Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ማመንና ያመኑትን ገልጦ ማሳየት

    እያንዳንዱ በልብ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘ አስፈላጊ እውነት በሕይወት የሚገለጥበት መንገድ ሊያገኝ ይገባል፡፡ የክርስቶስን ፍቅር መቀበል ሰዎች ኃይሉን ለሌሎች ለመመስከር ከሚኖራቸው ምኞት ጋር ተመጣጣኝ አለው፡፡ መልእክቱን ለማወጅ የሚያደርጉት ማንኛውም እንቅስቃሴ አምላካዊው እውነት በገዛ ነፍሳቸው ላይ የከበረ ዋጋ እንዲኖረውና በስፋት እንዲሰራጭ የማድረግ ኃይል አለው:፡--Review and Herald, Feb. 19, 1889. ChSAmh 130.2

    እምነት ያለ ሥራ ሙት እንደመሆኑ እምነታችን ብዙ መልካም ፍሬዎችን የሚያፈራ ሊሆን ይገባል፡፡--Testimonies, vol. 4, p. 145.ChSAmh 130.3

    ወንጌልን በልባቸው የሚቀበሉ ሁሉ መልእክቱን የማወጅ ናፍቆት ያድርባቸዋል፡፡ ሰማያዊ ውልደት ያለው የhርስቶስ ፍቅር በተግባር ሊገለጥ የሚችልበትን መንገድ ማግኘቱ የግድ ነው፡:--Christ’s Object lessons, p. 125.ChSAmh 130.4

    ኃይላችንን ሁሉ ተጠቅመን በምንሰጠው ተጨባጭ አገልግሎት እግዚአብሔርን እያወድስን የከበረ ስሙን ይዘን ወደፊት እንገስግስ፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 300.ChSAmh 130.5

    ከሦስቱ መላእክት መልእክት ንድፈ ሃሳብ ጋር የሚስማማው የዚህ ጊዜ እምነታችን መገታት የለበትም፡፡ የመቅረዛችን ብርሃን ያለማቋረጥ እንዲበራ፣ የሕይወት ብርሃን በጨለማ ለሚገኙ የብርሃን ጸዳል እንዲሆን የሚያደርገው የክርስቶስ ጸጋ ዘይት ሊኖረን የግድ ነው:: Testimonies, vol. 9, p. 155.ChSAmh 131.1

    መንፈሳዊ ብርታታችሁና በረከታችሁ ከምትሰጡት የፍቅር አገልግሎትና ከመልካሙ _ ሥራችሁ ጋር ተመጣጣኝነት ይኖረዋል፡፡ Testimonies, vol. 3, p. 526.ChSAmh 131.2

    የእውነት ብርሃን ያላቸው ሁሉ እውነትን ቢለማዱ ኖሮ ብዙ ብርሃኖች ለክርስቶስ መብራት በቻሉ ነበር፡፡Testimonies, vol. 9, p. 40.ChSAmh 131.3

    እንደ ሕዝብ የሚጎድለን ነገር እንዳለ ተመልቼ ነበር፡፡ ሥራችን ከእምነታችን ጋር ተጣጥሞ መሄድ አልቻለም፡፡ እምነታችን ሟች ለሆነው ሰብዓዊ ፍጡር ከዚህ ቀደም ባልተሰጠ፣ እጅግ በከበረና አስፈላጊ በሆነ መልእክት እወጃ ስር መኖራችንን ቢመሰhርም ነገር ግን ተጨባጩ እውነታ እንደሚያሳየው ጥረታችን፣ ቅንአታችንና ራሳችንን መሥዋዕት አድርጎ የመስጠት መንፈሳችን ከሥራው ባህሪ ጋር የሚነጻጸር አይደለም፡፡ ከሙታን እንነሳ ክርስቶስ ሕይወት ይሰጠናል--Testimonies, vol. 2, p. 114.ChSAmh 131.4

    እንዳመናችሁ ሆናችሁ በእምነት ውጡ፤ ወንጌልንም አውጁ፡፡ በእናንተ ውስጥ ሕያው እውነት መኖሩን የምትመሰክሩላቸው ሁሉ ይመልከቱ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 42. ChSAmh 131.5

    የክርስትና መገለጫ መልካም ምግባር የሆነው ክርስቶስን የሚመስል ሕይወት ብርቱ ኃይል ያለው መሟገቻ ነው፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 21.ChSAmh 131.6

    ልባቸው ከአገልግሎት ጋር አንዳች ትስስር ሳይኖረው በክርስቶስ እናምናለን የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን የእግዚአብሔርን መልክ ብቻ ከያዙ ስብስቦች ተርታ በመመደባቸው ድርጊታቸው አብልጦ አታላይነታቸውን ያመላክታል፡፡ በነፍሳትን ላይ ውድመት ለሚያስከትለው ሰይጣን ስኬታማ ወኪሎች በመሆን በራሳቸው ላይ የከፋ ኩነኔ ያስከትላሉ፡፡--Review and Herald, March 27, 1888.ChSAmh 131.7

    የጌታን መምጣት የሚጠባበቁ ሁሉ ለእውነት ታዛዥ በመሆን ነፍሳቸውን ያነጻሉ፡፡ ተግተው እየተጠባበቁ በቅንነት ይሠራሉ፡፡ የጌታ መምጫ እንደተቃረበ ስለሚያውቁ ነፍሳትን በማዳን ሥራ ከሰማያዊ ተወካዮች ጋር ለመተባበር ከፍተኛ ቀናኢነት ያድርባቸዋል “ለአገልጋዮቹ ምግባቸውን በወቅቱ” የሚሰጡ ታማኝና ጠቢብ አገልጋዮች የሚባሉት እንደነዚህ ያሉት ናቸው፡፡ ለወቅቱ አስፈላጊ የሆነውን እውነት ያውጃሉ፡፡ ሔኖክ፣ ኖህ፣ አብርሐምና ሙሴ ለኖሩበት ዘመን አስፈላጊ የሆነውን እውነት እንዳሳወቁ ሁሉ እንደዚሁም የክርስቶስ ተከታዮች በእነርሱ ዘመን ለሚኖረው ትውልድ መሰጠት የሚገባውን ልዩ ማስጠንቀቂያ ያሳውቃሉ፡፡-The Desire of Ages, p. 634.ChSAmh 132.1

    በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ሚያስችለን ስለ እውነት ብዙ ማወቃችን ሳይሆን ያወቅነውን በተግባር መተርጎም መቻላችን ነው፡፡ ብዙ ብርሃን ኖሮአቸው የእግዚአብሔር አገልጋይ ነን እያሉ ነገር ግን ብርሃኑን ችላ በማለት በየዕለቱ ከእምነታቸው ጋር የሚቃረን ኑሮ ከሚኖሩ ይልቅ— ክፉውን ከበጎ ለይተው በመገንዘብ በጎውን የሚመርጡ እግዚአብሔርን የማያውቁ ሕዝቦች ከእነዚያኞቹ በተሻለ ሀኔታ ውስጥ ይገኛሉ፡፡The De sire of Ages, p. 239. ChSAmh 132.2

    ጌታችን የሱስ ክርስቶስን መሻት ብቻ ሳይሆን ምጽአቱን መፋጠን የእያንዳንዱ ክርስቲያን Aዩ መብትና ጥቅም ነው፡፡ ስሙን የተሸከሙ ሁሉ ለክብሩ ፍሬ ቢያፈሩ ኖሮ የወንጌል ዘር በመላው የምድር ገጽ እጅግ ፈጥኖ መዘራት በቻለ ነበር፡፡ የመጨረሻው ታላቁ መከር በፍጥነት ሲደርስ፤ ክርስቶስ ያን የከበረ ሰብል ሊሰበስብ ይመጣል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 69.ChSAmh 132.3

    ክርስቲያኖች የነፍሳቸው ደኅንነት በግል ጥረታቸው ላይ መተማመን የሚያደርግ እንደመሆኑ ከእንቅልፋቸው ነቅተው ችላ ያሉትን ኃላፊነት ይውሰዱ፡፡-Review and Herald, Aug. 23, 1881.ChSAmh 133.1

    እውነተኛ አምልኮ ከክርስቶስ ጋር በኅብረት መሥራትን ያካትታል፡፡ ጸሎት፣ ልባዊ ምክሮችና ንግግሮች ያለማሰለስ የተሳሰሩ ርካሽ ፍሬዎች ሲሆኑ፤ ነገር ግን በመልካም ዛፍ ላይ ለመብቀል ተፈጥሮአዊ የሆኑት-ለምስኪኑ፣ አባት ለሌለው፣ ባሏ ለሞተባት የሚደረጉ ጥንቃቄዎችና እገዛዎች በመልካም ሥራ የሚገለጡ ፍሬዎች ናቸው::-- Review and Herald, Aug, 16, 1881.ChSAmh 133.2

    የቤተ ክርስቲያን አባላት የተመደቡበትን ብርሃን የመቀበል እንዲሁም የማሰራጨት ኃላፊነት ይወሰዱ፡፡ በጌታ የወይን ተክል ያለ ሥራ የሚቀመጥ ማንም ሰው በይቅርታ ሊታለፍ አይችልም፡፡--Review and Herald, Feb. 19, 1889.ChSAmh 133.3

    ቅን በመሆን፣ መልካም ቃላትን በመናገርና ለድኾች፣ ለምስኪኖችና ጉዳት ለደረሰባቸው ርኅራኄ በማሳየት ፍሬ ለማፍራት የሚያስችለንን መርኅ እንድንከተል ክርስቶስ ይጠይቀናል፡፡--Review and Herald, Aug 16, 1881.ChSAmh 133.4

    በያዕቆብ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ከየሱስ ጋር የተነጋገረችው ሳምራቷ ሴት ሌሎችን ወደ እርሱ ለማምጣት ምንም ጊዜ አልወሰደባትም ነበር፡፡ በዚህም ከእርሱ ደቀ መዛሙርት የላቀ ውጤታማ መሆኗን አስመሰከረች፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የወንጌልን ዘር በሰማርያ ለመዝራት ተስፋ የሚጣልበት ሁኔታ መኖሩን መመልከት አልቻሉም ነበር፡፡ አስተሳሰባቸው በወደፊቱ ሥራ ላይ ተስፋ ከመጣል ውጪ በዚያኑ ወቅት፣ አጠገባቸው ለመሰብሰብ የደረሰ ሰብል መኖሩን አላስተዋሉም፡፡ ሆኖም በዚያች በናቋት ሴት አማካኝነት የከተማው ሰው ሁሉ የሱስን ለመስማት ግልብጥ ብሎ ወጣ፡፡ የተቀበለችውን ብርሐን በአንድ ጊዜ ወደ አገሯ ሕዝቦችአደረሰች፡፡ ይህች ሴት በሥራ ላይ የሚገኘውን ተጨባጩን የክርስቶስ እምነተ ትወክላለች፡ - The Ministry of Healing, p. 102.ChSAmh 133.5

    ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ግስጋሴ እያሳዩ፣ ቁጥራቸውን በእጥፍ እሳደጉና አብያተ ክርስቲያናትን እያዋቀሩ የእውነትን ሰንደቅ በጨለማው የምድር ክፍል እያውለበለቡ የሚገኙ ቢሆንም ሥራው እግዚአብሔር በሚፈልገው ፍጥነት እየሄደ አይደለም፡፡ ለምን? የቤተ hርስቲያን አባለት በየግላቸው ብርቱ ጥረት አድርገው ወደፊት ለመገስገስ ተነሳሽነት ስለሚጎድላቸውና--እያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ የጋለ ቅድስና፣ ቀናኢነት፣ ትህትናና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሠራተኞች እጦት ውስጥ በመውደቁ ነው፡፡ ለመሆኑ የክርስቶስ መስቀል ወታደሮች ወዴት ነው ያሉት? እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞች፣ በሁለት ልብ ያልሆኑና በጽናት ወደ አምላካዊው ክብር የሚለከቱ ሁሉ ከስህተት ጋር ለሚደረገው ውጊያ ራሳቸውን ያዘጋጁ፡፡ በዚህ መንፈሳዊ ውዝግብ በበዛበት ወቅት እያለከለኩና ልባቸው በፍርሃት እየራደ የሚገኝ አያሌዎች አሉ፡፡ ከድካማቸው ወጥተው ይበረታቱ፣ በጀግንነት ለመዋጋት ወደ ባእድ ሰራዊት ይገሥግሡ! Historical Sketches, p. 290.ChSAmh 134.1

    ማንም ቢሆን እግዚአብሔር የሰጠውን ኃይል ለመጠቀም ሲቃወም የነበረው እየሻገተና እየጠፋ የመሄዱ ነገር ዓለማቀፋዊ እውነታ ነው፡፡ ያልኖርነውና ለሌሎች ያላጋራነው እውነት ሕይወት የመስጠት ኃይሉንም ሆነ የመፈወስ በጎነቱን ያጣል፡፡The Acts of the Apostles, p. 206.ChSAmh 134.2

    እወደዋለሁ የሚሉትን አምላካዊ አውነት ታቅፎ በመኖር ፋንታ ወደ ፊት ይዞ የመገስገስን ያህል ለቅድስናዎ አጥንትና ጅማት መሆን የሚችል ነገር የለም፡፡Testimonies, vol. 4, p. 236.ChSAmh 134.3

    ያለ ሥራ ተቀምጠው በጸጋው አማካይነት የሚጡትን በረከቶች እየተቀበሉ የክርስትናን ህይወት ለምራት የሚሞክሩ ሳይሠሩ ለመብላት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ይv አካሄድ በመንፈሳዊውም ሆነ በተፈጥሮአዊው ዓለምምን ጊዜም ዝቅጠትና መበስበስ ያስከትላል፡፡--Steps to Christ, pp. 80, 81.ChSAmh 134.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents