Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ውጤታማ ምሳሌዎች

    የምኅረት መልእከቱን ለአድማጮቹ እንደሚስማማ አድርጎ ያቀርብ ነበር፡፡ “ደካሞችን አበረታ ዘንድ ልዑል እግዚአብሔር ምን መናገ እንደሚገባኝ አስተምሮኛል” ለማለት የበቃው የእውነትን በረከት እጅግ በሚያጓጓ አኳኋን ለሰዎች ለማቅረብ ከንፈሩ በጸጋ የተቀባ ስለነበር ነበር፡፡ በጭፍን ጥላቻ ተሞልተው የነበሩትን ሰዎች የሚቀርበበት ዘዴ ስለነበረው አስገራሚ ምሳሌዎችን በመናገር አድማጮቹ አደረጋቸው፡፡ አስተሳሰባቸውን በመረዳት ወደ ልባቸው ደረሰ፡፡ ከየዕለት ኑሮ የተወሰዱት ምሳሌዎች ቀላል ቢሆኑም ጥልቀት ያለው አስገራሚ ትርጉም ግን ነበራቸው፡፡ የሰማይ ወፎችን፣ የሜዳ አበቦችን፣ ዘርን፣ እረኛንና በጎችን እንደ ምሳሌ በመጠቀም ስለ ዘላለማዊ እውነት ስተማረ፡፡ ከዚያ በኋለ አድማጮቹ እነዚህን ነገሮች ባዩ ቁጥር የእርሱን ቃል ለማስታወስ ቻሉ፡፡ የከርስቶስ ምሳሌዎች ያለ ማሰለስ ትምህርቱን ደግው ደጋግመው የሚያሳዩ ነበሩ፡፡-The Desire of Ages, p. 254.ChSAmh 172.2

    ሐዋርያት ስለ አብ እና የሰብዓዊው ዘር አዳኝ ስለሆነው ስለ ልጁ ዕውቀት ጣኦት አምላኪ ለነበረው ሕዝብ ለማካፈል ብርቱ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ በቅድሚያ የሕዝቡን ትኩረት ከሰብዓዊው ችሎታ ባሻገር ወዳለው አስደናቂ የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ በመመለስ--ጸሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ሥርዓታቸውን ጠብቀው ስለሚፈራረቁት ወቅቶች፣ ተራሮችን ስለሚያለብሰው ብርቱ የበረዶ ግግር፣ ስለ ተንዠረገጉት ግዘፍ ዛፎችና ሌሎች አስደናቂ ተፈጥሮአዊ ትዕይንቶች ነገሯቸው፡፡ ሐዋርያት እነዚህን የኃያሉን አምላክ ሥራዎች ተጠቅመው በባእድ አምልኮ የወደቀው ሕዝብ አእምሮ ስለ ታላቁ የዩኒቨርስ ገዢ እንዲያሰላስል አደረጉ፡፡The Acts of the Apostles, p. 180. 126 ChSAmh 173.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents