Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መንፈሳዊውን ነገር ለይቶ መረዳት አለመቻል

    ቤተ ክርስቲያን hርስቶስ የቀደደውን መንገድ ተከትላ ለመሥራት ቸል ማለቷ ያስከተለውን ውጤት በዓለም ብቻ አንመለከተውም፡፡ ይህ ቸልተኝነት ለቤተ ክርስቲያን የተሰጣት ከፍ ያለውና ቅዱሱ አምላካዊ ሥራ ላይ ጥላ እንዲያጠላ አድርጎአል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነቀፌታና የምሬት መንፈስ እንዲከሰት በማድረጉ የብዙዎች መንፈሳዊውን ነገር ለይቶ የመረዳት ክህሎት ደብዛዛ ሆኖአል፡፡ በዚህ የተነሳ የክርስቶስ አገልግሎት ለከፍተኛ እጦት ተዳርጎአል፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 297.ChSAmh 51.2

    እንደ ሕዝብ የምንገኝበትን ሁናቴ ሳስብ ከፍተኛ ሐዘን ይሰማኛል፡፡ የገዛ ራሳችን የማያቋርጥ ማፈግፈግ ከእግዚአብሔር ለየን እንጂ ጌታ የሰማይን ደጃፍ አልዘጋብንም፡፡ መታበይ፣ ስስትና ይህን ዓለም መውደድ በልባችን እንዲኖር በመፍቀዳችን ከእግዚአብሔር መለየት ወይም ኩነኔ ሊያስፈራን አልቻለም፡፡ እጅግ የከፋውን ኃጢአት በድፍረት እየሠራን ነው፡፡ ይህም ሆኖ ቤተ ክርስቲያን የተጠራችው እንድታብብና የተትረፈረፈ ሰላምና መንፈሳዊ ብልጽግና እንዲኖራት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀስ በቀስ ከመሪዋ ክርስቶስ እያፈገፈገች ወደ ግብፅ እያመራች ትገኛለች፡፡ መንፈሳዊውን ኃይል በመሻታቸው ይህን አሳሳቢ ሁናቴ ማስተዋል የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የአምላካዊውን ትንቢት መንፈስ ምስክርነት መጠራጠርና አለማመን እርሾ በየቤተ ክርስቲያኖቻችን ይታያል፡፡ ይህ አካሄድ ቤተ ክርስቲያን በሰይጣን ስር እንዳትወድቅ ያሰጋታል፡፡--Testimonies, vol. 5, p. 27. ChSAmh 51.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents