት በማብራትየሚለውጠውን ሕጉን የመታዘዝ ኃይል በክvደትና በጨለማ ለተዋጠው ዓለም በግልጽ የሚያሳዩ እንደ ሰማይ ከዋክብት የሚያንጸባርቁ የተመረጡ ወገኖችን አዘጋጅቶአል፡፡ እነዚህ ወገኖች በአሁኗ ሰዓትና ደቂቃ እንኳ በተለያዩ አገሮች፣ ቋንቋዎችና ሕዝቦች መሃል ይገኛሉ፡፡ ሰይጣን አንድም ሳይቀር ኃይሉን አቀናጅቶ “ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሃብታሞችና ድኾች፣ ጌቶችና ባሮች ሁሉ” ለሐሰተኛው ቀን ታማኝነታቸውን በማሳየት እጅግ የከፋውን የhህደት ተግባር በመፈጸም ምልክቱን በሚቀበሉበት ሰዓት “ንጹሃንና ያለ _ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች... እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ” ያበራሉ፡፡ ጨለማው ድቅድቅ በሆነ ቁጥር አብልጠው ያንጸባርቃሉ፡፡— Prophets and Kings, pp. 188, 189.ChSAmh 227.2

    የስደት ማዕበል በሚደርስብን ወቅት እውነተኛዋ መርከብ የእውነተኛውን እረኛ ድምጽ ትሰማለች፡፡ የጠፉትን ለማዳን የሚያስችሉ ራስን የመካድ ጥረቶች ገቢራዊ በሚሆኑበት ወቅት ከመንጋው ተበትነው የነበሩ ብዙዎች ታላቁን እረኛ ለመከተል ተመልሰው ይመጣሉ፡፡ Australian Signs of the Times, Supplement, Jan. 26, 1903.ChSAmh 228.1

    መለኮታዊ ከለላ ወዝግቡ የማያባራ ቢሆንም ማንም ብቻውን እንዲታገል አልተተወም፡፡ በእግዚአብሔር ፊት በትህትና የሚራመዱትን መላእክት ይረዷቸዋል ይጠብቋቸዋልም፡፡ ጌታችን በእርሱ የሚታመነውን ማንኛውንም ሰው አይተውም፡፡ ልጆቹ ከክፉ ከለላ ያገኙ ዘንድ በዙሪያው ሲሰባሰቡ ከጠላት የሚጠበቁባቸውን ትእዛዛት በሐዘኔታና በፍቅር ከፍ ያደርግላቸዋል፡፡ እንዳትነኳቸው፣ የእኔ ናቸው፣ በእጆቼ መዳፎች ቀርጫቸዋለሁይላል፡፡--Prophets and Kings, p. 571.ChSAmh 228.2

    ስለ ጽድቅ ሥቃይ ለሚደርስባቸው ሰማይ ቅርብ ነው፡፡ ክርስቶስ ፍላጎቱን ከታማኝ ሕዝቡ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰሩበተቀደሰ መልእክተኛው ላይ ሥቃይ ሲደርስ በእርሱም ላይ ይደርሳል፣ የእርሱን የተመረጡ ሕዝቦች የሚነካም እርሱን ይነካል፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አምላካዊውን አብሮነት በሁሉም ሁናቴዎች እንዲጠቀሙ የሚያስችለው፤ አካላዊውን ጉዳት ወይም ሥቃይ ለማዳን ቅርብ የሆነው ኃይል፤ ከላቀ የክፉ ተንኮል ለማዳንም የዛኑ ያህል የቀረበ ነው፡፡--Prophets and Kings, p. 545. ChSAmh 228.3

    አንዳንዴ ጌታ በቤተ ክርስቲያኑ ላይ የተጋረጠውን አደጋና በጠላቶቿ የሚሰነዘርባትን መቁሰል የዘነጋ ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር ግን አልረሳትም፡፡ በዚህ ምድር የቤተ hርስቲያኑን ያህል ለእርሱ የከበረ ነገር የለም፡፡ ምድራዊ አቋምና መመሪያዎች ስምና ዝናዋን ያጠፉ ዘንድ ፈቃዱ አይደለም፡፡ሕዝቦቹ በሰይጣን ማሳሳቻ እንዲሸነፉ አይተዋቸውም፡፡ እርሱን በተሳሳተ መንገድ ለመወከል የሚባዝኑ ሐሰተኞችን የሚቀጣ ሲሆን ልባዊ ንስሐ ለሚገቡ--ደግና ርኅሩኅ ነው፡፡--Prophets and Kings, p. 590. ChSAmh 229.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents