Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወደፊት ሂዱ

    የክርስትና ሕይወት ብዙውን ጊዜ በአደጋዎች ይከበባል፤ መንፈሳዊው ሥራም ለማከናወን አስቸጋሪ የሚመስሉ ከባድና አስቸጋሪ ሁኔታዎችይገጥመዋል፡፡ ከፊት ለፊት ሊመጣ ስለሚችል ውድመትና ጥፋት፤ ከኋላ ስለሚከተል እስራትና ሞት--በምናባችን ብንስልም ወደ ፊት ሂዱ የሚለው የእግዚአብሔር ድምፅ በጉልህ ይሰማል፡፡ ዐይኖቻችን ጨለማውን አልፈው መመልከት ባይችሉም እንኳ ትእዛዙን እንከተል፡፡ ግስጋሴያችንን የሚደናቅፉ መሰናክሎች የሚያመነታና የሚጠራጠር መንፈስ ካላቸው ሰዎች መወገድ አይችሉም፡፡ ከውድቀት ወይም ከሽንፈት ይታደገናል በሚል እሳቤ እያንዳንዱ ጥርጣሬ እኪወገድ መታዘዛቸውን የሚያዘገዩ እስከመጨረሻው ሳይታዘዙ ይቀራሉ፡፡ እምነት ከአስቸጋሪ ሁናቴዎች ባሻገር በመመልከት፤ የማይታይ የሚስለውንይኸውም ሁሉን ቻይ የሆነውን ጨብጦ ስለሚይዝ ግራ መጋባት አይኖርም፡፡ እምነት በማንኛውም ድንገተኛ ወቅት የክርስቶስን እጅ ጨብጠን የምንዝበት መሣሪያ ነው፡፡ Gospel Workers, p. 262. ChSAmh 152.1

    ጽንሰ ሐሳቦቻችን በድምሩ ሲታዩ እጅግ ጠባብ ናቸው፡፡ አምላካዊውን ብርሐን የመፈንጠቅ ሥራ ይዘን ያለማሰለስ ወደፊት እንድንገሰግስ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ ወደ ሕዝቦች ለመድረስ የሚያስችሉንን የተሻሻሉ ስልቶች ማጥናት ይኖርብናል፡፡ የመርከቢቱ አዛዥ የሆነው ኃያሉ የሰራዊት ጌታ “ወደ ፊት ሂዱ” ሲለን በእምነት እንስማው፡፡ እግዚአብሔር አይተወንም—አሁኑኑ ወደ ተግባር እንግባ፡፡ እኛ በእምነት የድርሻችንን ስንወጣ እርሱም የበኩሉን ይሠራል፡፡ በውነት ጎዳና ለረጅም ዘመን የተመላለሳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንድትሠሩ የጠራችሁበትን ሥራ አልሠራችሁም፡፡ ለነፍሳት ያላችሁ ፍቅር የት አለ? Historical Sketches, pp. 289, 290.ChSAmh 152.2

    ነፍሳትን ማዳን ለክርስቶስ ብርቱ ደስታ ያጎናጽፋል፡፡ ይህን ማድረግ የእርስዎ ሥራና ደስታ ይሁን፡፡ ስለ ክርስቶስ ብለው እያንዳንዱን ተግባር ሲያከናውኑና ማንኛውንም መሥዋዕትነት ሲከፍሉ ያለማሰለስ ከጎንዎ የማይለይ ረዳትዎ ይሆናል፡፡ የአገልግሎት ጥሪ ወደ ሚደመጥበት ስፍራ በቀጥታ ያምሩ አንዳችም አስቸጋሪ የሚመስል ነገር ያስጓጉልዎ፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጦትን ኃላፊነቶች ተሸክመው ወደ ፊት ሲያመሩ ምናልባት አንዳንዴ የሸክሙ ክብደት ቢሰማዎ “ወንድሜ አንድም ቀንበር ሳይሸከም ያለ ሥራ የተቀመጠው ለምንድን ነው?” ብለው አይጠይቁ፡፡ በቅርብዎ ያለውን ሥራ በጥንቃቄና በአግባቡ ይሥሩ እንጂ የሰዎችን ምስጋና አይሹ፡፡ የጌታ እንደመሆንዎ ለጌታ ይሥሩ፡፡Southern Watchman, April 2, 1903.ChSAmh 152.3

    ወደፊትና ወደ ላይ የሚዘረጋው የእግዚአብሔር ሕዝቦች የጉዞ አቅጣጫ ወደ ድል የሚያመራ ሊሆን ይገባል፡፡ ከኢያሱ የበለጠው አዛዥ የእስራኤልን ሠራዊት ይመራል፡፡ “እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ነገር ግን አይዞአችሁ፣ እኔ ዓለምን አሸንፌአለሁ” በማለት የሚያበረታታን የደኅንነት አዛዥ እነሆ በመካከላችን ነው:: በእርግጥ እርሱ ወደ ድል ይመራናል፡፡ በማንኛውም ጊዜ ይህን ሊያደርግልን እንደሚችል እግዚአብሔር ቃል ገብቶልናል፡፡ ሕዝቡ በሥራው ላይ ተሳታፊ ሲሆን በእነርሱ አማካይነት መፈጸም ይቻለዋል፡፡ Testimonies, vol. 2, p. 122.ChSAmh 153.1

    በክርስቶስ መንፈስ ደስ የማንሰኘውና አድናቆታችንን የማንገልጸው ለምንድን ነው? በሥቃይ ውስጥ ያለው ዓለም አሳፋሪና የከፋ ሁኔታ እምብዛም ውስጣችንን የማይነካው ለምንድን ነው? ክርስቶስ በሚደፋልን አክሊል ላይ ተጨማሪ ከዋክብቶች ጫን ስለምንችልበት ከፍ ስላለው ልዩ መብትና ጥቅም አስበን እናውቃለን? የሰይጣንን ሰንሰለት በጥሰን በማትረፍ በእግዚአብሔር መንግሥት ደኅንነት ስለሚያገኘው ነፍስ በጥልቅ አስተውለናል? ቤተ ክርስቲያን የወንጌል አካል የሆነውን ወቅታዊ እውነት ለዓለም የማስተላለፍ ግዴታ እንዳለባት መገንዘብ ይኖርባታል፡፡ ከትንቢተ ዘካርያስ መጽሐፍ ሦስተኛውንና አራተኛውን ምዕራፍ እንድታነቡ እለምናችኋለሁ፡፡ እነዚህ ምዕራፎች በአግባቡ መስተዋል ከቻሉና ተቀባይነት ካገኙ ጽድቅን ለሚራቡና ለሚጠሙ የሚበጁ ሥራዎች መሠራት ይችላሉ፡፡ ይህም ቤተ hርስቲያን ወደፊትና ወደላይ በመዘርጋት የምትሠራው ሥራ እንደተሰጣት ማሳያ ነው::Testimonies, vol. 6, p. 296. ChSAmh 153.2

    አብላጫዎቹ የምድራችን ሕዝቦች ታማኝነታቸውን ለጠላት ቢያስረክቡም እኛ ግን አልተታለልንም፡፡ ምንም እንኳ ሰይጣን የብዙዎችን ልብ ቢያሸፍትም ነገር ግን ክርስቶስ በሰማያዊው ቤተ መቅደስና በምድር ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በመጨረሻዎቹ ቀናት እርክስናና ምግባረ ብልሹነት እንደሚንሰራፋ ይነግረናል፡፡ የትንቢቱን ፍጻሜ መመልከታችን በመጨረሻ ድል አድራጊ በሚሆነው በክርስቶስ መንግሥት ላይ የሚኖረን እምነት ጠንካራ ሊሆንና የተመደበልንን ሥራ ለመሥራት በታደሰ ወኔ ወደ ፊት እንድናመራ ሊያደርገን ይገባል፡፡ Gospel Workers, pp. 26, 27.ChSAmh 154.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents