Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአውራው ጎዳና ተወካዮች

    ለወቅታዊው ጥሪ ምላሽ ሰጥተው ወደ ጌታ አገልግሎት የተቀላቀሉ ሠራተኞች የአምላካዊን አሠራር ዘዴ በጥልቅ ማጥናት ይችላሉ፡፡ አዳኙ በምድራዊ የአገልግሎት ጎዳና ያገኛቸው የነበሩትን መልካም ዕድሎች ጥቅም ላይ ያውል ነበር፡፡ የሱስ በአገልግሎቱ ሲያልፍና ሲያገድም በቅፍርናሆም አጭር ቆይታ ያደርግ ስለነበር “የራሱ ከተማ በሚል ትታወቅ ነበር፡፡ ይህች ከተማ የአዳኙ አገልግሎት ማዕከል ለመሆን የሚያስችላት ምቹነት ነበራት፡፡ ቅፍርናሆም ከደማስቆ ወደ የሩሳሌም፣ ግብጽና የሜዲቴራኒያን ባሕር አቅጣጫ በሚያመራው አውራ መንገድ ላይ የምትገኝ ከተማ እንደመሆኗ መልክአ ምድራዊ አቀማጧ ለአገልግሎት ብርቱ ጠቀሜታ ነበረው፡፡ የተለያዩ አገሮች ሕዝቦች በተለያዩ ተግባራት ይህቺን ከተማ አቋርጠው ያልፉ ወይም አጭር ቆይታ ያደርጉባት ነበር፡፡ በመሆኑም የሱስ የተለያዩ lገር ሕዝቦችን፣ ባለ ሥልጣኖችን፣ ታላላቅ ሰዎችንና ሐብታሞችን እንዲሁም ድኾችንና ምስኪኖችን በዚህች ከተማ መገናኘት በመቻሉ ትምህርቱ ወደ ሌሎች አገሮችና ቤተሰቦች በቀላሉ የመሰራጨትና የመስፋፋት ዕድል ያገኝ ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን መመርመር አስደሳችና ማራኪ ስሜት በመፍጠር የብዙዎች ትኩረት ወደ አዳኙ እንዲያነጣጥርና ተልዕኮው ለዓለም እንዲቀርብ አስችሎአል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 121. ChSAmh 174.2

    በቱሪስት መዳረሻነታቸው ከፍተኛ ዝና ያተረፉ ከተሞች ጎዳናዎች ላይ የአያሌዎችን ትኩረት መሳብ የሚችሉ አገልጋዮችና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ይኑሩ፡፡ እነዚህ አገልጋዮች ለዚህ ዘመን ተስማሚ የሆነውን መልእክት ለማቅረብ የሚያስችሏቸውን ዕድሎች እየፈተሹ ሁናቴዎች ሲመቻቹ የወንጌል ስብሰባዎችን ያድርጉ፡፡ ያገኟቸውን ዕድሎች ተጠቅመው መልእክታቸውን ለሕዝቦች ለማቅረብ ፈጣን ይሁኑ፡፡ ChSAmh 175.1

    በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልተው እንደ መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” (ማቴ.3፡2) እያሉ ሕዝቡን ይቀላቀሉ፡፡ ጆሮ ያላቸው እውነትን ይሰሙ ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽና በኃይል ሊቀርብ ይገባል፡፡ ወቅታዊው የወንጌል እውነት ጎዳና እና አደባባይ ላይ ሲወጣ ተቀባይነት የሚያገኘው በጥቂቶች ብቻ አይሆንም፡፡ ይልቁንም ጥቂቶቹ ወደ መጡበት ሐዝቦችና ለዓለም የሚያሰራጩት ይሆናል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 122. ChSAmh 175.2

    ከትንቢት መንፈስ ሥራዎች መካከል “Ministry of Healing” እና “Christ’s Object lessons” በመባል የሚታወቁት መጻሕፍት በተለይ የቱሪስት መዳራሻ ለሆኑ ስፍራዎች የበለጠ አገልግሎት እንዲሰጡ ሆነው የተዘጋጁ እንደመሆናቸው የእነዚህን ሥራዎች ቅጂ የተረጋጋ መንፈስና የማንበብ ዝንባሌ ወዳላቸው ወገኖች የሚደርሱባቸው መንገዶች በተቻለ ሊመቻቹ ይገባል፡:--Testimonies, vol. 9, p. 85. ChSAmh 175.3

    የጤና ምግቦችን የሚያዘጋጁ ምግብ ቤቶችና የህክምና መስጫ ጣቢያዎች ሊቋቋሙ ይገባል፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹን ተቋማት ለመመስረትየምናደርጋቸው ጥረቶች ታላላቅ የባሕር ዳርቻ መዝናኛዎችን ጭምር ሊያካትቱ ይገባል፡፡ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ” የሚል የመጥምቁ ዮሐንስ ድምፅ በምድረበዳ እንደተሰማ ሁሉ የጌታ መልእክተኞችም ድምጽ ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻ በሆኑ የባሐር ዳርቻዎችና መዝናኛዎች ሊሰሙ ይገባል፡፡—Testimonies, vol. 7, pp. 55, 56.ChSAmh 176.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents