Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ጀማሪ የhርስትና አገልግሎት ሠራተኞችን ማበረታታት

    እግዚአብሔርን ደስተኛ ሆነው በጥቃቅን ነገሮች የሚያገለግሉ ከሁሉም የላቁት ስኬታማ ሠራተኞች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ፍጹም የሆነውን ንድፍ ለማግኘት የሚያስችለውን የሽመና ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 15.ChSAmh 136.2

    ሥራችንን ከዘላለማዊው ብርሃን አኳያ በመመልከት የየዕለት የአምልኮ ተግባራችን ጠቀሜታ ያለማቋረጥ እየጨመረና እያደı እንዲሄድ ማድረግ ይኖርብናል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 150.ChSAmh 136.3

    ጌታ በታላቁ እቅዱ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሆን ቦታ አለው፡፡ ለአገልግሎት የማያስፈልጉ መክሊቶች አልተሰጡም፡፡Testimonies, vol. 9, p. 37.ChSAmh 137.1

    እያንዳንዱ ሰው በሰማያዊው ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ቦታ አለው፡፡ ማንኛውም ሰው ለነፍሳት ደኅንነት ከክርስቶስ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እንዲሠራ ተጠርቶአል፡፡ በሰማይ የተዘጋጀልን መኖሪያ በምድር ለእግዚአብሔር እንድንሠራ ከተሰጠን የተለየ አገልግሎት በላቀ የተረጋገጠ አይደለም፡፡--Christ’s Object lessons, pp. 326, 327. ChSAmh 137.2

    ለእያንዳንዱ እቅድ ያለውየጌታ ዓይኖች በአባላቱ ላይ ናቸው፡፡ Testimonies, vol. 6, P. 12.ChSAmh 137.3

    በሥራው ሁሉም የድርሻቸውን አንድ ነገር ማድረግ ይችላሉ፡፡ ማናቸውም በቅንነትና ከራስ ወዳድነት በጸዳ መንፈስ ለነፍሳት ደኅንነት ካልሠሩ በቀር ከጥፋተኝነት ሊመልጡ አይችሉም፡፡- Testimonies, vol. 5, p. 395. ChSAmh 137.4

    በእርስዎ መከናወን የሚገባው ተግባር ለሌላ ሊውል አይችልም፡፡ የእርስዎን ሥራ እርስዎ እንጂ ሌላ ማንም መሥራት አይችልም፡፡ ብርሃንዎ እንዳይበራ የሚገቱ ከሆነ በእርስዎ ቸልተኝነት በጨለማ ውስጥ የሚተው ወገን ይኖራል፡፡— Testimonies, vol. 5, p. 464.ChSAmh 137.5

    ለእግዚአብሔር ጥሪ በታዛዥነት ምላሽ የሚሰጠው ሠራተኛ መለኮታዊ ድጋፍ ለመቀበል እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ታላቅ የሆነውንና ቅዱሱን ላፊነት መቀበል በራሱ የጸባይ ዕድገት ማሳየት ነው፡፡ ይህ ኃላፊነት አእምሮና ልብን እያጠነከረና እያነጻ ከፍ ያለው የአዕምሮና የመንፈስ ኃይል ወደ ተግባር እንዲገባ ጥሪ ያርባል፡፡ ደካማው ሰው በእግዚአብሔር ኃይል ላይ እምነት ሲኖረው እንዴት እንደሚበረታ፣ የብርቱ ጥረት ባለቤት ሲሆንና ከፍተኛ ውጤት የሚያስገኝ ፍሬ ሲያፈራ መመልከት ድንቅ ነገር ነው፡፡ ረጅሙን ጉዞ ፍጹም በሆነ ትህትና በጥቂት ዕውቀት በመጀመር የበለጠውን ለማወቅ እየተጋ የሚያውቀውን ለሌሎች የሚያካፍል፤ ያሻውን ያህል ሰማያዊ ሀብት ያገኛል፡፡ አንድ ሰው ለነፍሳት በሚኖረው የተለየ ፍቅር የእግዚአብሔርን ቃል አብልጦ ለሌሎች ለማካፈል ጥረት ሲያደርግ አምላካዊው ቃል ይበልጥ ግልጽና በቀላሉ የሚስተዋል ይሆንለታል፡፡ ዕውቀታችንን ይበልጥ ጥቅም ላይ በማዋል ያለንን ጉልበት ስንለማመድ የላቀውን ዕውቀትና ኃይል እናገናለን፡፡- Christ’s Object Lessons, p. 354. ChSAmh 137.6

    እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር ብሎም ለነፍሳት ደኅንነት ይሥራ እንጂ የሆነ ሰው መጥቶ የሚሠራውን እስኪሰጠው እጆቹን አጣጥፎ አይቀመጥ፡፡ የሚሠራውን ሥራ የሚሰጠው ያ የሆነ ሰው” በብዙ ኃላፊነቶች የተጣበበ ሊሆን ስለሚችል የእርሱን መመሪያ መጠበቅ ጊዜው ያለ ሥራ እንዲባክን ሊያደርግ ይችላል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሐድሶ ለማምጣት የሚያስችል ጥበብ የሚሰጥዎ እግዚአብሔር ጥሪ እያደረገልዎ ይገኛል “ልጄ ሆይ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ” “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታደንድኑ” (ዕብ. 3፡7-8)፡፡ እግዚአብሔር ለጥሪው በመግቢያነት የተጠቀመው “ልጄ” የተሰኘውን የከበረ የፍቅር ቃል ነው፡፡ እንዴት ደግ፣ ርኅሩኅና አቸኳይ መልእክት ነው! ይህ የፍቅር ግብዣው በውስጡ ትእዛዝ መያዙን ልብ ይሏል፡፡Counsels to Teachers, p. 419.ChSAmh 138.1

    ክፉውን ለመቋቋም የሚያስችል ወደር የለሽ ጥንካሬ ማግኘት የምንችለው በሙሉ ይላችን ስናገለግል ነው፡፡--The Acts of the Apostles, p. 105.ChSAmh 138.2

    እያንዳንዱ ፍትሐዊነት፣ ይቅር ባይነትና ርኅሩኅ ድርጊት ሰማይን ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ ዜማ ነው፡፡-Review and Herald, Aug. 16, 1881,ChSAmh 138.3

    የክርስቶስ መንፈስ የወንጌላዊ መንፈስ ነው፡፡ ተሐድሶ ያገኘው ልብ ተቀዳሚ ምኞት ሌሎችን ወደ አዳኙ ማምጣት ነው፡፡--The Great Controversy, p. 70.ChSAmh 138.4

    በጸጋ ለማደግ ብቸኛው መንገድ ክርስቶስ ለእኛ ለመሥራት ደስ የተሰኘበትን ሥራ መሥራት ነው፡፡Review and Herald, June 7, 1887. ChSAmh 139.1

    ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመውጣት ታላላቅ ጊዜያቶችን ወይም ያልተለመዱ አስደናቂ ችሎታዎችን እስኪያገኙ መጠበቅ የለቦትም፡፡ Steps to Christ, p. 83.ChSAmh 139.2

    አንድ ሰው የተማረ ወይም ያልተማረ ቢሆን ለማኅበረሰቡ በረከት፣ ለሐይወቱ ደግሞ ክንውን የሚያገኘው መላውን ኃይሉንና ጉልበቱን ለእግዚአብሔር አገልግሎትና ለባልጀራው ደኅንነት ሲያውል ነው፡፡-Southern Watchman, April 2, 1903.ChSAmh 139.3

    እጅግ በጣም ጥሩ ሥራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ብቃት እግዚአብሔር የሰጣቸው ብዙዎች በትንሹ ስለሚሞክሩ ጥቂት ብቻ ይሠራሉ፡፡Christ’s Object lessons, p. 331. ChSAmh 139.4

    ለአንድ መቶ ነፍሳት መስክረው የዘጠና ዘጠኙ ባይሳካና አንዱን ብቻ ከጥፋት ቢያድኑ፤ እነሆ ለአዳኙ ታላቅና የከበረ ሥራ ሠርተዋል፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 132. ChSAmh 139.5

    በእግዚአብሔርና በእያንዳንዱ ነፍስ መካከል ያለው ግንኙነት-ተወዳጁን ልጁን ለመስጠት ከዚያ ግለሰብ በቀር በዚህ ምድር የእርሱን ጥበቃና ጥንቃቄ የሚጋራ ሌላ ነፍስ የሌለ ያህል በዓይነቱ ልዩና የተሟላ ነው፡፡Steps to Christ, p. 100. ChSAmh 139.6

    ድካም ቢኖርዎትም መክሊትዎን የተቀደሰ ስጦታ አድርገው ለአገልግሎት ቢያቀርቡ፤ ሁሉን የሚመለከተውና የሚያስተውለው ጌታ ይጠቀምቦታል፡፡ ንቁና ቅን አገልግሎት ደካማውን በማጠንከር የአምላካዊው የከበረ _ የፍቅር መልእክት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ የጌታ በእገልግሎታችን ደስ መሰኘት የብርታታችን መሰረት ነው፡፡ ታማኝ ከሆኑ፤ በዚህ ምድር የአምላካዊው ሰላም--በመጪው ሕይወት ደግሞ የጌታ ደስታ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ Testimonies, vol. 8, p. 34.ChSAmh 139.7

    አነስተኛ መክሊት ያላቸው cዎች ልቦቻቸውን ከአምላካዊው ፍቅር ጋር በታማኝነት ካስተሳሰሩ ለክርስቶስ አያሌ ነፍሳትን መማረክ ይችላሉ፡፡ ሐርላም ኤጅ በመባል ይታወቁ የነበሩት ግለሰብ ውሱን ትምህርትና ዝቅተኛ የመካኒክነት ችሎታ ነበራቸው፡፡ ነገር ግን አምላካዊውን መልእክት ለሌሎች የማሰራጨቱን ሥራ ዋና ተግባራቸው አድርገው በመውሰዳቸው ጥረታቸው ብርቱ ፍሬ አፍርቶ የስኬትን አክሊል እንዲደፉ አስቻላቸው፡፡ ሐራላም ከሰዎች ጋር በግል በመገናኘትና በጸሎት በመትጋት ለባልንጀሮቻቸው ደኅንነት አጥብቀው ሠሩ፡፡ የጸሎት ስብሰባዎችን በመጀመር፣ በቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርጎ ግብሮችን በማዋቀርና መንፈሳዊ በራሪ ጽሑፎችን በማደል ያላሰለc አገልግሎት የሰጡት እኚህ ግለሰብ ትንፋሻቸው ሊቋረጥ ጥቂት ሲቀረው፤ በገጽታቸው ላይ ዘላለማዊ ጥላ እየተስተዋለ የሚከተለውን መናገር ችለው ነበር “የሠራሁት ሁሉ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ እንጂ በእኔ ችሎታ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ከአንድ መቶ የሚበልጡ ነፍሳት ወደ ጌታ እንዲመጡ እግዚአብሔር እኔን በግል በመሣሪያነት ለመጠቀሙ ምስክር ነኝ”-- Testimonies, vol. 5, pp. 307, 308. ChSAmh 140.1

    ይህ ዓለም የክርስቲያኖች ገነት ሳይሆን ኃጢአት ከማያውቁት የተቀደሰው ሰማይ መላእክት ጋር በብቃትና በሕብረት በመሥራት አምላካዊ ጥገና የሚካሄድበት ስፍራው ነው፡፡--Testimonies, vol. 2, P 187. ChSAmh 140.2

    ትሑታኑና ምስኪኖቹ የየሱስ ደቀ መዛሙርት ለሌሎች በረከት መሆን ይችላሉ፡፡ ምናልባት አንዳችም የተለየ መልካም ነገር እያደረጉ እንደሆነ በቅጡ ልብ ሳይሉና በስፋትም ሆነ በጥልቀት በሰዎች ላይ የሚተዉአቸው ተጽእኖ አሳዳሪ የበረከት ሞገዶች እስከ መጨረሻው የሽልማት ቀን ሳይታወቃቸው ሊዘልቁ ይችላሉ፡፡ እያደረጉ ያለው ታላቅ ነገር ላይሰማቸው ወይም ላይታወቃቸው ይችላል፡፡ ስለ ስኬት እያሰላሰሉ ራሳቸውን ሸብርና ስጋት ውስጥ እንዲከቱ አልተየቁም፡፡ ይልቁንም በጸጥታ ወደፊት በመራመድ ከአምላካዊው በጎነት የተመደበላቸውን ሥራ በታማኝነት ሲሠሩ ሕይወታቸው ከንቱ አይሆንም፡፡ የገዛ ነፍሶቻቸው አብልጠው ክርስቶስን እየመሰሉ ያድጋሉ፡፡ በምድራዊው ሕይወታቸው ከእግዚአብሔር ጋር በመሥራት ከፍ ላለው አገልግሎት ብቁ ሆነው በመገኘታቸው ጥላ ያላጠላበት የሚመጣው ሕይወት ደስታ ተካፋዮች ይሆናሉ፡፡Steps to Christ, p. 83. ChSAmh 140.3

    ራሳቸውን ለክርስቶስ አሳልፈው ቢሰጡም ታላቅ ሥራ ለመሥራት ወይም በአገልግሎት ከፍ ያለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል የሚያስችል ዕድል ያልተመለከቱ lያሌዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት አብልጦ ተቀባይነት ለማግኘት የግድ እንደ ሰማዕት ራስን አሳልፎ መስጠት አይገባም የሚለው አስተሳሰብ ምቾት ይሰጣቸዋል፡፡ በሰማያዊው መዝገብ ስሙ በደማቅ የሚጻፈው በየዕለት አገልግሎቱ ከአደጋና ከሞት ጋር የሚጋፈጠው ወንጌላዊ ላይሆን ይችላል፡፡ ይልቁንም በግል ሕይወቱ ዓላማ መር በሆነ ታማኝነት በየቀኑ ራሱን ለክርስቶስ አሳልፎ የሚሰጥ፣ የአስተሳሰብ ንጽህና የሚያጎለብት፣ ትንኮሳ ሲገጥመው በየዋህነት የሚያልፍ፣ እምነትና ቅድስና የተላበሰና በቤት ሕይወቱ የክርስቶስን ጸባይ የሚወክል-በዓለም የከበረ ዝና ካለው ወንጌላዊ ወይም ሰማዕት ይልቅ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ይሆናል፡፡--Christ’s Object lessons, p. 403. ChSAmh 141.1

    በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ያለው ሥራው የተሠራበት መንፈስ እንጂ የተገኘው የክንውን መጠን ወይም በግልጽ የሚታየው ውጤት አይደለም፡፡ --Christ’s Object Lessons, p. 397. ChSAmh 141.2

    ጌታ ለሥራው ምስጋና የሚቸረው ከፍ ያለ ከንዋኔ በማግኘታችንና አያሌ ነገሮችን ማፍራት በመቻላችን ሳይሆን በጥቂት ነገሮችም ቢሆን ታማኝ በሆናችን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሚዛን የሚደፋው ላቅ ያለውን ውጤት ማስመዝገባችን ሳይሆን ተግባሩን ያከናወንበት መነሳሻ ምክንያታችን ነው፡፡ መሠራት ከቻለው ታላቅ ሥራ በበለጠ ለመልካምነታችንና ለታማኝነታችን ወሮታ ይሰጣል፡፡Testimonies, vol. 2, pp. 510, 511. ChSAmh 141.3

    አነስተኛ የሆኑትን ነገሮች እያለፉ ከፍ ወዳለው ሥራ አያተኩሩ፡፡ አነስተኛውን ሥራ በስኬት ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከፍ ያለውን ሥራ ለመሥራት የሚያደርጉት ሙከራ ሙሉ ለሙሉ ሳይሳካ ይቀርና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ መሠራት የሚኖርበትን ማንኛውንም ሥራ ከመሥራት ወደ ኋላ አይበሉ፡፡ ሐብታም ወይም ደኻ፣ ታላቅ ወይም ትሑት ቢሆኑ--ንቁ አገልግሎት ይሰጡት ዘንድ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብሎታል፡፡ ጉልበትዎን ለአገልግሎት አውለው እጆችዎ የሚሠሩትን ሲያገኙ ተሰጥኦዎም ሆነ መክሊትዎ ያድጋል፡፡ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሎትን በየቀኑ የሚያገኙትን መልካም ዕድል ችላ ባሉ ቁጥር ፍሬ ዐልባ እየሆኑና እየጠወለጉ ይሄዳሉ፡፡ በጌታ የአትክልት ስፍራ አያሌ ፍሬ የማያፈሩ ዛፎች የኖሩበት ምhንያት ይኸው ነው፡፡Testimonies, vol. 9, p. 129.ChSAmh 142.1

    ጌታ እያንዳንዱን ተሰጥኦ ጥቅም ላይ አውለን ለማየት ይመኛል፡፡ ይህን ካደረግን በሥራ ላይ የምናውላቸው ከፍ ያሉ ስጦታዎች ባለቤቶች እንሆናለን፡፡ ያሉንን መክሊቶች በጥቅም ላይ ስናውል ሌሎች ተጨማሪ እንዲኖሩንና እንድናጎለብታቸው አብሮን ይሠራል እንጂ ተአምራዊ በሆነ መንገድ የሚጎድለንን ብቃት አይሰጠንም፡፡ ለጌታ አገልግሎት በሙሉ ልባችንና በጽኑ መሥዋዕትነት ስንሠራ ጉልበታችን እየጨመረ ኃይላችንም እየታደሰ ይሄዳል፡፡Christ’s Object Lessons, pp. 353, 354. ChSAmh 142.2

    የክርስቶስ ልብ ምን መናገር እንዳለባቸው እንኳ ገና ባልገባቸው ትሑታን፣ ጽድቅን በሚራቡና በሚጠሙ ምስኪኖች ደስ ይሰኛል፡፡ ምናልባትም እነርሱ የሚገኙበት ሁናቴ ብዙ አገልጋዮችን ተስፋ ሊያስቆርጥቢችልም እርሱ ግን በደስታ ይቀበላቸዋል፡፡Gospel Workers, p. 37. ChSAmh 142.3

    ለክርስቶስ የምንሠራው ሥራ ምናልባትም ከመኖሪያ ቤታችን ቅጥር እጅግ ያልራቀ ሊሆን ስለሚችል ለአገልግሎት ወደ ባዕድ ምድር መሄድ ላያስፈልገን ይችላል፡፡ አገልግሎት የምንሰጠው በቤታችን ዙሪያ፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በምናውቃቸው ሰዎች አካባቢና በምንሠራበት ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡--Steps to Christ, p. 81. ChSAmh 143.1

    የክርስቶስን ሕይወትና አስተምህሮ የጥናታችን ማዕከል ካደረግን እያንዳንዱ እያለፈ ያለ ክስተት በአስደናቂ መልእክት የተሞላ ይሆናል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 63. ChSAmh 143.2

    ምድራዊው ሕይወት ሰማያዊ ሕይወት የሚጀመርበት ነው፡፡ ምድራዊው ሥነ ትምህርት የሰማያዊ መርኅዎች ጅማሮ ነው፡፡ በምድር እየተለማመድን የምንገኘው ሕይወትና አገልግሎት--የሰማያዊው ሕይወትና አገልግሎት ሥልጠና ነው፡፡Education, p. 307. ChSAmh 143.3

    ከክርስቶስ ጋር በኅብረት ለማገልገል ያገኙትን ልዩ መብትና ጥቅም የሚቃወሙ የክብሩ ተካፋይ ሊያደርጋቸው የሚችለውን ብቸኛውን ሥልጠና ለመውሰድ ይቃወማሉ፡፡ በዚህ ሕይወት የብርቱና ገናና ጸባይ ባለቤት ሊያደርጋቸው የሚችለውን ሥልጠና ለመውሰድ ይቃወማሉ፡፡Education, p. 264. ChSAmh 143.4

    ራስ ወዳዱን የሕይወት አቅጣጫ እየተከተለና የገዛ ፍላጎቱን እያገለገለ ወደ ጌታው ደስታ መግባት እንደሚችል አድርጎ ማንም አይገምት፡፡ እንዲህ ያለው ሰው በአፍቃሪና ከራስ ወዳድነት የጸዳ ደስታ ውስጥ ተሳታፊ መሆን አይችልም፡፡ _ ለሰማያዊዎቹ ቅጥሮች ብቁ አይሆንም:፡ በሰማይ የተንሰራፋውን ንጹሁን የፍቅር ንፍቀ ክበብ ማድነቅ አይችልም፡፡ የመላእክት ድምጽም ሆነ የበገናቸው ጣዕመ ዜማ እርካታ አይሰጠውም፡፡-Christ’s Object Lessons, pp. 364, 365. ChSAmh 143.5

    ክርስቶስ በመላው ምድር ተበታትነውና በኃጢአታቸው እየጠፉለሚገኙ በሺ ለሚቆጠሩ ነፍሳት በትዕግሥት ተግተን እንድንሠራ ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ የክርስቶስ ክብር ተካፋይ የሆኑ ደካማውን በመርዳት፣ ምስኪኑን፣ የተከፋውንና ተስፋ የቆረጠውን በመጎብኘት የአገልግሎቱ ተካፋዮች ሊሆኑ የግድ ነው፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 31. ChSAmh 144.1

    የቤተ ክርስቲያን አባላት አገልግሎት በሚሰጡባቸው ዘርፎች ሊሰለፉ ይገባል፡፡ አዳኙ የሰብዓዊውን ሐዘን እንደተካፈለ እነርሱም የባልንጀራቸውን ሐዘን ሲካፈሉ አብሮአቸው እየሠራ መሆኑን በእምነት ይመለከቱታል፡፡ Testimonies, vol. 7, p. 272. ChSAmh 144.2

    እያንዳንዱ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የእርሱን አምሳል ይወስድ ዘንድ እነሆ በፊቱ ይገኛል፡፡ ሰብዓዊ ፍጡሮች “የልጁን መልክ እንዲመስሉ” የቀደመው የእግዚአብሔር ውሳኔ ነው፡፡ ታጋሽ ፍቅሩ፣ ቅድስናው፣ ትሕትናው፣ ምህረቱና እውነቱ ለዓለም ሊገለጥ ይገባል፡፡--The Desire of Ages, p. 827. ChSAmh 144.3

    እያንዳንዱ ሰው ሁሉንም በመሰዊያው ላይ ሮ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ሁላችንም የኤልሳዕ ዓይነት አገልግሎት እንድንሰጥ ወይም ያለንን ሁሉ ሸጠን እንድንከተለው አልተጠየቅንም፡፡ ነገር ግን አገልግሎቱ የሕይወታችንን ቀዳሚ ስፍራ እንዲወስድና የእርሱን ዳግም ምጽአት የሚያፋጥን ሥራ ሳንሠራ አንድ እንኳ ቀን በከንቱ እንዳያልፍ እግዚአብሔር ይጠይቀናል፡፡ እርሱ ከሁሉም ሰዎች አንድ ዓይነት አገልግሎት አይጠብቅም፡፡ አንዱ ወደ ባዕድ አገር ተጉዞ አገልግሎት እንዲሰጥ ሌላው ደግሞ ለወንጌል ሥራ ድጋፍ የሚሆን ገንዘብ እንዲቸር ይጠየቃል፡፡ እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ስጦታ ይቀበላል፡፡ ይህ ድርጊት ሕይወትንና ተጓዳኝ የሆኑ አስፈላጊ ነገሮችን በሙሉ ቀድሶ መስጠት ነው፡፡ እንዲህ ያለውን የቅድስና ተግባር የሚፈጽሙ የሰማይን ጥሪ ይሰማሉ ይታዘዙማል፡፡Prophets and Kings, p. 221. ChSAmh 144.4

    በዓለም ያለው የሚጸልይ፣ ዕቅድ የሚያወጣና ስለ ንግድ ሥራውአጥብቆ የሚያስብ በጥበብ የተሞላ ሰው በዘላለማዊውም ነገሮች ጥበበኛ እንዲሆን አጥብቆ ሊጥር ይገባል፡፡ ምድራዊ ጥቅሙን አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚጥር ሁሉ በተመሳሳይ ጉልበቱን የሰማያዊው ሐብትና ሕይወት ባለቤት ለሚያደርገው ተግባር ለምን አያውለውም?- Testimonies, vol. 6, p. 297. ChSAmh 145.1

    እግዚአብሔር የወቅቱን እውነት ለማወጅ በትህትና ከሚላለሱ ጋር ይንቀሳቀሳል፡፡ ብዙዎቹ እነዚህ ሕዝቦች በጨለማ ለሚገኙት ብርሃን ለመስጠት በመንፈስ ቅዱስ ይል እዚህም እዚያም በጥድፊያ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ፡፡ እንደ ሰደድ እሳት በአጥንታቸው የሚንቀለቀለው እውነት መልእክቱን በጨለማ ለተቀጡት ያስተላልፉ ዘንድ በሚነድ ምኞት ይሞላቸዋል፡፡ ያልተማሩ ከሚባሉ መሃል የሆኑ ብዙዎች የእግዚአብሔርን ቃል ያውጃሉ፡፡ vጻናት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው የሰማይን መልእክት ለማወጅ ይወጣሉ፡፡ ለወቅቱ መልእክት ራሳቸውን ባዘጋጁት ላይ መንፈስ ቅዱስ ይፈስባቸዋል፡፡ ሰብዓዊውን ሕግና ደንብ አሽቀንጥረው ጥንቃቄ የተሞላው እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የጌታን ሠራዊት ይቀላቀላሉ፡፡-Testimonies, vol. 7, pp. 26, 27. ChSAmh 145.2