Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለራሱ ቅድሚያ የማይሰጥ

    መልካም ለማድረግ ያለማሰለስ ይንቀሳቀስ የነበረው ክርስቶስ ምሳሌያችን ሊሆን ይገባል፡፡ ክርስቶስ በቤተ መቅደስ፣ በአይሁድ ቤተ አምልኮ፣ በዐውራ ጎዳና፣ በገበያ ማዕከል፣ በሥራ ቦታ፣ በባህር ዳርቻና በኮረብታማ ስፍራዎች እየተዘዋወረ ወንጌልን ይሰብክና የታመመውን ይፈውስ ነበር፡፡ ለእኔ የሚል ራስ ወዳድነት የማያውቀው የአገልግሎት ሐይወቱ በጥልቅ የምናጠናው መጽሐፋችን ሊሆን ይገባል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 31. ChSAmh 335.4

    ለጌታ እንድንሠራ የሚያነሳሳን ኃይል ለራሳችን ቅድሚያ ከመስጠት ጋር የሚያመሳስለው አንዳች ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት ለስጠት ሁል ጊዜም ከራስ ወዳድነት የጸዳ አምልኮና ራስን መሥዋዕት አድርጎ የሚሰጥ መንፈስ በፊትም ሆነ አሁን በቅድሚያ የሚጠየቁ ናቸው፡፡ የራስ ወዳድነት አንድ ድር እንኳ ሾልካ የሸማ ሥራው አካል እንድትሆን የጌታችንና የፈጣሪያችን ዕቅድ አይደለም፡፡ የጥንት የግንባታ ሠራተኞች የማደሪያውን ድንኳን እንዲሠሩ በፍጽምና አምላክ እንደተጠየቁ _ ሁሉ _ ብልሃት፣ ችሎታ፣ _ ትክክለኝነትና ጥበብ የጥረታችን አካል ሊሆን ይገባል፡፡ የላቀው ተሰጥኦ ወይም እጹብ ድንቅ የሆነው አገልግሎት ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው እኔነት ሕያው የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ በመሠዊያው ላይ ሲቀርብ ብቻ መሆኑን በአገልግሎታችን ሁሉ ማስተወስ ተገቢ ነው:: Prophets and Kings p 65.ChSAmh 336.1

    የተሐድሶ አራማጆች በምድር ከሚኖሩ ሕዝቦች በላቀ--ለራሳቸው ቅድሚያ የማይሰጡ፣ ደጎች፣ ትህትናና መልካም ምግባር የተላበሱ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ከራስ ወዳድነት መንፈስ የጸዳ እውነተኛ መልካምነት በሕይወታቸው ሊታይ የግድ ነው:፡- The Ministry of Healing, p. 157.ChSAmh 336.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents