Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ጥሪ ለክርስቲያን ቤተሰቦች

    የወንጌላዊ ቤተሰቦች ወደ ጠፉ ስፍራዎች በማምራት ኑሮአቸውን በዚያ መቀለስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በግብርና ሙያ የሚተዳደሩ፣ በቂ የመዋዕለ ንዋይ አቅም ያላቸው፣ በግንባታ ሥራና በሌሎች ሙያ ነክና የዕደ ጥበብ ዘርፎች የተሰማሩችላ ወደ ተባሉ ስፍራዎች በማምራት ከምድሪቱ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም እያጎለበቱና የጎጆ ኢንዱስትሪዎችን እያቋቋሙ ለመኖሪያ የሚሆን ጠነኛ መኖሪያ ቀልሰው ለጎረቤቶቻቸው በጎ ተግባራት ያከናውኑ፡፡The Ministry of Healing p. 194.ChSAmh 253.2

    የክርስቲያን ቤተሰቦች በጨለማና በስvተት ወዳሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች በመሄድ ለጌታ በብልሀት ተግተው እንዲሠሩ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡ ለዚህ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ራስን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ የግድ ይሆናል፡፡ ብዙዎች እያንዳንዱ መሰናክል እስኪወገድ መጠባበቅን በመምረጣቸው ነፍሳት ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር እየሞቱ ነው፡፡ ብዙዎች—እጅግ ብዙዎች ዓለማዊ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሳይንሳዊ የምርምር ሥራ ለመሥራት ሲሉ ወረርሽኝና በሽታ በተንሰራፋበቸው አደገኛ አካባቢዎች ለመሄድ በመድፈር አስቸጋሪውን ሁኔታ ይጋፈጣሉ፡፡ ስለ አዳኙ ሲሉ ይህን እውነት ለሌሎች ለመንገር ፈቃደኞች የሆኑ ወገኖች የት ነው ያሉት? በጨለማ ለሚገኙት ነፍሳት አዳኙን በማመላከት ወንጌል ሊነገርበት ወደ ሚገባው ስፍራ የሚንቀሳቀሱ ወንዶችና ሴቶች የት ናቸው?-Testimonies, vol. 9, p. 33.ChSAmh 254.1

    ነፍሳትን በማዳን ሥራ በግል ተሳታፊ በመሆን በባተሌ እጆቻቸውና አእምሮአቸው ያለማሰለስ አድካሚውን ሥራ የሚሠሩ፣ ለሥራው ስኬት አዳዲስ ዘዴና ብልሃቶችን የሚነድፉ መላው የቤተሰብ አባል የወንጌል ሠራተኛ የሆነባቸው ቤተሰቦች አሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 40. ChSAmh 254.2

    ቤተሰቦች መንፈሳዊ ጽልመት በሰፈነባቸው ሕዝቦችና የምድር ክፍሎች በመኖር የክርስቶስ ህይወት ብርሃን ከእነርሱ ወደ ሌሎች እንዲያንጻባርቅ የሚፈቅዱ ከሆነ ታላቅ hንውን መገኘት ይችላሉ፡፡ ሥራው ተስፋፍቶ የሰበካ ቢሮውን የገንዘብ ድጋፍ የሚፈልግበት ደረጃ ላይ እስኪደርስ በፋይናንስ ዙሪያ ትኩረት ሳያደርጉ ሥራቸውን በተረጋጋና ከግርግር በራቀ አካሄድ ይጀምሩ፡፡— Testimonies, vol. 6, p. 442.ChSAmh 254.3